የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.73K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ የመንገድ መሠረተ ልማት ያበላሸ ድርጅት 300,000 ብር በመቅጣት ተጠያቂ ማድረጉ ገለፀ

16/05/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ካሳንቺስ አካባቢ ጨለማን ተገን በማድረግ የሽንት ቤት ፍሳሽ ወደ ኮሊደር ልማት አስፓልት የለቀቀው ኢንተርናሽናል ሆቴል በደንብ ማስከበር ባለስልጣን፣ በሰላምና ጸጥታ እንዲሁም ከፖሊስ ጋር በጋራ በመሆን እጅ ከፍንጅ በመያዝ በጥፋታቸው መሰረት 300,000 ብር በመቅጣት ቦታውን እንዲያጸዱ ተደርጓል።

ባለስልጣኑ በከተማችን ውስጥ የተለያዩ ስራ ላይ የተሠማሩ የንግድ ድርጅቶችና ግንባታ ገንቢዎች ሁሉ ህግና አሰራርን በመከተል በተሠጣችሁ ፈቃድ መሰረት በመንግስትና በህዝብ ሀብት የተገነቡ መሠረተ ልማቶችን ደህንነት በመጠበቅ እንዲሰሩ መለዕክቱን አስተላልፏል፡፡

የአዲስ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በከተማው ደንብ በሚተላለፉ የግልና የመንግስት ድርጅቶች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቃል።

ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
👍101
ባለስልጣናኑ አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ እና ከፋና ቴሌቪዥን በጋራ ለመስራት የስምምነት ፊርማ ተፈራረመ

16/05/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የደንብ መተላለፎችን በተመለከተ የሚሰጠውን ግንዛቤ ለህብረተሰቡ ተደራሽነቱን ለማሳደግ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ በቴሌቪዥንና በሬዲዮፕሮግራም እና በፋና ቴሌቪዥን በኦሮምኛ ቋንቋ ፕሮግራም በጋራ ለመስራት የስምምነት ፊርማ ተፈራረመ ።

ባለስልጣኑ ህብረተሰቡን እያዝናና ግንዛቤ የሚፈጥሩ ፕሮግራም በማዘጋጀት የባለስልጣኑ ተልዕኮ ፣ የደንብ መተላለፍ አይነቶችና ጉዳታቸው ፣ ደንብ መተላለፎችና ቅጣታቸው የተመለከቱ ፕሮግራሞች በአዲስ ሚዲያ በአማርኛና በፋና ቴሌቪዥን በኦሮምኛ ቋንቋ በሰፉ ሴራ ፕሮግራም ለመስራት አቅዷል ።

በስምምነት ፊርማው የባለስልጣኑ አመራሮች ከተቋማቱ አመራሮችና ተወካዮች በተገኙበት ተፈራርመዋል።

ዘገበው :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ነው፡፡
👍9👏5
ባለስልጣኑ የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር አከናወነ

19/05 /2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሰኞ ማለዳ ከስራ ገበታ በፊት የሚያካሂደው የእውቀት ሽግግር ፕሮግራም የባለስልጣኑ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት አካሄደ፡፡

የመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ የእውቀት ሽግግር የተሞከሮ መድረክ በአመራሩና በሰራተኞች መካከል ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ተቀራርቦ ለመስራትና ለስራዎች ውጤታማነት የሚያግዝ መሆኑ ገልፀዋል።

በዕለቱ የባለስልጣኑ የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዬብ ከበደ የራሳቸውን የህይወትና የትምህርት እና የስራ ተሞክሮና ልምዳቸውን ለሌሎች አስተማሪ በሆነ መልኩ አጋርተዋል።

በእውቀት ሽግግር መድረኩ ሰራተኞች ስራቸውን አክብረው በመስራት በእውቀትና በክህሎት ራሳቸውን መገንባት እንዳለባቸው እና ተገልጋዮችን በቅንነት ማገልገል እንደሚገባቸው አቶ እዬብ ከበደ ተናግረዋል፡፡

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
ባለስልጣኑ የተመደቡት አመራር ከተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ጋር ትውውቅ አደረጉ

ጥር 19/2017 ዓ.ም


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በምክትል ስራ-አስኪያጅ ማዕረግ የስልጠና እና የቅድመ መከላከል ዘርፍ ሃላፊ ሆነው ወደ ተቋሙ የተመደቡት አቶ ንጋቱ ዳኛቸውን ከተቋሙ የማዕከልና የክፍ ለከተማ አመራሮች በተገኙበት ከመላው የባለስልጣኑ ሰራተኞች ጋር ትውውቅ አደረጉ።

በመድረኩ የቀድሞ የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅነት ያገለገሉና አሁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት የተሾሙት ኮማንደር አህመድ መሀመድን የሽኝት ፕሮግራም ተደርጓል።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ወደ ተቋሙ ተመድበው ለመጡት አቶ ንጋቱ ዳኛቸውን ወደ ተቋሙ እንኳን ደና መጡ በማለት ከተቋሙ ለተዘዋወሩት ኮ/ር አህመድ መሀመድን ለባለስልጣኑ ስኬት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበው መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።

ተቋሙ ውስጥ ያለው አንድነት ለስራዎች መሳካት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን በቆየሁበት ጊዜ መረዳት ችያለው በማለት ለተደረገኝ የሽኝት ፕሮግራም ከልብ አመሰግናለሁ ሲሉ የቀድሞ የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ የአሁኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ኮማንደር አህመድ መሀመድ ገልጸዋል ።

በቀጣይ የተጀመሩ ስራዎችን ከአመራሩና ከሰራተኞ ጋር በጋራ በመሆን በማስቀጠልና በማከናወን ውጤታማ በመሆን የተሰጣቸውን ሀላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ተናግረዋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
👍14🤔5