የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.75K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
የህዝብና የመንግስት መሬት በመውረር ግንባታ የገነባ ባለሀብት በቁጥጥር ስር በማዋል በግንባታው እርምጃ ተወሰደ

ግንቦት 27/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማሰከበር ባለስልጣን ‎በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በወረዳ 06 በ125 ካሬ መሬት ወረራ ያከናወነን ግለሰብ በቁጥጥር ስር በማዋል በአዋጅ 721/2004 መሰረት ተጠያቂ በማድረግ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ መደረጉ ተገለፀ። የወረዳዉ ደንብ ጽህፈት ቤት ሀላፈ አስታዉቋል።

‎በግለሰቡ የደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ከወረዳው ሰላምና ፀጥታ ጽህፈት ቤት ፣ ከወረዳዉ መሬት አስተዳደር ጽህፈት ቤት እንዲሁም ከፖሊስ ጋር በመተባበር በተገነባው ግንባታ ላይ እርምጃ የተወሰደ መሆኑን የደንብ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ኢ/ር ደሳለኝ ሌንጮ ገልፀዋል።

ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ የመንግስትና የህዝብ መሬት በህገ-ወጥ መንገድ በመውረር በበሚገነባ ግንባታ የህዝብና የመንግስት ሀብት ከብክነት እንዲጠብቁ መልዕክቱን አስተላልፏል።
👍104👎2
ለኢትዮጵያ ብልፅግና የመንግስት ሰራተኛው ተሳትፎ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ

28/9/2017
**የአዲ ስአበባ**

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን "ብቃት ያለው ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል በከተማ ደረጃ እየተካሄደ ያለውን ስልጠና ከማዕከል አመራርና ሰራተኞች ጋር ውይይት አደረገ።

የባለስልጣኑ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው መንግስት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ላይ መሆኑን ጠቅሰው፤ ውይይቶቹ መንግስትና ህዝብን ለማቀራረብ አስፈላጊ በመሆናቸውና ከውይይት የሚጨመቁ ሀሳቦች ፓሊሲዎችን ስትራቴጂዎች ሊቀይሩ እንደሚችሉ ገልፀዋል።

የመወያያ ሰነዱ በይዘት ሀገራዊ ለውጥ ያስመዘገባቸው ውጤቶችና የሲቪል ሰርቫንቱ ሚና፣ የሲቪል ሰርቪስ አሁናዊ ሀኔታ፣ የአመራር ሁኔታ፣ የመንግስት ሰራተኛ ሁኔታ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የሲቪል ሰርቫንት ሪፎርም እና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ የመሳሰሉትን ዋና ዋና ይዘቶች ለማየት ተችሏል።

በሰነዱ በአዲስ አበባ ውስጥ ከ70ሺህ በላይ የመንግስት ሰራተኞች ሲኖሩ እነዚህ ሰራተኞች አሁን ላለው ለውጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን በተለይም በትምህርት ፣ በጤና ፣ በአረንጓዴ አሻራ ፣ በኮሪደር ልማት በመሳሰሉት ከተማ አቀፍ ስራዎች ሚናቸው ጉልህ መሆኑ ተገልጿል።

በውይይቱ የኑሮ ውድነት ላይ ስርነቀል ስራ መሰራት እንደሚገባ ፣ገበያ ማረጋጋት ምርቶችን ቀጥታ ከገበሬው የሚያገኝበት መንገዶች ቢመቻች፣ የቤት አቅርቦት ለመንግስት ሰራተኛው ቢታሰብበት፣ የትምህርት እድሎች ሰፋ ባለ መልኩ ቢዘጋጅ እና የሰራተኞች የፐብሊክ ትራንስፖርት እጥረት የመሳሰሉት ጉዳዮች በውይይቱ ተነስተዋል።

የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ ሰራተኛው ከብልሹ አሰራር ችግር በመውጣት ህብረተሰብን ወጥ በሆነ መንገድ ማገልገል እንደሚገባ አና ለመንግሥት ሰራተኛውም ምቹ ሁኔታዎች ሊፈጠረለት እንደሚገባ በሰጡት የማጠቃለያ ሀሳብ ገልጸዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ከተማዋን በማዘመን ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየሠራ እንደሚገኝና ከላይ የተነሱ ጥያቄዎችን በየደረጃው ለመፍታት ሰፊ እርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በማጠቃለያ ንግግራቸው ላይ አመላክተዋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
5