የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
996 subscribers
1.5K photos
4 videos
1 file
51 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ በአገልግሎት አሰጣጥ እና ደንበኞች አያያዝ ላይ ስልጠና ሰጠ:

ህዳር 26/2017
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠና ጥናት ዳይሬክቶሬት ከፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር በደንበኞች አገልግሎት አስጣጥ እና አያያዝ ዙሪያ ለማእከል እና ክፍለ ከተማ ሲቪል ሰራተኞች በባለስልጣኑ መሰብሰባያ አዳራሽ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በመክፈቻ ንግግራቸው ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከከተማ አስተዳደሩ የተጣለበት ህዝብን በቅንነት በታማኝነት አገልግሎትን በጥራት የመስጠት ኃላፊነትን በመወጣት ላይ የሚገኝ ተቋም እንደመሆኑ እንደነዚ አይነት ስልጠናዎች መዘጋጀታቸው ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው ብለዋል::

በመ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅና የቅድመ መከላከል እና ስልጠና ዘርፍ ኃላፊ ኮ/ር አህመድ መሀመድ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱን ጤናማ ለማድረግ ስልጠናዎች መሰጠታቸው ትልቁን ድርሻ እንዳለው ገልፀዋል::

ስልጠናው ከትምህርት ተቋማት ከምናገኘው እውቀት ባሻገር እንደነዚህ አይነት ስልጠናዎች መዘጋጀታቸው ስራችንን ብቁ እና ተወዳዳሪ ከማድረግ አኳያ ትልቅ አስተዋፆ እንዳለው መረዳት እንደሚገባ ገልፀው ከዛሬው ስልጠና ትምህርት ወስዳችሁ ቅን ታዛዥ ታማኝ የሆነ አገልጋይ እንድትሆኑ መልክቴን አስተላልፋለው በማለት የመክፈቻ ንግግራቸውን አስተላልፈዋል::

የአገልግሎት አሰጣጥ እና የደንበኛ አያያዝ ስልጠና ሰነዱን ያቀረቡት ወ/ሮ ሰላማዊት ይመር ስለ አገልግሎት አሰጣጥ ምንነት, ስለ ተገልጋይ ስነ-ልቦና አረዳድ ክህሎት, ስለ አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት እንዴት ማዘመን ይቻላል,በሚል አቅርበዋል።

ስልጠናው የደንበኛን ቅሬታ ማስተናገጃ መንገዶችን በትክክል ከመረዳት እና የመፍቻ መንገዶች ጋር በተያያዘ እንዲሁም ስለ አጠቃላይ ፅንሰ ሀሳቡ በማንሳት የተቋሙን ባህሪ መሰረት በማድረግ ተሰጥቷል ::

በመጨረሻም ተሳታፊዎችም የመንግስት ተቋም የራሱ የሆነ የአሰራር ስርአት እና የህግ ማዕቀፍ ያለው በመሆኑ አገልግሎት አሰጣጡ ያንን ማዕከል ያደረገ እንዲሆንና ሰራተኞችም ስራችን በጥራት በመከወን እና ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት ይገባናል የሚሉ ሀሳብ አስተያየት ሰጥተዋል::

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይም የባለስልጣኑ የኦንላይን ቅሬታ መቀበያ ፎርም ለማግኘት የተዘጋጀ ሊንክ እና አተገባበር በተመለከተ በተቋሙ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ አቶ ሚሊዮን ካሳሁን ተዋውቋል::

ምክትል ስራ አስኪያጅ ኮ/ር አህመድ መሀመድ ስልጠናው መሰጠቱ በቀጣይ ከኛ ምን ይጠበቃል የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ እና ስልጠናው ወደ ተግባርም መቀየር እንደሚያስፈልግ ተገንዝበን የአገልግሎት አሰጣጣችንን ልናሻሽል ልናዘምን እንደሚገባ ገልፀዋል።
ባለስልጣኑ በለውጥ አመራር እና በውሳኔ ሰጪነት ላይ ስልጠና ሰጠ

05/04/2017 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከማዕከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ አመራሮች በስልታዊ አስተቃቀድ፣ በአስተዳደር ፣ውሳኔ ሰጪነትና እና የለውጥ አመራር ላይ ስልጠና ሰጠ።

የስልጠናው መክፈቻ ንግግር ያደረኩት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የተቋማችን የቅድመ መከላከል እና ስልጠና ዘርፍ በእቅድ ውስጥ በመያዝ የአመራሮችን አቅም ይገነባል ተብሎ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል።

አክለውም ሰልጣኝ አመራሮ በሚኖረው የ3 ቀናት ቆይታ በስልጠናው መሰረት የተቋሙን ፍላጎት እና አላማ አውቆ ወደ ስራ መግባት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።

ስልጠናው ከኢትዮጲያ ስራ አመራር ኢንሰቲትዩት በመጡ አሰልጣኝ ዶ/ር ጀቤሳ ተሾመ እና በአቶ ሀገር መኩሪያ ለቀጣይ 2 ቀናት የሚቀጥል መሆኑ ተገልጿል።

የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ ኮማንደር አህመድ መሀመድ ስልጠናው በእውቀት ላይ የተመሰረተ አመራር ለመፍጠር ወሳኝነት እንዳለው ተናግረው ስልጠናው ለቀጣይ ሁለት ቀናት በጥብቅ ዲሲፕሊን እንደሚመራ ገልፀዋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
የአንካራው ስምምነት የተገኘው ውጤት የሀገራችን ጠንካራ የዲፕሎማሲ ውጤት ማሳያ መሆኑን ተገለፀ

07/04/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የማዕከል፣የክፍለ ከተማና የወረዳ ኃላፊዎች እእንዲሁም የማዕከሉ ዳይሬክተሮች በተገኙበት በወቅታዊ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የተደረሰውን የአንካራ ስምምነት ተከትሎ የውይይት መድረክ ተካሄደ።

የውይይቱ መነሻ ሰነድ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ ቤት የአቅም ግንባታ እና የፖለቲካ ዘርፍ ምክትል ሀላፊ አቶ ዘውዱ ከበደ የአንካራው ስምምነት የተገኘው ውጤት የሀገራችን ጠንካራ የዲፕሎማሲ ውጤት ማሳያ መሆኑ ገልፀዋል።

በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ተፅኖ ፈጣሪነት ለማሳጣት በጎረቤት ሀገራት በጠላትነተ ለማስፈረጅ የየተዘጋጁ አካላት ሴራ ያከሸፈ መሆኑ ገልፀዋል።

አክለውም ስምምነቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ጥበብና ብስለት በተሞላበት መንገድ ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ጥያቄ በህጋዊ መልኩ ምላሽ የተገኘበት መሆኑ ገልፀዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በአንካራው ስምምነት በርካታ የኢኮኖሚ ትሩፋቶች የሚያስገኝ በመሆኑ የተጀመሩ የልማት ስራዎች አጠናክሮ በማስቀጠል የሀገራችን ብልፅግና እውን ለማድረግ የሚያጠናክር መሆኑ ገልፀዋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።