የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት በበጀት አመቱ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገቡ ተገለፀ
15/10/2016ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት በ2016 በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም እንዲመዘገብ ላደረጉ አካላት የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም አካሄደ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አይዳ አወል በበጀት ዓመቱ በክፍለ ከተማው ከደንብ ማስከበር ተቋም ጋር በርካታ የፀጥታ እና የደንብ ማስከበር ተግባራት መከናወናቸውን በመግለፅ በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት መዘጋጀት ይገባል ብለዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አክለውም ክ/ከተማው የንግድ እና የሰዎች እንቅስቃሴ የሚበዛበት በመሆኑ በቀጣይ ብዙ የሚቀሩ ስራዎች ስላሉ ለማስተካከልና በቀጣይ አብሮ ለመስራት እንዲሁም ለፅ/ቤቱ በሚያስፈልገው ሁሉ ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸው ገልፀዋል።
በመድረኩ የእንኳን መጣቹ ንግግር ያደረጉት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ደረጄ ነገሮ በበጀት አመቱ በደንብ መተላለፎች በግንዛቤ እና በቁጥጥር ተግባራት የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገቡ ገልፀዋል።
በተጨማሪም ፕሮግራሙ የተዘጋጀው በ2016 በጀት አመት ለተሰሩ ውጤታማ ስራዎች አመራሮች እና ኦፊሰሮች ለማመስገን የተዘጋጀ የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም መሆኑና በቀጣይ በጀት ዓመት በጥንካሬ ያገኘናቸውን ለማስቀጠል ክፍተቶቹ ለመሙላት መነቃቃትን ለመፍጠር የተዘጋጀ መድረክ መሆኑ ገልፀዋል።
የመድረኩ የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በንግግራቸው በከተማችን ደንብ መተላለፎች ከመከታተል እና ከመቆጣጠር ባሻገር እንደስሟ አዲስና ውብ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰራ መሆኑ ጠቁመዋል።
በመጨረሻም በበጀት አመቱ በፅ/ቤቱ የተሻለ አፈፃፀም እንዲመዘገብ ጉልህ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

👍5
"ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም!” ሀገር አቀፍ የጎዳና ሩጫ ውድድር እየተካሄደ ነው
ሰኔ 30/2016 ዓ.ም
ሰላምን አስመልክቶ የተዘጋጀ ሀገር አቀፍ የ6 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች እየተካሄደ ነው።
ውድድሩ “ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም!” በሚል መሪ ሀሳብ ከማለዳ 12 ሠዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋና በሌሎች ዋና ዋና የክልል ከተሞች እየተካሄደ ነዉ ።
በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው መርሐ ግብር ታዋቂ አትሌቶችና ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች እየተሳተፉ ነው።

👍9👏2