የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.12K subscribers
1.85K photos
4 videos
1 file
54 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ማስታወቂያ
ግንቦት 14/2016 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አድራሻ ለማወቅ ከዛሬ ጀምሮ በየትኛውም የአለም ሀገራት ላይ በመሆን በጉግል ማፕ/Google Map/ በመጠቀም ማየት የሚቻል መሆኑን በደስታ እንገልፃለን።

የባለስልጣኑ አድራሻ በቀላሉ ሁሉም ሰው ማግኘት እንዲችል ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመግባት
1. rate፦ የሚለው ላይ 5ኛው የኮከብ ምልክት በመጫን፤
2. Comment፡- በሚለው ላይ ጠቃሚ መሆኑን ሀሳብ በመስጠት፤
3. Helpful:-የሚለው በመንካት ለሁሉም ማህበረሰብ እንዲደርስ በማድረግ የበኩሎን እንዲወጡ በአክብሮት እንጠይቃለን።

የደንብ መተላለፎችን በጋራ እንከላከል!
የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

https://maps.app.goo.gl/aUor5q24AvhbqLLN8
👍5
በሀገር አቀፍ ተነባቢ በሆነው አዲስ ዘመን ጋዜጣ በዛሬው እትሙ "በታሪካዊ ተቋም ታሪካዊ ስልጠና " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የተቋማችን ዓምድ እንድታነቡ በአክብሮት ተጋብዘዋል።

የደንብ መተላለፎችን በጋራ እንከላከል!

የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
👍156👏4
ባለስልጣኑ በደንብ ቁጥር 150/2015 ዙርያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ

26/09/2016ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ የደ/መ/መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት በደንብ ቁጥር 150/2015 ላይ ለእድር ምክር ቤት አመራሮች ፣ ለባለድርሻ አካላት እና በከተማው በየአካባቢው ለተወከሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መድረክ በአራዳ ክ/ከተማ መሰብሰቢያ አዳራሽ ሰጥቷል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከህብረተሰቡ ለተወጣጡ አካላት በደንብ ቁጥር 150/2015 በተመለከተ ግንዛቤ ለመፍጠር የተዘጋጀው ስልጠና በሰነድ በባለስልጣኑ በስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ እዬብ ከበደ ተሰጥቷል።

በሰነዱ የባለስልጣኑ አደረጃጀት፣ተጠሪነት እና ተግባር ኃላፊነት ፣ በህገወጥ ንብረት አያያዝ አሻሻጥና አወጋገድ ፣ ስለ አስተዳደራዊ ቅጣት እርምጃ አወሳሰድና አቤቱታ አቀራረብ ፣ የፖራ ሚሊተሪ ሰራተኞች ኦፊሰሮች ተግባርና ኃላፊነት ፣ የፖራ ሚሊተሪ ሰራተኞች ምልመላ ቅጥር ምደባ ዝውውርና ድልድል ፣ የፖራ የፖራሚሊተሪ ኦፊሰሮች ደመወዝና የሰራ ሰዓት ፣ የኦፊሰር ግዴታ እና ስነምግባር ፣ የዲስፕሊን እርምጃዎች የቅሬታ አቀራረብና አገልግሎት ሰለማቋረጥ እንዲሁም ልዩ ልዩ ድንጋጌዎችና የቅጣት ሰንጠረዦች በዝርዝር ተብራርቷል ።

በመጨረሻም ከሰልጣኞች ውይይት በማድረግ ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች በአሰልጣኙ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው ስልጠናው ተጠናቋል።

ዘገባው ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍4
ወታደራዊ እና ንድፈ ሀሳባዊ ስልጠና ሲሰለጥኑ የቆዮ ነባር የደንብ ማስከበር አመራሮች እና ኦፊሰሮች በዛሬው ዕለት ተመረቁ

ሰኔ 2/2016 ዓ.ም
*ሰንዳፋ*

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሰንዳፈ በሚገኘው የኢትዮጲያ ፖሊስ ዮኒቨርስቲ ያሰለጠናቸው የክፋ ለከተማ እና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ከ 5000 በላይ ኦፊሰሮች የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ የሰንዳፋ ከተማ ከንቲባ፣ የደንብ ማስከበር አመራሮች፣ የኢትዮጲያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የአዲስ አበባ የከተማ አስተዳደር የተለያዩ የቢሮ ሃላፊዎች እና የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል።

በምረቃ ዝግጅቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በከተማዋ የሚስተዋሉ የመሬት ወረራና ሌሎች የደንብ መተላለፎችን በተደራጀ መልኩ ለመከላከል ያስችል ዘንድ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የኢፌዲሪ ፓሊስ ዮኒቨርስቲ ጋር በመተባበር አቅማቸው የመገንባት ስልጠና ተከናውኗል፤ በመሆኑም ሰልጣኞች በወሰዳችሁት ስልጠና እና ልምድ በመታገዝ በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን በቁርጠኝነት እንዲቆጣጠሩ አደራ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የኢትዮጲያ ፓሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ አንጋፍ ተቋማቸው በርካታ ስልጠናዎችን እየሰጠ ሀገራዊ ግዴታውን እየተወጣ የሚገኝ ተቋም መሆኑን እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በመሆን ለኦፊሰሮች እንዲሁም አመራሮች በአጭር ጊዜ ውስጥ በማሰልጠን ለምረቃት ማብቃታቸውን ገልፀዋል።

ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ በንግግራቸው ለሰልጣኞች በስልጠናው ያገኙትን እውቀት በተግባር እንዲያውሉት አሳስበው በስልጠናው ሂደት ለተባበሩ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ በአዋጅ 74/2014 ከተቋቋመ ጀምሮ በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ተልዕኮ እየተወጣ መሆኑና ከዘመኑ ጋር እኩል የዘመነ ለማድረግ አቅምን የማጎልበት የስልጠና ስራ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ገልፀዋል።

አያይዘውም በእውቀት ላይ የተመሰረተ የደንብ መተላለፎችን ለመከላከል በሚያስችል ሁኔታ ለተከታታይነት ያለው አቅምን የሚሞላ ስልጠና ለአመራሮችና ለኦፊሰሮቻችን በአንጋፋው ፖሊስ ዮኒቨርስቲ የንድፈ ሀሳብ እና የአካል ብቃት እንዲወስዱ መደረጉ ተናግረዋል።

እነዚህ ኦፊሰሮች ወደ ስራ ሲሰማሩ ብቃት እና ጠንካራ ስምሪት የሚሰጥ አመራር ያስፈልጋል በመሆኑም የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮችን ጎን ለጎን ስልጠናዎችን እንዲወስዱ ማድረግ እና በዛሬው ዕለት ማስመረቅ ተችሏል ብለዋል።

ወደ ስራ ስትሰማሩ በስልጠናው ያገኛችሁትን እውቀት ያለምንም ስስት በአገልጋይነት መንፈስ በመላበስ ወደ ስራ እንድትገቡ አደራ በማለት ለስልጠናው ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በመጨረሻም ለስልጠናው መሳካት አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት የእውቅት እና ሽልማት በማበርከት ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሮክቶሬት ነው ።
5