የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.12K subscribers
1.87K photos
4 videos
1 file
54 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ በተግባቦት ፣ በመረጃ አያያዝ እና የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም በተመለከተ ስልጠና ሰጠ ።

መጋቢት 12/ 2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በክፍለ ከተማ እና በወረዳ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤቶች በኮሙኒኬሽን እና ሶሻል ሚዲያ ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች በተግባቦት ፣በመረጃ አያያዝ እና በሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ እንደተናገሩት ባለስልጣኑ ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ የሚዲያ አግባቦችን በመጠቀም ላይ ይገኛል ይህንንም ስራ በጋራ ለማሳለጥ ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ ድረስ የመረጃ ቅብብሎሹን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

ሀላፊው አያይዘው የተቋሙን ገጽታ በመገንባት ለደንብ ማስከበር ስራ ህብረተሰቡ አዎንታዊ አመለካከት እንዲኖረው እና ህገ-ወጥነትን የሚኮንን ዜጋን ለማፍራት ተግባቦት እና ሚዲያ ሚናው ከፍተኛ ስለሆነ ስልጠናው እንደሚያግዝ ገልፀው በቀጣይ የተሰጠውን ስልጠና ተግባራዊ በማድረግ ከሰልጣኞች እና ሁሉም የተቋሙ ባለሙያዎች በተቋሙ ገጽታ ግንባታ ስራው የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል ።

በተግባቦት፣በመረጃ አያያዝ እና የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ላይ የተዘጋጀው ስልጠና በባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ የምስራች ግርማ የተቋሙን ተግባራት ማዕከል ባደረገ መልኩ ሰጥተዋል።

የስልጠናው ዓላማ በተቋሙ የሚሰሩ ስራዎችን ለማህበረሰቡ ለማስተዋወቅ ፣ሶሻል ሚድያ በመጠቀም የተቋሙ የመረጃ ልውውጥ ተደራሽ ለማድረግና ተቋሙ በየጊዜው የሚከፈትበትን የሶሻል ሚድያ ስም ማጥፋት ዘመቻ ሰራተኛው ትግል በማድረግ ትክክለኛውና የተደራጀ መረጃ ለህብረተሰቡ እንዲሰጥ ለማስቻል መሆኑ ተገልጿል ።

የሚዲያ አካላትን በአግባቡ ከተጠቀምንባቸው የተቋምና የሀገር ገጽታ ከመገንባት ባለፈ ለሀገራችን ሰላም ከፍተኛ ሚና ያለው ሲሆን ያለአግባብ ከተጠቀምንበት ከፍተኛ ጉዳት የሚያመጣ መሆኑን በመገንዘብ ማህበራዊ ሚዲያን ለመልካም ተግባርና ለሀገር ግንባታ ልንጠቀምበት እንደሚገባ በስልጠናው ተገልጿል።

በመጨረሻም ከሰልጣኞች ጋር በቀጣይ በጋራ በተቀናጀና በተናበበ ሁኔታ ለመስራት ውይይት በማድረግ ከሰልጣኞች ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች በባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ የምሰራች ግርማ እና የሬ/ቴ/ህ/ዝግጅት ቡድን መሪ በአቶ ሄኖክ ታደሰ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል ።

ዘገበው ፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፦
የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ፎሎው፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
የፌስ ቡክ ገፃችን፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082525711518&mibextid
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/codeenforcement
የዩቱብ ቻናላችን
https://youtube.com/@A.A.C.ACODEENFORCEMENT
የቲክቶክ አካውንታችን
https://www.tiktok.com/@addisababacodeenforcemen
የትዊተር/X/ ሚዲያ ገፃችን
https://x.com/Addis_Denb?t=u8wW3qnxWk48GYzJ4RD96Q&s=09
ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ!
👍2
ኘረስ ሪሊዝ

ባለስልጣኑ በ2016 ዓ.ም በመጀመሪያው ስድስት ወራት የላቀ የእቅድ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አካላት ዕውቅና ሊሰጥ ነው።

መጋቢት 20/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2016 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የላቀ እቅድ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ለማዕከል ዳይሬክቶሬቶችና ቡድኖች እንዲሁም ለክፍለ ከተማና ለወረዳ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤቶች እውቅና በመስጠት የማበረታቻ ሽልማትና የምስክር ወረቀት ሊያበረክት መሆኑ ተገልጿል።

እውቅናው በነገው እለት ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በጌት ፋም ሆቴል የከተማውና የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላው እንግዶች በተገኙበት በእቅዳቸው መሠረት ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ አካላት እውቅናው እንደሚሰጥ የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ ጠቁመዋል።

መረጃው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍6