የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.75K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት ለመከላከል በወጣዉ ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ።

26/06 /2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠናና የቅድመ መከላከል ዘርፍ ከአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር
የወንዞች ዳርቻ ልማትን እና ብክለት ለመከላከል
በወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ የሁለቱ ተቋማት ኃላፊዎች በተገኙበት የአሰልጣኞች ስልጠና በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሄደ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በከተማችን የሚገኙ ትላልቅና ትናንሽ ወንዞች ለልማት ውለው ለህብረተሰቡ መገልገያና ለቱሪስት መስብ እንዲሆኑ በርካታ ተግባራት በከተማ አስተዳደሩ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ወንዞችን እና የወንዝ ዳርቻዎችን ከብክለት ጽዱ ለማድረግ ሁለቱም ተቋማት በጋራ በመቀናጀት ለመከላከልና የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት ዕውቀትና ልምድና ባለቸው አሰልጣኞች ስልጠናውን በመስጠትና ወደ ታች በማውረድ በየደረጃው ላሉ አካላትና ለከተማው ነዋሪዎች በቂ ግንዛቤ በመፍጠር ወንዝ ዳርቻዎችን እንዳይበከሉ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል ።

በመድረኩ የተገኙት የአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን ዮናስ የከተማችንን የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል ከተማዋን ፅዱ ፣ አረንጓዴ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ በከተማዋ ዉስጥ የሚገኙ ወንዝ ዳርቻዎች የማልማት ስራ እየተከናወነ ሲሆን ንፁህና ጤናማ አካባቢ እንዲሆኑ እና እንዳይበከሉ ለማድረግና ጥበቃ በማድረግ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ይህ ደንብ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ወንዞች ብክለት በአካባቢ እና በጤና ላይ የሚያደርሰው ጉዳት እና መፍትሔዎች እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል ደንብ ቁጥር 180/2017 ቀርቦ ግንዛቤ ተፈጥሮበታል።

ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ከተፈጠረ በኃላ በቸልተኝነት ደንቡን ተላልፎ በሚገኝ አካል ላይ ዝቅተኛው የገንዘብ ቅጣት ሁለት ሺህ ብር ሲሆን ከፍተኛው እስከ አንድ ሚሊዮን ብር ድረስ የሚያስቀጣ እንደሆነ በደንቡ ተገልጿል።

በስልጠናው ማጠቃለያም የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የወንዝ ዳርቻ ልማት እና ብክለትን መከላከል ዙሪያ በወጣው ደንብ ላይ የተሰጠንን የስራ ተልዕኮና ኃላፊነት ለመወጣት ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ ሰልጥኖ አሰልጣኞች በየደረጃው በመውረድ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራውን አጠናክረው ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበት ቀጣይ የስራ አቅጣጫ በባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ተሰጥቷል።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍31
የደንብ መተላለፍን በመቀነስ የላቀ አፈፃፀም ያስመዘገበው ክፍለ ከተማ ልምዱን አጋራ

27/06/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

ባለስልጣኑ በ2017 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ክፍለ ከተሞች 25% የደንብ ጥሰትን እንዲቀንሱ ያወረደውን መሪ እቅድ 50.4% በመቀነስ 100% አስመዝግቦ ውጤታማ የሆነው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት ልምዱን ለሌሎች ክፍለ ከተሞች አጋርቷል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የተመራው የልምድ ልውውጥ ልዑካን ቡድን የተቋሙን ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የማዕከል ዳይሬክተሮችና የ11ዱንም ክፍለ ከተማ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳኜ ሂርጳሳ የልምድ ልውውጥ ልዑካን ቡድኑን የጽ/ቤታቸው፣የአመራራቸውና የሰራተኛው ቅንጅታዊ አሰራር ልምድና ተሞክሯቸውን በዝርዝር አስቃኝተዋል።

ስትራቴጂካዊ የሆነ የአመራር ስልትን በመንደፍ ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ድረስ ስራዎችን በቅንጅት መምራት በመቻሉ የደንብ ጥሰትን ከእቅዱ በላይ ለመቀነስ ማስቻሉን አቶ ዳኜ አስገንዝበዋል።

በተለይ የቁጥጥርና ኢኒስፔክሽን፣ የቅድመ መከላከልና የግብረ-ኃይል ቡድኑ እስከ ወረዳ ድረስ ባደረገው ጥልቅ ድጋፍና ክትትል ዘጠኙንም የደንብ መተላለፎች ላይ አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል።

የተሰሩ ስራዎችንም የካይዘን ፍልስፍናን ተግባራዊ በማድረግ መረጃዎችን በማጥራት፣ ማደራጀት፣ ማንፃት፣ ማቀናጀትና ማዝለቅ የተቻለ መሆኑን በልምድ ልውውጡ ተመላክቷል።

የልምድ ልውውጡ ተሳታፊ አካላትም ክፍለ ከተማው በ2017 ግማሽ ዓመት ቀዳሚ እንዲሆን ያበቃውን አፈፃፀም በአካል ወርደን በማየታችን ውጤቱ የሚገባውና እኛም በርካታ ልምዶችን የቀሰምንበት ነው በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ጽ/ቤቱ በሪፎርም ስራም በክፍለ ከተማው ካሉ 36 ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር ተወዳድሮ በአንደኛነት ማጠናቀቁ በእርግጥም ሌሎች ክፍለ ከተሞች ልምዱን በመቅሰም የተቋሙን ራዕይ እውን ለማድረግ የሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝ ማሳያ መሆኑን የገለፁት የልምድ ልውውጥ ቡድኑን የመሩት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ገልፀዋል።

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተገኘውን ሁሉን አቀፍ የላቀ አፈፃፀም ጠምሮ በመቀመር ከማዕከል እስከ ወረዳ ብሎም ሌሎች የከተማ አስተዳደሩና የክልል ከተማ ተቋማት ጭምር እንዲጋሩት ማድረግ እንደሚገባ ዋና ስራ አስኪያጁ በአፅንኦት አስገንዝበዋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
👍3
ፍሳሽ ቆሻሻን በመልቀቅ ወንዝ የበከለ ድርጅት 300 ሺህ ብር ተቀጣ

28/06/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ*

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣ ከአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመቀናጀት በዛሬው ዕለት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ይህን ደንብ ተላልፎ በተገኘ ቫይብስ ሆቴልና ስፓ/Vibes Hotel & Spa/ ድርጅት ላይ በደንብ ቁጥር 180/17 የቅጣት ሰንጠረዥ 1 ተራ ቁጥር 3 ያልተጣራ ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቀ ድርጅት 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል።

ባለስልጣኑ በደንብ ቁጥር 180/2017 ላይ ከአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በተደደጋጋሚ በመገናኛ ብዙኃንና በመድረኮች ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ፈጥሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ በጀት በመመደብ ከተማዋን ውብ ጽዱና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የወንዝ ዳርቻና የኮሪደር ልማት 7/24 በመስራት የወንዞች ዳርቻ የማስዋብ ስራዎችን እየሰራ መሆኑ ይታወቃል።

ህብረተሰቡም መንግስት ከፍተኛ ወጪ አውጥቶ ያለማቸውን ሀብቶች እንዲንከባከብና ደንብ ተላልፎ የሚገኝ አካል ሲገኝ በ9995 ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን አቅርቧል።

ባለስልጣኑ በቀጣይ በየትኛውም የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች ዙሪያ የሚደረጉ የደንብ መተላለፎችን እንደማይታገስና እርምጃውንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
👍6