የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.75K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ሲሰጥ የቆየው የ6ኛ ዙር ፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮች የአሰልጣኞች ስልጠና አጠናቀቀ።


11/07/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቀጣይ ለሚሰጠው 6ኛ ዙር የፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና የባለድርሻ አካላት ደንብ፣ መመሪያና አሠራርን የተመለከቱ ንድፈ ሀሳቦች ላይ ሲሰጥ የቆየው የአሠልጣኞች ስልጠና በዛሬው እለት አጠናቋል።

ባለስልጣኑ ከግንባታ ፍቃድ፣ መሬት አስተዳደር ፣ ከተማ ግብርና፣ ቄራዎች ድርጅት፣ አከባቢ ጥበቃ፣ ውኃና ፍሳሽ፣ ፅዳት አስተዳደር፣ ትራፊክ ማናጅመንት፣ ንግድ ቢሮ፣ ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን እና የገቢ ደረሰኞች የውስጥ ቁጥጥር ኦዲት ጋር በጋራ በመሆን ከማዕከል እና ከአስራ አንዱም ክ/ከተማ ለተውጣጡ ሰልጣኞች በማዕከሉ አዳራሽ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ስልጠናውን ሲሰጥ ቆይቷል።

የስልጠናና ጥናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ላቀች ኃይሌ እንደተናገሩት ሰልጣኞች የስልጠናውን ዓላማ በመረዳት ያገኙትን እውቀት የተሻለ አፈጻጸም እና ትግበራ ላይ እንዲውል ለማስቻል በቀጣይ በሚሰጡት ስልጠና ላይ አጽኖት በመስጠት እና በማስገንዘብ ሀላፊነት መወጣት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ለተከታታይ ሶስት ቀናት ሲሰጥ በቆየው ስልጠና ላይ ባለድርሻ ተቋማቱ በነባር እና በተሻሻሉ ደንብ ፣ መመሪያዎች እና አሰራሮቻቸው ላይ ከደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ጋር በመሆን በቀጣይ ከህግ አንጻር በቅንጅት እንሰራበታለን ባሏቸው ነጥቦች ላይ ሰነዶችን አቅርበዋል።

በስልጠናው ሂደት ላይ ከሰልጣኝ ኦፊሰሮች ሊነሱ ይችላሉ ባሏቸው ነጥቦች እና አጠቃላይ በነበሩ ቀናት ባይዋቸው ሰነዶች ላይ ከቤቱ ጥያቄዎች በማንሳት ከተቋማቱ በመጡ ተወካዮች ከመድረክ ምላሸ በመስጠት የጋራ ተደርጓል።

በመድረኩ ማጠቃለያ የሰጡት የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ እና የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የስልጠናውን ዓላማ በመረዳት ለቀጣይ በማንኛውም የስራ ተልዕኮ እና መደበኛ ስራ ዘላቂነት የበኩላቹን ድርሻ መወጣት እንደሚገባም በማሳሰብ ሰልጣኞች በዲስፕሊንና በመልካም ተሳትፎ ስልጠናውን ስለተከታተሉ በማመስገን በቀጣይ የበለጠ ለቅንጅታዊ አሰራር ትኩረት ተሰጥቶ መስራት እንደሚገባ እና ሰለጣኞችንም በሚፈለገው ልክ ብቁ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ዘገባው:- የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
👍41👎1
ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን 4,289,000/ አራት ሚሊየን ሁለት መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ሺህ/ ብር መቅጣቱ አስታወቀ

11/07/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በዛሬው እለትም በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት በድምሩ 4,289,000/ አራት ሚሊየን ሁለት መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ሺህ/ ብር የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ 1,315,000 ብር፤ በአቃቂ ክ/ከተማ 800,000 ብር ፤በየካ ክፍለ ከተማ 600,000
ብር፤በቦሌ ክፍለ ከተማ 600,000 ብር፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ 500,000
ብር ቅጣት ተቀጥቷል።

በተያያዘ ዜና በጉለሌ ክፍለ ከተማ 254,000 ብር ፤በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ
170,000 ብር እና በኮልፌ ክፍለ ከተማ 50,000 ብር ቅጣት በመቅጣት ለመንግስት ገቢ ተደርጓል፡፡

ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በአጠቃላይ 14 ድርጅቶች እና 22 ግለሰቦች በድምሩ 4,289,000/ አራት ሚሊየን ሁለት መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ሺህ/ብር ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል።

ባለስልጣኑ ወንወዞችና የወንዞች ዳርቻ እንዳይበከሉ ለድርጅቶችና ለግለሰቦች በደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ሰፊ የግንዛቤ ስራ መስራቱ የገለጸ ሲሆን ህግ የማስከበሩ ስራ አጠናክሮ አንደሚቀጥል አስታውቋል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍122
ሕብረተሰቡ የተቋሙን ስም ለማጠልሸት የሚንቀሳቀሱ ህገ-ወጦችን እንዲያወግዝ ጥሪ ቀረበ

12/07/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ተልኮ ለማስፈፀም ከሌሎች ባለድርሻ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ተጨባጭ የሆነ ለውጥን በማስመዝገብ ላይ ይገኛል፡፡

ባለስልጣኑ ለህብረተሰቡ ጥቅም ሲባል የሚወጡ ደንቦችን አስቀድሞ ግንዛቤ እያስጨበጠ፤ ሆን ብሎ ደንቡን ተላልፎ በሚገኝ ማንኛውም አካል ላይ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን በመውሰድ የደንብ መተላለፍን በመከላከል ላይ ይገኛል፡፡

በዛሬውም ዕለት የተቋሙ ያልሆነ የደንብ ልብስ በመልበስ የሱቅ ማስታወቂያ ሰርተው በማህበራዊ ሚዲያ ያሰራጩ ተጠርጣሪ ግለሰቦችን የአዲስ አበባ ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ በማድረግ ተጨማሪ ምርመራ እያካሄደ በመሆኑ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ታላቅ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡

ሆኖም ተጠርጣሪዎቹ የለበሱት ዩኒፎርም የቀድሞውንም ሆነ የአሁኑን የተቋሙን የደንብ ልብስና ሎጎ የማይወክል መሆኑን ባለስልጣኑ ያስታውቃል፡፡

ህብረተሰቡም ማንኛውም የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ደንብ አስከባሪ የሆነ ኦፊሰር የተቋሙን ሎጎ ያለበት ዪኒፎርም በመልበስ ደንብ የሚያስከብር መሆኑን በመገንዘብ ህገ ወጥ ግለሰቦች ከሚያደርጉት ማጭበርበር እራሱን እንዲጠብቅ መልዕክት አስተላልፏል።

ባለስልጣኑ ሕብረተሰቡ የተቋሙን ስም ለማጠልሸት የሚንቀሳቀሱ ህገ-ወጦችን እንዲያወግዝ ጥሪ የቀረበ ሲሆን ማንኛውም የሚያጠራጥር ጉዳይ ሲያጋጥመው በ9995 ነፃ የስልክ መስመር እና በክፍለ ከተማና ወረዳ በሚገኝ መዋቅር የደንብ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
👍5
ስነምግባር በተላበሰ መልኩ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ተገለፀ

12/07/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ለአራዳ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች "ስነ-ምግባርና መልካም አስተዳደር ለተሻለ አገልግሎት አሰጣጥ" በሚል መሪ ቃል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በክ/ከተማው አዳራሽ ሰጠ።

ስልጠናውን የሰጡት የባለስልጣኑ የስነምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዬብ ከበደ የስነምግባርና ብልሹ አሰራር ችግር ለተቋማችን ገጽታ ግንባታ ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ በመገንዘብ በዚህ ድርጊት በሚሳተፉ ላይ ጠንካራ የተጠያቂነት ስርዓት በመዘርጋትና በመከላከል ሁሉም አካል ብልሹ አሰራርን ሊጸየፍና ሊታገል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ስነ-ምግባር ለመልካም አስተዳደር መስፈን ያለዉ ፋይዳ የላቀ በመሆኑ ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ለሌሎች አርኣያ የሚሆን ስነ ምግባር በተላበሰ መልኩ አገልግሎቶችን መስጠት እንደሚጠበቅባቸው አቶ እዮብ ገልጸዋል ።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የአራዳ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ ሻምበል ኑርልኝ ገ/ኪዳን ኦፊሰሩ ከብልሹ አሠራር እራሱን በመጠበቅ የተሰጠዉን ተልዕኮ በአግባቡ መወጣትና ከዳር ማድረስ እንዳለበት ገልጸዋል።

በመድረኩም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበታል።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍12