የእንኳን ለ2017 ዓ.ም የጥምቀትና በዓል በሰላመ አደረሳችሁ!
ጥር 10/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሠላም አደረሳችሁ እያለ፤በዓሉ የሠላም፣
የፍቅር እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱ ይገልፃል።
የጥምቀት በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እምነታቸውን በነፃነት በአደባባይ ወጥተው በጋራ የሚያከብሩበት ፣የእርስ በርስ ግንኙነታቸውን የበለጠ የሚያጠናክሩበት ፣መንፈሳዊ እሴቶቻቸውን የሚያዳብሩበት እና ማህበረሰባችን ተቻችሎና ተከባብሮ በጋራ መኖርን ለመላው የዓለም ህዝቦች ተምሳሌትነቱን የሚያሳዩበት ታላቅ በዓል ነው።
በዓሉ የአብሮነትና የሰላም በመሆኑ በዓሉ ስናከብር በጋራ፣በመተሳሰብ፣ በአንድነት የበዓሉን ሀይማኖታዊ ይዘቱንና ኢትዮጵያዊ ዕሴቶቻችንን በጠበቀ መልኩ ሊናከብረው ይገባል።
በዓሉ ስናከብር በከተማው የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች እና ተያያዥ ህገ ወጥ ተግባራት እንዳይፈጸሙ፣የኮሪደር ልማት ስራዎች እንዳይበላሹ እና በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የበኩልን ድርሻ እንዲወጣ አደራ ማለት እወዳለሁ፡፡
መልካም የጥምቀት በዓል !
ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ዋና ሥራ-አስኪያጅ

ባለስልጣኑ በመጀመሪያው 6ወራት ከባለድርሻ ጋር በቅንጅት በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ከ27 ተቋማት ጋር የአፈፃፀም ግምገማ እና የእውቅና መድረክ አካሄደ።
13/05/2017 ዓ.ም
**አዳማ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት በመጀመሪያው 6 ወራት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀም ለመገምገም በዛሬው ዕለት የከተማውና የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ፣የተቋሙ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ የሚገኙ የባለስለጣኑ አመራሮች በተገኙበት የአፈፃፀም ግምገማ እና የእውቅና መድረክ አካሄደ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንዳሉት ከተማችን አዲስ አበባ የበርካታ ዲፕሎማት ማረፊያ ናት፤ ተቋሙ ስሟ እና ተግባሯ ተመሳሳይ እንዲሆን እየሰራ የሚገኝ መሆኑን ገልፀዋል።
ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የደንብ መተላለፎችን የሚጠየፍ ህብረተሰብ ከመፍጠር አንፃር ውጤት እያስመዘገበ መሆኑ ገልፀዋል።
ተቋሙ በህግ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስራዎችን ለመስራት ጥረት እያደረገ እና የህግ ማስከበር ስራዎችን በማዘመን ላይ ይገኛል ሲሉ ገልፀው ሸስራው ዘላቂ እንዲሆን ተቋሙ ከተፈራረማቸው ተቋማት ጋር የተመዘገቡ እምርታዊ ውጤቶችን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ የፍትህና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር ሙሉነህ ደሳለኝ እንዳሉት የቅንጅት እና የትብብር አሰራር በድጋፍ ክትትል እንዲሁም በምዘና ወቅት ትኩረት እንዲሰጠው ማሳሰቢያዎችን እንሰጥ ነበር ሲሉ ተናግረው የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የመጀመሪያው ተቋም ነው ብለዋል።
አክለውም በመናበብ የከተማችንን ነዋሪዎች የምናገለግል ልንሆን ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
የእንኳን ደና መጣቹ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንዳሉት በ 2017 ዓ.ም የ6ወራት የስራ አፈፃፀም በጋራ ከሰራናቸው 27 ባለድርሻ ተቋማት ጋር በመሆን የምንገመግም ይሆናል ብለዋል።
በ6ወራት ውስጥ አብረን በሰራነው ልክ 56.8 የደንብ መተላለፎችን መቀነስ መቻሉን ገልፀው። በቅንጅት በመስራት በርካታ ውጤቶችን ያስመዘገብን ሲሆን ለዚህም በጊዜው ተገናኝተን ውይይት ማድረግ በመቻላችን ነው ሲሉ ተናግረው። ይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
በመቀጠልም ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በ6ወራት ውስጥ የተሰሩ ስራዎች አፈፃፀም በስታንዳርዳይዜሽን ዝግጅትና አገልግሎት ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ዳንኤል ቀፀላ ቀርቧል።
በቀረበው ሰነድ ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን የውይይት መድረኩን የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ የአዲስ አበባ ከተማ የፍትህና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር ሙሉነህ ደሳለኝ እና የባስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ከመድረኩ ለተነሱ ሀሳብ እና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ተሰቶባቸዋል።
በመጨረሻም ከተቋሙ ጋር በጣም ከፍተኛ እና ከፍተኛ አፈፃፀም ላላቸው ባለድርሻ አካላት የእውቀና ሽልማት በተቋሙ ተበርክቶላቸው መድረኩ ተጠናቋል።
ዘገባው:-የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

ባለስልጣኑ የ6 ወራት ቅንጅታዊ ስራዎች አፈፃፀም የእውቅና ሰጠ
13/05/2017 ዓ.ም
**አዳማ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት በመጀመሪያው 6 ወራት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀም በመገምገም የከተማውና የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ባለድርሻ አካላት በጣም ከከፍተኛ እና ከፍተኛ አፈፃፀም ለስመዘገቡ ለ27 ተቋማት እውቅና ሰጥቷል።

ለከተማው ፈጣን እድገት የሚመጥን ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥና እና ህገ-ወጥነትን መከላከል መቻሉ ተገለፀ
15/05/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የ 2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚገኙ አመራሮችና ዳይሬክተሮች በተገኙበት የጋራ የግምገማ መድረክ አካሄዱ ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር እና ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ ባከናወናቸው ተግባራት የከተማችንን ፈጣን እድገት የሚመጥን በከተማችን ላይ ዘላቂ ሰላም ማምጣት፣ የህብረተሰቡን የጸጥታ ስጋት መቀነስ እና ህገወጥነትን መከላከል ተችሏል ሲሉ ገልጸዋል ።
አክለውም በቅርቡ በተከበሩት የአደባባይ በዓላት የሀይማኖታዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን የታየበት ሆኖ በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ለተወጡ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
የባለስልጣኑ ዋና ሰራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት በስድስት ወራት ውስጥ በቅንጅት በመሰራቱ የከተማችንን ሰላም ማስጠበቅ እና የደንብ መተላለፎችን መቀነስ መቻሉን ገልፀው።
በቀጣይ ህዝብን የሰላም ባለቤት በማድረግ አጋዥ ሀይል አንዲሆን ማብቃት ፣ ተቋማችንን በቴክኖሎጂ የማዘመን ሰራዎችን ማጠናከር እንዲሁም በመዲናዋ የተገነቡ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ደህንነታቸው እንዲጠበቅ እና ህብረተሰቡ በአግባቡ እንዲጠቀምባቸው እየተሰራ ያለው ሰፊ የጥበቃ ሰራ በቀጣይነት ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮን የ6 ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማስረሻ ሀብቴ ቀርቧል።
ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር በመስራት በከተማዋ ውስጥ ሠላምን የሚያደፈርሱ አዝማሚያዎችን ቀድሞ በመለየት እና አንዳንድ የተፈጸሙ የወንጀል ድርጊቶችን ሳይባባሱ በቅንጅት በመከላከል የከተማውን እና የህብረተሰቡን ደህንነት በማስጠበቅ ላይ እንደሚገኝ በሪፖርቱ ተጠቅሷል ።
የባለስልጣኑ የ2017 የግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በባለስልጣኑ እቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል።
በሪፖርቱ ባለስልጣኑ የተቋም ግንባታ ሰራዎች ማከናወኑን ፣የሥልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን በስፋት መስራቱ ተጠቅሷል ።
ከደንብ ተላላፊዎች ቅጣት እና ከተወረሱ ንብረቶች ጨረታ ሽያጭ ከ135 ሚሊዮን ብር በላይ ወደ ፋይናንስ ገቢ ማድረግ መቻሉን ተገልጿል ።
በቀረቡት ሪፖርት ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን ለቀረቡት ሀሳብና አስተያየቶች የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እና የባስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ምላሽና ማብራሪያ ተሰቶባቸዋል።
ዘገበው :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ነው።