የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.22K subscribers
2.3K photos
5 videos
1 file
56 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ከባለድርሻ ተቋመት ጋር የቅንጅት ተግባራት በማጠናከር ከተማችን ውብ፣ ጽዱና የደንብ መተላለፍ የቀነሰባት ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ

11/02/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ከባለድርሻ አካላት ጋር በ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በቅንጅት የተሰሩ ስራዎችን አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን በመከላከልና የህግ ማስከበር ስራን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመናበብ በመስራት በከተማችን የደንብ መተላለፍ 83% እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል ።

አክለውም ደንብ ማስከበር በከተማዋ አስተዳደር የተሰጠዎን ተልዕኮ ለመወጣት የቅንጅት ስራዎች ከፍተኛ ሚና ያላቸው እንደመሆኑ በጋራ የመስራት ባህልን በማጠናከር ከተማችን ውብ ጽዱ የደንብ መተላለፍ የቀነሰባት ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል ።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ደንብ መተላለፎችንና ህገ-ወጥነትን በመከላከል፣ ሰላምና ጸጥታ በማስጠበቅ ፣ የምሽት ንግድን በመደገፍ ፣ የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ብክለትን በመከላከል እንዲሁም የኮሪደር ልማቶች ደህንነት በመጠበቅ ከሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር ተቀናጅቶ በመስራቱ ውጤታማ ስራዎች መስራት መቻሉን በመድረኩ ተገልጸዋል ።

የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከባለድርሻ አካላት ጋር በ2018 ዓ.ም 1ኛ ሩብ ዓመት በቅንጅት የተሰሩ ስራዎች በጥንካሬ እና በጉድለት በሰነድ ተለይተው በባለስልጣኑ የስታንዳርዳይዜሽን ዝግጅት፣ አገልግሎት አሰጣጥና ድጋፍ ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ቀጸላ ቀርቧል ።

በሪፖርቱ ተቋሙ ከ20 ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር በቅንጅት ለመስራት በሰነድ በተፈራረመው ልክ ወደ ስራ በመግባት በጋራ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል ።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል ።

የመረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ነው፡፡
👍2