ባለስልጣኑ በዛሬው እለት ወንዝና የወንዝ ዳርቻ የበከሉ ተቋማትን 2,600,000/ሁለት ሚሊየን ስድስት መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱ አስታወቀ
02/07/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ፍሳሽና በካይ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቁ ድርጅቶችና ግለሰቦች በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት የገንዘብ ቅጣቶች በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡
ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጆ ጥቁር አንበሳ እስፒሻላይዝድ ልዩ የካንሰር ህክምና ተቋም 400,000 ብር፤ በወረዳ 7 ኤክስትሪም ሆቴል 300,000 ብር እና ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተክርስቲያን 100,000 ብር ቅጣት ተቀጥተዋል።
በተጨማሪም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሙኒዝ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት 300,000 ብር፣ አል ሐኪም ቢዝነስ ድርጅት 400,000 ሺህ ብር እና ታዬ ቦጋለ የግል ድርጅት 100,000 ሺህ ብር ሲቀጡ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ፍቅር ፕላዛ 100,000 ሺህ ብር ተቀጥቷል።
በተያያዘ ዜና በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ድሬ ኢንዱሰትሪ ኃ/የተወሰነ የግል ማህበር 300,000 ብር ፤በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 የነገ ሰው ጽዳት ድረጅት 300,000 ብር እና በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ሰንሴት ሆምስ ድርጅት 300,000 ብር ቅጣት ተቀጥተዋል፡፡
ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በአጠቃላይ 2,600,000/ሁለት ሚሊየን ስድስት መቶ ሺህ/ ብር ቅጣት መቅጣቱ ገልጿል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው

👍10
ባለስልጣኑ በዛሬው እለት ደንብ ቁጥር 180/2017 የተላለፉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች 6,700,000/ስድስት ሚሊየን ሰባት መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱ ገለጸ
03/07/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቁ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት የገንዘብ ቅጣቶች በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱ ገለጸ፡፡
ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 1,800,000 ብር ፤በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 1,750,000 ብር፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ 1,200,000 ብር፣በጉለሌ ክፍለ ከተማ 600,000 ብር ፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ 400,000 ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል።
በተያያዘ ዜና በቦሌ ክ/ከተማ 450,000 ብር በኮልፌ ክ/ከተማ 400,000 ብር ፤በልደታ ክፍለ ከተማ 100,000 ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድ ለመንግስት ገቢ አድርጓል።
ባለስልጣኑ በአጠቃላይ በዛሬው እለት 24 ድርጅቶች እና 3 ግለሰቦች በድምሩ 6,700,000/ስድስት ሚሊየን ሰባት መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱ ገልጿል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

👍18❤1