የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች አጠናክረን እንቀጥላለን" ሻምበል ኡባድ ጁና የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ
ሐምሌ 25 -2017ዓ/ም
አዲስ አበባ
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር አስተዳደር ጽ/ቤት የ2017 የ90 ቀናት እቅድ አካል የሆነው የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም ከየወረዳው የደንብ ማስከበር አመራሮችና ኦፊሰሮች በማስተባበር አካሂዷል ፡፡
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ሻምበል ኡባድ ጁና በጎነት ለራስ ነው በክረምቱ የበጎ ፈቃድ ተግባራችን አንዳችን ላንዳችን በመረዳዳትና በአብሮነት መኖራችን የምናሳይበት በመሆኑ በቀጣይ የአቅመ ደካማ ነዋሪዎች ቤት እንደሚያድሱ ገልጸዋል፡፡
ሻምበል ኡባድ ጁና ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የደንብ መተላለፎች ከመከላከልና ከመቆጣጠር በተጨማሪ አመራሩና ኦፊሰሩ በራሱ ካለዉ ላይ አዋጥቶ የሚሰጥም ጭምር መሆኑን ተናግረዋል ።
በዝግጅቱ የተገኙት ኦፊሰሮች በበኩላቸው ማዕድ ማጋራታችን አቅመ ደካማና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ በቀጣይም በሚችሉት እንደሚያግዙ ተናግረዋል፡፡

❤3
ፕሬስ ሪሊዝ
ባለስልጣኑ የ2017 በጀት አመት የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም ሊያካሄድ መሆኑ ተገለፀ
28/11/ 2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የ2017 በጀት አመት የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም ከአስር ሺ በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት በቀን 29/11/2017 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ እንደሚያካሄድ ተገለፀ፡፡
በፕሮግራሙ የፌደራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ኃላፊዎች ፣ የባለሥልጣኑ ከፍተኛ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ፣ የክ/ከተሞችና የወረዳዎች ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣ መላው የፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች፣ የማህበረሰብ አንቂዎች፣የህብረተሰብ ተወካዬች ፣ የሀይማኖት አባቶችና የሲቪክ ማህበራት ተወካዪች ይገኛሉ ።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

👍11❤6
በሁለት የደንብ ማስከበር አባላትን ላይ የድብደባ ወንጀል የፈጸሙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ
ሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ/ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ በማስከበር ተግባራቸውን በመወጣት ላይ በነበሩ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አባላት ላይ የድብደባ ወንጀል የፈጸሙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተካሄደ መሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገለፀ።
ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ/ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው ጀሞ መስታወት ፋብሪካ አካባቢ ሲሆን ተከሳሾች ዮሀንስ ከበደ፣ ሠዒድ ሠይፉ፣ እስማኤል ሱልጣን፣ ሃይረዲን ሽፋ፣ ፈጅሩ ሱልጣን፣ ባህሩ ራህመቶ፣ ሚነወር ሀይሉ፣ ሀይልዬ ጀማልና አስማረ አለሙ የተባሉ እና ሌሎች ያልተያዙ ሁለት ተጠርጣሪዎች መኖራቸው ተጠቁሟል።
ተጠርጣሪዎቹ በእግረኛ መንገድ ላይ ህገ ወጥ የጎዳና ላይ ንግድ በማከናወን ላይ እያሉ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አባላት የሆኑት ማቱሳላ ማዶሬና አቡሽ ሽጉጤ ድርጊቱን ለመከላከል ሙከራ በሚያደርጉበት ወቅት ተጠርጣሪዎቹ አባሪ ተባባሪ በመሆን አባላቱን በድንጋይና በእርግጫ ተረባርበው የድብደባ ወንጀል መፈጸማቸውን ፖሊስ አስታውቋል።
ተጠርጣሪዎቹ በወቅቱ ድርጊቱን ፈጽመው ቢሰወሩም በክ/ከተማው ፖሊስ በተደረገ ክትትል በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን ፖሊስ ገልጾ በፈጸሙት የወንጀል ድርጊትም ተገቢውን ምርመራ የማጣራትና ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረቱን መቀጠሉንም ገልጿል።
በጎዳና ላይ የሚደረጉ ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች የእግረኛና የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ በማወክ ዜጎችን ለመንገድ ትራፊክ አደጋ ተጋላጭ ከማድረጉም ባሻገር ጤናማ የንግድ እንቅስቃሴን የሚጎዳ መሆኑ እየታወቀ ይህንንም ድርጊት ለመከላከል የተሠማሩ የጸጥታ አካላት ላይ ትንኮሳ መፈጸምና ለህግ ተገዢ ያለመሆን ተጠያቂነትን የሚያስከትል ድርጊት መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።

👍10❤3
ባለስልጣኑ የ2017 በጀት አመት አፈፃፀም የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም አካሄደ
29/11/ 2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ኃላፊዎች የክ/ከተሞችና የወረዳ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣አጠቃላይ የፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች፣ የህብረተሰብ ተወካዮች በተገኙበት በሚሊኒየም አዳራሽ የ2017 በጀት አመት የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም አካሄደ፡፡
በመዶረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጁ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በበጀት አመቱ ከ27 ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር በመዘረጋት፣ ለህብረተሰቡ የደንብ ስርፀት ስራ በመስራት ፣የኮሪደር ልማት በመጠበቅና የወንዝ ዳርቻ ልማትን በማጠናከር በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰዋል።
በበጀት አመቱ ከአስተዳደራዊ ቅጣት አራት መቶ አራት ሚሊየን ብር በመቅጣት እርምጃ የተወሰደ ሲሆን የደንብ ጥሰት በ69.8 ፐርሰንት መቀነሱን በመግለፅ የከተማ አስተዳደሩም ለባለስልጣኑ የሰጠው እውቅናና ሽልማት ለቀጣይ ስረሠ ብርታት እና ተወዳዳሪነት እንደሚፈጥር ተናግረዋል።
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ሰለምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወሮ ሊዲያ ግርማ ባለስልጣኑ የደንብ ጥሰትን በመከላከልና በመቆጣጠር ከተማዋ በስርዓት እድትመራ በማድረግ ፣ በከተማ አስተዳደሩ የሚወጡ ደንቦችን በማስተግበር፣ ጠንካራ ስራዎችን ማከናወኑ ጠቁመዋል።
ይህንን ውጤት በቀጣይ በጀት አመትም በቁርጠኝነት በማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።
በእውቅናና ሽልማት መድረኩ ተሸላሚ የሆኑ ክፍለ ከተሞች
1ኛ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ
2ኛ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ
3ኛ ቦሌ ክፍለ ከተማ ሲሆኑ ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች፣ አንደኛ ለወጡ 11 ወረዳዎችና ኦፊሰሮች ሽልማትና እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በሽልማቱ ከአንድ እስከ 3ተኛ ደረጃ ላገኙ ክፍለ ከተሞች እና ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች አንደኛ ለወጡ 11 ወረዳዎች የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል፣ ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች አንደኛ ለወጡ ከ11ኦፊሰሮች ሰርተፍኬትና የ5 ሺህ ብር ቦንድ እንዲሁም ለማዕከል ዳይሬክቶሬቶች፣ ቡድኖች እና ፈፃሚዎች የዋንጫ ሰርተፍኬትና የ5ሺህ ብር ቦንድ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

❤1