የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.75K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ የወርቃማ ሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ-ግብር አከናወነ

02-10 -2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሰኞ ማለዳ ከስራ ገበታ በፊት የሚያካሂደው የእውቀት ሽግግር ፕሮግራም የባለስልጣኑ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት አካሄደ፡፡

የመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ለስድስተኛ ዙር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ምርቃት ፕሮግራም በደመቀ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ከስልጠናው ሂደት ጀምሮ እስከ ምርቃት ፕሮግራም መሳካት የበከሉላቸውን ላበረከቱ አካላትና ለመላው የደንብ ማስከበር ሰራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

የወርቃማ ሰኞ መድረክ ሳምንቱን ንቁ ሆነን ዉጤታማ ስራ ለማከናወንና በየሳምንቱ ከሰራተኞቻችን ጋር እንደቤተሰብ እየተማማርን መልካም ምኞት በመለዋወጥ እርስ በእርሳችን ምንማማርበት፣ ልምድ የምንለዋወጥበት መሆኑን ገልጸዋል ።

በዕለቱ የባለስልጣኑ የኢንስፔክሽን እና ቁጥጥር ባለሙያ አቶ አባትነህ ውባለም የራሳቸውን የህይወት፣ የትምህርት እና የስራ ተሞክሮና ልምዳቸውን ለሌሎች አስተማሪ በሆነ መልኩ አጋርተዋል።

በተጨማሪም የተቋም ግንባታ ምንነት በሚል ርዕስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ በማቅረብ እውቀት አጋርተዋል ።

ውጤታማ የተቋም ግንባታ የረጅም ጊዜ ስኬትን ለማስመዝገብ፣ አዎንታዊ ግንኙነትን ለመፍጠር እና ለሰራተኞችም ሆነ ለማህበረሰቡ የበለጸገ አከባቢ ለመፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አቶ አባትነህ አስረድተዋል ።

መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍74
ብልሹ አሰራርን ለመታገል የተባባሪ አካላት ሚና ጉልህ መሆኑ ተገለጸ

05-10 -2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ከአስራ አንዱም ክ/ከተማ እና ከ119 ወረዳ ብልሹ አሰራርን ለመታገል ለተመለመሉ ተባባሪ አካላት "ብልሹ አሰራርን በጋራ ለመታገል የተባባሪ አካላት ሚና" በሚል መሪ ቃል የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዋጅና በመመሪያ የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ ከስነ-ምግባር ጉደለትና ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ እንዲያከናውን የተባባሪ አካላት ሚናቸው የላቀ በመሆኑ ገልጸዋል ።

አክለውም የተቋሙ ሰራተኛና ኦፊሰሩ በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰትን ፣ የኮሪደር ልማቶችን ደህንነት በመጠበቅና የወንዝ ዳር ብክለትን በመከላከልና በመቆጣጠር ሂደት ራሱን ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል ።

የስነምግባር ችግር እና ብልሹ አሰራርን ለመታገል የተዘጋጀው የስልጠና ሰነድ በባለስልጣኑ የስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ እዬብ ከበደ ቀርቧል።

በሰነዱ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አሁናዊ ያለበት ሁኔታ ፣ ብልሹ አሰራርን ከመታገል አንጻር የተባባሪዎች አካላት ሚና እንዲሁም የስነ-ምግባርና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል መከናወን ያለባቸው ተግባራት በዝርዝር ቀርበዋል።

ተቋማችን ከብልሹ አሰራርና ከስነ ምግባር ጉድለት በጻዳ መልኩ ሰራዎችን ለማከናወንና አንዳንድ ችግር የሚታይባቸውን አካላት ተጠያቂ ለማድረግ የተባባሪ አካላት ሚና ጉልህ እንደመሆኑ ወጥ በሆነ ሁኔታ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አቶ እዬብ አስገንዝበዋል ።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶ መድረኩ ተጠናቋል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
2👍1
ባለስልጣኑ በደንብ ቁጥር 167/2017 እና በዲሲፕሊን መመሪያ ቁጥር 31/2015 ዙርያ ስልጠና ሰጠ

ግንቦት 5/2017 ዓ.ም
አዲሰ አበባ

የኢዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ዙርያ ፣በደንብ ቁጥር 167/2017 በተደነገጉ አስተዳደራዊ ቅጣቶች እና የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የዲሲፕሊን መመሪያ ቁጥር 31/2015 ላይ ስልጠና ሰጠ።

ስልጠናውን ያስጀመሩት የባለሰልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የስልጠናና ቅድመ መከለከል ዘርፍ ኃላፊ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በበጀት አመቱ ከከተማው ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ጋር በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ዙርያ በርካታ ውጤታማ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን ገልፀዋል።

አያይዘውም በደረቅቅ ቆሻሻ አወጋገድ እና በደንብ 167/2017 ዙርያ የሚሰጠው ስልጠና በጋራ ለሚሰሩ ስራዎች አቅም የሚፈጥር በመሆኑ ግንዛቤውን ወስዶ ለማህበረሰቡ ማድረስ እንደሚገባ አሳስበዋል ።

ከአዲስ አበባ ከተማ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ የግንዛቤና ስርፀት ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ዳዊት ተክሉ ስለ ድርቅ ቆሻሻ ምንነት ፣ምንጮቹ ፣ አይነቶች፣ አወጋገድ፣ የደረቅ ቆሻሻ እርከኖች እና ደረቅ ቆሻሻን መልሶ ለመጠቀም ሀገራት ያሉበትን ደረጃ በተመለከተ ግንዛቤ ፈጥረዋል።

በደንብ ቁጥር 167/2017 ዙርያ ባሉት 36 የቅጣት እርከኖች ከግለሰብ እሰከ ድርጅት በሎም ቆሻሻውን ከሚያነሱ አደረጃጀቶችን ጨምሮ ለሚያጠፋት ጥፋት የሚጣሉትን አስተዳዳራዊ ቅጣቶች እስከ አንድ መቶ ሺህ ብር ድረስ እንደሚያስቀጣ አቶ ዳዊት ገልፀዋል።

በመድረኩ የዲሲፕሊን መመሪያ ቁጥር 31/2015 ዙርያ የተዘጋጀ ስልጠና የባለስልጣኑ የህግ አገልግሎት ቡድን መሪ በአቶ ብርሃኑ ኮርሣ አማካኝነት ተሰጥቷል ።

በግንዛቤው ስለ ቀላላና ከባድ የዲሲፕሊን ቅጣቶች፣ሰለ ዲስፕሊን ጥፋት አይነቶች አመዳደብ፣ ሰለ ዲሲፕሊን ክስ አመሰራረት ፣ሰለ ውሳኔ አሰጣጥ እና በቅሬታ አቀራረብ ዙርያ በስፋት በመዳሰስ ስልጠና ተሰጥቷል።

ስልጠናው በማዕከል እና በክ/ከተማ ደረጃ ለሚገኙ ዳይሬክተሮች ፣ ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን በእለቱ የተለያዩ አስተያየት እና አግባብ ያላቸው ጥያቄዎች ተነስተው በአሰልጣኞቹ ምላሽ ተሰጥቶባቸው ስልጠናው ተጠናቋል።

ዘገባው፦ የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
ባለስልጣኑ የቀጣይ 90 ቀናት እቅድ ከጠቅላላ ፕሮሰስ ካውንስል አባላት ጋር ውይይት አካሄደ

06/10/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የቀጣይ 90 ቀናት ዕቅድ በተመለከተ የባለስልጣኑ ከጠቅላላ ፕሮሰስ ካውንስል አባላት ጋር ውይይት አካሄደ።

በመድረኩ የባለሥልጣኑ ዋና-ስራ አስኪያጅ ከ2017 በጀት አመት ልምድ በመውሰድ የቀጣይ 90 ቀናት እቅድ መፈጸምና የማስፈፀም አቅምን በማጎልበት እቅዱ ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት አቅጣጫ ሰጥተዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የ 90 ቀናት ዕቅድ በባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ በአቶ ንጋተ ዳኛቸው ቀርቧል ።

በእቅዱ መደበኛ የተቋሙ ስራዎችና ሰው ተኮር ተግባራት ከማዕከል እስከ ወረዳ በተሰኩረት እንደሚከናወኑ በሰነዱ ተመላክቷል።

በተዘጋጀው እቅድ ላይ ሰፊ ውይይቱ የተደረገ ሲሆን በእቅዱ ላይ የተነሱ ጠቃሚ ሀሳቦች በማካተት መሠራተሰ እንዳለበት ተገልጿል ።

መረጃው፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍104