የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.1K subscribers
1.83K photos
4 videos
1 file
54 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

የካቲት 20/2017 ዓ.ም
**አዲስ አባባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ባሉት ክፍት የስራ መደቦች ላይ ስራ ፈላጊዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በአካል በመምጣት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

አመልካቾች የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በመያዝ ፒያሳ እሪ በከንቱ አካባቢ ከኤሊያና ሆቴስ ወደ አብርሆት ቤተ-መፅሐፍ በሚወስደው መንገድ /EMA/ ህንጻ 8ኛ ፎቅ የባለሥልጣኑ የሰው ሀብት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08/11 ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በመሆኑም ዝርዝር መረጃውን የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም በወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ መመልከት ይችላሉ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
👍9
በወንዝና ወንዝ ዳርቻዎች ላይ የሚደርሱ ብክለቶችን ለመከላከል ይፋ በሆነው ደንብ ላይ ግንዛቤ ተፈጠረ።

21/6/2017 ዓ.ም
**የአዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ፣ከአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ መንገዶች ባለስልጣን እና ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል ደንብ ቁጥር 180/2017 አስመልክቶ ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቀቀ።

በልጠናው የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ባለስጣኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ አቅሙን በማጎልበቱ የከተማ አስተዳሩን ልማቶች ለመጠበቅ ተልዕኮዎች እየተሰጡት መሆኑን ጠቅሰው፤ የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል ዙሪያ በወጣው ደንብ ላይ የተሰጠንን የስራ ተልዕኮ ለመወጣት የግንዛቤ ፈጠራ አስፈላጊ በመሆኑ በየደረጃው ግንዛቤ ፈጠራው እንደሚቀጥል አፅኖት ሰጥተዋል።

በስልጠናው የወንዝና ወንዝ ዳርቻን ስለማልማትና ከብክለት ስለመከላከል፣ ስለ ተከለከሉ ተግባራት እንዲሁም ቅንጅታዊ አሰራር ስለቅጣት ዓይነቶች በሰፊው ገለፃ ተደርጓል።

ለማህበረሰቡ ከሚሰጠው ግንዛቤ በኃላ በቸልተኝነት ደንቡን ተላልፎ በሚገኝ አካል ላይ ዝቅተኛው የገንዘብ ቅጣት ሁለት ሺህ ብር ሲሆን ከፍተኛው እስከ አንድ ሚሊዮን ብር ድረስ የሚያስቀጣ እንደሆነ በደንቡ ተገልጿል።

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናውን የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የመስክ ክትትል ቁጥጥር ኦፊሰሮች ፣ የባለስልጣኑ ባለሙያዎች ፣ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በመጨረሻም ከሰልጣኞች አስተያየትና ጥያቄዎች ተነስተው የደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ሀላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዘገባው፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
👍1
የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል በወጣዉ ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ።

26/06 /2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠናና የቅድመ መከላከል ዘርፍ ከአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር
የወንዞች ዳርቻ ልማትን እና ብክለት ለመከላከል
በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ የሁለቱ ተቋማት ኃላፊዎች በተገኙበት የአሰልጣኞች ስልጠና በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሄደ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በከተማችን የሚገኙ ትላልቅና ትናንሽ ወንዞች ለልማት ውለው ለህብረተሰቡ መገልገያና ለቱሪስት መስብ እንዲሆኑ በርካታ ተግባራት በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ወንዞችን እና የወንዝ ዳርቻዎችን ከብክለት ጽዱ ለማድረግ ሁለቱም ተቋማት በጋራ በመቀናጀት ለመከላከልና የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት ዕውቀትና ልምድና ባለቸው አሰልጣኞች ስልጠናውን በመስጠትና ወደ ታች በማውረድ በየደረጃው ላሉ አካላትና ለከተማው ነዋሪዎች በቂ ግንዛቤ በመፍጠር ወንዝ ዳርቻዎችን እንዳይበከሉ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል ።

በመድረኩ የተገኙት የአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን ዮናስ የከተማችንን የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል ከተማዋን ፅዱ ፣ አረንጓዴ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ በከተማዋ ዉስጥ የሚገኙ ወንዝ ዳርቻዎች የማልማት ስራ እየተከናወነ ሲሆን ንፁህና ጤናማ አካባቢ እንዲሆኑ እና እንዳይበከሉ ለማድረግና ጥበቃ በማድረግ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ይህ ደንብ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ወንዞች ብክለት በአካባቢ እና በጤና ላይ የሚያደርሰው ጉዳት እና መፍትሔዎች እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል ደንብ ቁጥር 180/2017 ቀርቦ ግንዛቤ ተፈጥሮበታል።

ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ከተፈጠረ በኃላ በቸልተኝነት ደንቡን ተላልፎ በሚገኝ አካል ላይ ዝቅተኛው የገንዘብ ቅጣት ሁለት ሺህ ብር ሲሆን ከፍተኛው እስከ አንድ ሚሊዮን ብር ድረስ የሚያስቀጣ እንደሆነ በደንቡ ተገልጿል።

በስልጠናው ማጠቃለያም የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የወንዝ ዳርቻ ልማት እና ብክለትን መከላከል ዙሪያ በወጣው ደንብ ላይ የተሰጠንን የስራ ተልዕኮና ኃላፊነት ለመወጣት ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ ሰልጥኖ አሰልጣኞች በየደረጃው በመውረድ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራውን አጠናክረው ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበት ቀጣይ የስራ አቅጣጫ በባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ተሰጥቷል።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍31