የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.79K photos
4 videos
1 file
53 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ የመሬት ባንክ የገባ መሬት በመውረር በተገነባ ግንባታ ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ

የካቲት 30/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 2 መሬት ባንክ ገብቶ ሲጠበቅ የነበረ 1000 ካ.ሜ. የህዝብና የመንግስትን መሬት በህገወጥ መንገድ ሁለት ግለሰቦች የ2012 ዓ.ም ካርታ አለን በማለትና ከወረዳው የግንባታ ፍቃድ በማውጣት ቦታውን አጥረው ህገ-ወጥ ግንባታ ለመገንባት ሙከራ ሲያደርጉ መያዛቸው ተገለፀ ።

ባለስልጣኑ መሬት ባንክ ገብቶ ሲጠብቀው በነበረን መሬት ላይ የተገነባውን ግንባታ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ደንብ ማስከበረ ጽ/ቤት ከክፍለ ከተማና ከወረዳ አመራሮች ጋር በመቀናጀት የጸጥታ አካላትን በማሳተፍ ግንባታውን በማፍረስ የመንግስትና የህዝብ መሬት ወደ ነበረበት እንዲመለስ ማድረጉ አስታውቋል።

ጥፋተኞችን ለህግ ለማቅረብ መረጃውን በማደራጀት በቁጥጥር ስር በማዋል በሊዝ አዋጁ ተጠያቂ ለማድረግ በሂደት ላይ መሆናቸው ተጠቁሟል።

ባለስልጣኑ በህገ-ወጦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፀ ሲሆን ደንብ የሚተላለፉ አንዳንድ ግድ የሌሽ ግለሠቦችን ልማት ወዳዱ የከተማችን ነዋሪዎች በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጡ ጥሪውን ያቀርባል ።
👍112
የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ከዋና ፍሳሽ መስመር በማገናኘት ወደ ወንዝ እንዲገባ ያደረጉ የንግድ ቤቶችን 600 ሺህ ብር ተቀጡ

30/06/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ*

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ከዋና መስመር ትቦ ጋር ባገናኙ ሁለት የንግድ ቤቶች በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት እያንዳንዳቸው 300,000/ሶስት መቶ ሺህ/ ብር በድምሩ 600,000/ስድስት መቶ ሺህ ብር በመቅጣት እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ ማንኛውም አይነት ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ ከመልቀቅና ደረቅ ቆሻሻ ወንዝ ውስጥ ከመጣል እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

ተቋሙ ድርጊቱን በሚፈፅሙ ግለሰቦችና ተቋማት በደንብ ቁጥር 180/2017 መሠረት እርምጃውንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል።

የከተማ አስተዳደሩ የአዲስ አበባ ወንዞች ከመጥፎ ሽታ ተላቀው የመዝናኛ ቦታዎች እዲሆኑ የጀመረው ስራ ዳር ለማድረስ ደንብ በማስከበር የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ገልጿል።

ህብረተሰቡም ደንቡን ተላልፎ የሚገኝ አካል ሲመለከት በነፃ የስልክ መስመር 9995 ጥቆማ እንዲሰጥ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍84
ባለስልጣኑ በዛሬው እለት ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቁ ግለሰቦችና ተቋማትን 2,300,000/ሁለት ሚሊየን ሶስት መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱ አስታወቀ

02/07/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቁ ድርጅቶችና ግለሰቦች በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት የገንዘብ ቅጣቶች በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ 3 ድርጅቶች እያንዳንዳቸው እያንዳንዳቸው 300,000/ሶስት መቶ ሺህ/ ብር በድምሩ 900,000/ዘጠኝ መቶ ሺህ ብር እና አንድ ግለሰብ 100,000/አንድ መቶ ሺህ/ ብር በድምሩ 1 ሚሊዮን ብር ቀጥቷል፡፡

በተያዘ ዜና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 700 ሺህ ብር ፤በነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 300 ሺህ ብር ፤ በጉለሌ ክፍለ ከተማ 300 ሺህ ብር በድምሩ በዛሬው እለት 2300,000/ሁለት ሚሊየን ሶስት መቶ ሺህ ብር/ በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

ባለስልጣኑ ተቋማት እና ግለሰቦች ማንኛውም አይነት ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ በመልቀቅም ሆነ ደረቅ ቆሻሻ ወንዝ ውስጥ በመጣል ደንብ በመተላለፍ ከሚወሰደው የቅጣት እርምጃ እራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስቧል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ድርጊቱን በሚፈፅሙ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ በደንብ ቁጥር 180/2017 መሠረት የሚወሰደው እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል።

ህብረተሰቡም ደንቡን ተላልፎ የሚገኝ አካል ሲመለከት በነፃ የስልክ መስመር 9995 ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን አስተላልፏል።

ዘገባው ፦ የባስልጣኑ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
👍11