የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.12K subscribers
1.85K photos
4 videos
1 file
54 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ የአቅመ ደካማ ቤቶችን ገንብቶ በማጠናቀቅ ለቤት ተጠቃሚዎች አስረከበ

ግንቦት 10 /2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በክፍለ ከተማው ወረዳ 12 ያስገነባቸው የ3 ደጋፊ የሌላቸው አባወራ እና እማወራ 7 ክፍል ቤቶች በማጠናቀቅ በዛሬው እለት ለቤቶቹ ተጠቃሚዎች ቁልፍ አስረከበ።

በቁልፍ ርክክብ ፕሮግራሙ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ፣ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ፉፋ፣የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ሰራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ኤጀና እና ፣የአቃቂ ቃሊቲ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኣበራ ኢቲቻና ሌሎች የክ/ከተማውና የወረዳ ደንብ ማስከበር አመራሮች፣ ኦፊሰሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

በፕሮግራሙ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በባለስልጣኑ የበጎ ፈቃድ ሰራ ላይ አየተሰራ ያለው ተግባር የሚደነቅና የሚበረታታ መሆኑ በመግለፅ የአቅመ ደካማውን ማህበረሰብ ማገዝና ወደ ተሻለ የኑሮ ደረጃ የማምጣት ሚና የሁሉም ሀላፊነት መሆኑን ተናግረዋል።

የአቃቂ ክ/ከተማ ዋና ሰራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ሜጀና በፕሮግራሙ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የደንብ መተላለፎችን ከመከላከል ጎን ለጎን የከተማውን ሰላምና ጸጥታ እያስጠበቀኔ በተለያዩ ሰው ተኳር የበጎ ፍቃድ ተግባር ላይ በመሰማራት እየሰራ ያለው ስራ ሊበረታታ የሚገባ መሆኑን ተናግረዋል ።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አበራ ኢቲቻ በበኩላቸው በበጀት ዓመቱ ከተያዙት እቅዶች ውስጥ በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ተግባራት መሳተፋ እንደሆነ ገልፀው በክ/ከተማው ወረዳ 12 የአመራሩ እና የኦፊሰሩ የጉልበት ወጪን ሳይካተት 1.5 ሚሊዮን ብር ለቤቶችን ወጪ በማድረግ ቤቶቹ መገንባታቸውን ገልጸዋል ።

አክለውም የበጎ ፈቃድ ተግባራት የብዙዎችን ህይወት እየቀየሩ እንደሚገኝና በቀጣይም ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በንግግራቸው የቤት እድሳቱን ላስጀመሩት የቀድሞ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ ከተማ የአሁኑ አዲስ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ደጀኔ ነገሮ እንዲሁም በግንባታ ወቅት ለተሳተፉ አካላት ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

ዘገባው ፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን
👍1
ማስታወቂያ
ግንቦት 14/2016 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አድራሻ ለማወቅ ከዛሬ ጀምሮ በየትኛውም የአለም ሀገራት ላይ በመሆን በጉግል ማፕ/Google Map/ በመጠቀም ማየት የሚቻል መሆኑን በደስታ እንገልፃለን።

የባለስልጣኑ አድራሻ በቀላሉ ሁሉም ሰው ማግኘት እንዲችል ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመግባት
1. rate፦ የሚለው ላይ 5ኛው የኮከብ ምልክት በመጫን፤
2. Comment፡- በሚለው ላይ ጠቃሚ መሆኑን ሀሳብ በመስጠት፤
3. Helpful:-የሚለው በመንካት ለሁሉም ማህበረሰብ እንዲደርስ በማድረግ የበኩሎን እንዲወጡ በአክብሮት እንጠይቃለን።

የደንብ መተላለፎችን በጋራ እንከላከል!
የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

https://maps.app.goo.gl/aUor5q24AvhbqLLN8
👍5
በሀገር አቀፍ ተነባቢ በሆነው አዲስ ዘመን ጋዜጣ በዛሬው እትሙ "በታሪካዊ ተቋም ታሪካዊ ስልጠና " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የተቋማችን ዓምድ እንድታነቡ በአክብሮት ተጋብዘዋል።

የደንብ መተላለፎችን በጋራ እንከላከል!

የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
👍156👏4
ባለስልጣኑ በደንብ ቁጥር 150/2015 ዙርያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ

26/09/2016ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ የደ/መ/መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት በደንብ ቁጥር 150/2015 ላይ ለእድር ምክር ቤት አመራሮች ፣ ለባለድርሻ አካላት እና በከተማው በየአካባቢው ለተወከሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መድረክ በአራዳ ክ/ከተማ መሰብሰቢያ አዳራሽ ሰጥቷል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከህብረተሰቡ ለተወጣጡ አካላት በደንብ ቁጥር 150/2015 በተመለከተ ግንዛቤ ለመፍጠር የተዘጋጀው ስልጠና በሰነድ በባለስልጣኑ በስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ እዬብ ከበደ ተሰጥቷል።

በሰነዱ የባለስልጣኑ አደረጃጀት፣ተጠሪነት እና ተግባር ኃላፊነት ፣ በህገወጥ ንብረት አያያዝ አሻሻጥና አወጋገድ ፣ ስለ አስተዳደራዊ ቅጣት እርምጃ አወሳሰድና አቤቱታ አቀራረብ ፣ የፖራ ሚሊተሪ ሰራተኞች ኦፊሰሮች ተግባርና ኃላፊነት ፣ የፖራ ሚሊተሪ ሰራተኞች ምልመላ ቅጥር ምደባ ዝውውርና ድልድል ፣ የፖራ የፖራሚሊተሪ ኦፊሰሮች ደመወዝና የሰራ ሰዓት ፣ የኦፊሰር ግዴታ እና ስነምግባር ፣ የዲስፕሊን እርምጃዎች የቅሬታ አቀራረብና አገልግሎት ሰለማቋረጥ እንዲሁም ልዩ ልዩ ድንጋጌዎችና የቅጣት ሰንጠረዦች በዝርዝር ተብራርቷል ።

በመጨረሻም ከሰልጣኞች ውይይት በማድረግ ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች በአሰልጣኙ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው ስልጠናው ተጠናቋል።

ዘገባው ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍4