የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.1K subscribers
1.79K photos
4 videos
1 file
53 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ሕብረተሰቡን በታማኝነት ማገልገል እንደሚገባ ተገለፀ።

22/09/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአቃቂ ቃሊቲ፣ ኮልፌ ቀራኒዮና ንፋስ ስልክ ላፍቶና አራዳ ክፍለ ከተማ አመራርና ኦፊሰሮች ጋር በስነምግባር ችግር እና ብልሹ አሰራርን ለመታገል የተመለከተ ግምገማዊ ስልጠና መድረክ አካሄደ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራና ዘርፍ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

"የስነምግባር ችግር እና ብልሹ አሰራርን ለመታገል የኦፊሰሩ ሚና" በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን የስልጠና ሰነድ በባለስልጣኑ የስነምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዬብ ከበደ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።

ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት በሁሉም ረገድ እየዘመነች ያለች ከተማን ደንብ መተላለፍ በአግባቡ ለመከላከል እና ህብረተሰቡን በታማኝነት ለማገልገል ከፍተኛ ቁርጠኝነት የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሌም በስነ-ልቦና ዝግጁ በመሆን ተልዕኳችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።

በቅርቡ አስመርቀን ወደ ስራ የምናሰማራቸውን የ6ተኛ ዙር ኦፊሰሮቻችንን ጨምረን የሰው ኃይል አቅማችንን የበለጠ በማጠናከር ሕገ-ወጥነትንና የደንብ መተላለፍን በአስተማማኝ መልኩ የምንከላከል ይሆናል ብለዋል።

ሁሉም ኦፊሰር በተመደበበት ቀጠና ላይ በሰዓቱ በመገኝት ከስነ-ምግባርና ብልሹ አሠራር በፀዳ መልኩ ተልእኮውን እንዲወጣ አሳስበዋል።

በትላንትናው ዕለት ከተቀሩት ክፍለ ከተማ ኦፊሰሮችና አመራሮች ጋር ውጤታማ ውይይት መካሄዱ ይታወሳል።

መረጃው ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
2👍1
ባለስልጣኑ ለ3 ቀናት ሲሰጥ የቆየውን የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ

22/09 /2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ለማዕከል እና ለክፍለ ከተማ ሲቪለሸ ሠራተኞች በአንደኛና በሁለተኛ ዙር በአጠቃላይ ለ3 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየውን የአቅም ግንባታ ስልጠና አጠናቀቀ።

ስልጠናው በአሰልጣኝ ቢንያም አብረኃ በጊዜ አጠቃቀም፣ ውጤታማ የቡድን ትብብር ችሎታ እና የራስ ተነሳሺነት፣ እራስን ማስተዳደር እና ሌሎች ርዕሶች ላይ በምዘና የታጀበ ውጤታማ ስልጠና ተሰጥቷል።

በስልጠናውም ላይ ተሳታፊዎቹ የሰጡት አስተያየት በእውቀት፣ በአመለካከትና በክህሎታችን ላይ ስር ነቀል የሆነ ለውጥ የሚያመጣ እና ያገኘነው ስልጠናም በፈተና ጭምር የተረጋገጠ በመሆኑ ውጤታማ ነበር ሲሉ ተደምጠዋል።

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የባለስልጣኑ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊና ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ተገኝተዋል።

አቶ ንጋቱ እንዳሉት ተቋሙ ከፍተኛ በጀት በመመደብ የአቅም ግንባታ ስራ ላይ እየሠራ እንደሚገኝና በእውቀት በአስተሳሰብና ክህሎት የበቃ ባለሙያ ለተቋም ለውጥ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ በቀጣይም መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

ሰልጣኞችም ተቋሙ ከፍተኛ ትኩረት በማድረግ ያቀረበውን ስልጠና ወደ ተግባር በመለወጥ በአፈፃፀማችን ላይ የሚታይ ተጨባጭ ለውጥ በማስመዝገብ ለህብረተሰባችን የተሻለ አገልግሎት ልንሰጥ ይገባል ብለዋል።

በዚህ ቴክኖሎጂ በዘመነበት ክፍለ ዘመን ላይ እንደመገኘታች መጠን በተለያዩ የኦን ላይን ኮሮሶች ጭምር እራሳችንን በማብቃት በሁሉም ዘርፍ ተወዳዳሪና ብቁ ባለሙያ ልንሆን ይገባል፤ በማለት መልክታቸውን አስተላልፈዋል።

መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍3