የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች አጠናክረን እንቀጥላለን" ሻምበል ኡባድ ጁና የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ
ሐምሌ 25 -2017ዓ/ም
አዲስ አበባ
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር አስተዳደር ጽ/ቤት የ2017 የ90 ቀናት እቅድ አካል የሆነው የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም ከየወረዳው የደንብ ማስከበር አመራሮችና ኦፊሰሮች በማስተባበር አካሂዷል ፡፡
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ሻምበል ኡባድ ጁና በጎነት ለራስ ነው በክረምቱ የበጎ ፈቃድ ተግባራችን አንዳችን ላንዳችን በመረዳዳትና በአብሮነት መኖራችን የምናሳይበት በመሆኑ በቀጣይ የአቅመ ደካማ ነዋሪዎች ቤት እንደሚያድሱ ገልጸዋል፡፡
ሻምበል ኡባድ ጁና ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የደንብ መተላለፎች ከመከላከልና ከመቆጣጠር በተጨማሪ አመራሩና ኦፊሰሩ በራሱ ካለዉ ላይ አዋጥቶ የሚሰጥም ጭምር መሆኑን ተናግረዋል ።
በዝግጅቱ የተገኙት ኦፊሰሮች በበኩላቸው ማዕድ ማጋራታችን አቅመ ደካማና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ በቀጣይም በሚችሉት እንደሚያግዙ ተናግረዋል፡፡

❤3