የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.11K subscribers
1.84K photos
4 videos
1 file
54 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ኦፊሰሮች ከሰላም ሰራዊት አባላትና ከሌሎች የፀጥታ አካላት የህገወጥ መከላከልና የፀጥታ ስምሪት ተሰጠ

8/12/ 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት እና ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት "እኔ ለከተማዬ ሰላም ባለቤት እና ጠባቂ እሆናለሁ" በሚል መሪ ቃል የንቅናቄ መድረክ በማዘጋጀት ህገወጥነት የመከላከልና የፀጥታ ስምሪት የመስጠት ፕሮግራም በአበበ በቂላ ስታዲየም አካሂደዋል ።

በመድረኩ የተገኙት የአዲስ ከ/ ክፍለ ከተማ ዋና ሰራ አስፈጻሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ ክ/ ከተማችን ከሁሉም የከተማችን አካባቢ እና ከመላው የሀገራችን ክልሎች የተወጣጡ ማህበረሰብና ሸማቾች አንዲሁም የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ሰፊ ግብይት  የሚፈጽሙበት እንደመሆኑ በተደራጀ የፀጥታ ስምሪትና  ዲሲፒሊን አስተማማኝ ሰላሟ የሰፈነ ለነዋሪዎቿ ምቹ እንድትሆን ጠንክረን መሥራት ይገባናል ሲሉ ገልጸዋል ።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በበኩላቸው የክፍለ ከተማችን የፀጥታ አካላት ፣የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች እና የሰላም ሠራዊት ሰላምና ፀጥታን እንዲሰፍን በቅንጅት በመስራታቸው ህብረተሰቡ በሰላም ወቶ እንዲገባ እንዲሰራና የፈለገውን እንዲገበያይ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል ።
በቀጣይም ለሚከበሩት ሀይማኖታዊና የአደባባይ በዓላት ባህላዊ እሴታቸውን በጠበቀ መልኩ በሰላም ተከብረው እንዲጠነቀቁ ሁሉም አካላት የቅንጅት ስራቸውን በማጠናከር የበኩላችንን ኃላፊነት መወጣት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
👍5
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የአቅመ ደካማ ቤት ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቱ ቁልፍ አስረከበ

09/12/ 2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በክረምት በጎ ፍቃድ ስራ በወረዳ 02 ያስገነባውን የአቅመ ደካማ ቤት በማጠናቀቅ ለባለቤቱ አስረክቧል።

በፕሮግራሙ የተገኙት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ደንብ ማስከበር በከተማችን የሚስተዋሉ ደንብ መተላለፎችንና ህገ-ወጥ ተግባራትን ከመከላከል ጎን ለጎን ወደ ማህበረሰቡ በመውረድ ችግር ፈቺ የሆኑ ሰው ተኮር የበጎፍቃድ ስራዎችን በመስራት የችግኝ ተከላ፣ የደም ልገሳ፣የማዕድ ማጋራትና የቤት ዕድሳት ተግባራትን በማከናወን ለህብረተሰቡ ያለውን አለኝታነቱ በተግባር እያረጋገጠ መሆኑ ገልጸዋል ።

አክለውም የተጀመረው ሰው ተኮር በጎ ተግባር በቀጣይም በሁሉም ዘርፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል ።

በመርሐ ግብሩ ንግግር ያደረጉት የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት አቶ አበራ ኢቲቻ በክረምት የዘጠና ቀናት ዕቅድ 2 ቤቶችን ለመገንባትና ለማደስ ታቅዶ በዛሬው ዕለት አንዱን ቤት በራስ አቅም ኦፊሰሮችን ባለሀብቶችን በማስተባበር ከፈረሳ ጀምሮ እስከሚጠናቀቅ በየጊዜው ክትትል በማድረግና ሁሉም አካል የበኩሉን ሚና በመወጣት 1.3 ሚሊዩን ብር በላይ ወጪ ተደረጎበት ለምረቃ መብቃቱን ገልጸዋል ።

የቤት እድሳት የተደረገላቸው ወ/ሮ ውዴ ያኢ በተደረገላቸው በጎ ተግባር መደሰታቸውን በመግለፅ በተግባሩ ለተሳተፉ በሙሉ ላቅ ያለ ምሳጋቸውን አቅርበዋል።

በምረቃ ፕሮግራሙ የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ፣የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት አቶ አበራ ኢቲቻ ፣ የክ/ከተማው የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ኤርሚሾ ፣ የወረዳ 02 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አዱኛ ዘነበ ፣የወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣ ኦፊሰሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

የቤት ግንባታው ሲከናወን ድጋፍ ላደረጉ እና ለአስተባበሩ አካላት የእውቅናና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቷል ።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍6👏1
ባለስልጣኑ የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር አከናወነ

12- 12- 2017 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሰኞ ማለዳ ከስራ መግቢያ በፊት የሚያካሂደው የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር ፕሮግራም ከማዕከሉ ሰራተኞች ጋር አካሂዳል፡፡

በዕለቱ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ የስነምግባርና የጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬእተር እንደገለፁት በሳምንቱ ያሉትን የስራ ጊዜያቶች በንቃት ለማሳለፍና በሰራተኞች መካከል ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ተቀራርቦ ለመስራት ፕሮግራሙ የሚያግዝ ነው በማለት የመልካም ሳምንት ምኞታቸውን ገልጸዋል ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ የህግ ቡድን መሪ አቶ ብርሃኑ ኮርሳ የራሳቸውን የህይወት ተሞክሮ ለሰራተኞች ልምድና እውቀት ይሆን ዘንድ አካፍለዋል ።

በተጨማሪም የቤተሰብ ሕግን በተመለከተ ያዘጋጁትን ሰነድ ለሰራተኛው በሚመጥን መልኩ በዝርዝር አቅርበዋል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍4