የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.1K subscribers
1.81K photos
4 videos
1 file
53 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ ለ6ተኛ ዙር ፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና ከኢትዮጵያ ፓሊስ ዩንቨርሲቲ ጋር የውል ስምምነት ተፈራረመ።

17/06/2017
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በ6ተኛ ዙር ለሚያሠለጥናቸው 2ሺህ የፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና ውል ስምምነት ተፈራረመ::

ስልጠናው የሚሰጠው በኢትዮጵያ ፓሊስ ዩንቨርስቲ አፓስቶ ካምፓስ እንደሚሰጥ በውል ስምምነቱ ወቅት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ አስታውቀዋል።

የፓራ ሚሊተሪ እጩ ኦፊሰሮቹ ስልጠና የንድፈ ሀሳብና ወታደራዊ ስልጠናዎችን ያካተተ እንደሚሆንና ብቁ የደንብ አስከባሪ ኦፊሰሮችን በማሰልጠን ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ የኢትዮጵያ ፓሊስ ዩንቨርሲቲ ምክትል ፕሬዘዳንት ረ/ኮሚሽነር ደረጀ አስፋው ገልፀዋል።

በውል ስምምነት ፊርማው ወቅት የሁለቱም ተቋማት አመራሮች ተገኝተዋል ኃላፊዎቹ ተፈራርመዋል።

ከዚህ ቀደም ዩንቨርስቲው የ5ተኛ ዙር የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮችን ስልጠና እና የአጠቃላይ ኦፊሰሮችን የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን መስጠቱ ይታወሳል።

ዘገባው :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
👍9👏3
የወርቃማ ሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርኃ ግብር ተከናወነ።

17/06 /2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሰኞ ማለዳ ከስራ ገበታ በፊት የሚያካሂደው የእውቀትና ተሞክሮ ሽግግር የሚካሄድበት የወርቃማ ሰኞ ማለዳ ፕሮግራም ሠራተኛውን የሚነቃቃና ለስራ ዝግጁ የሚያደርግ መሆኑ ተገለፀ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ያለፈውን ሳምንት ውጤታማ ስራዎችን አስታውሰው የተያዘው ሳምንት የስራ አቅጣጫዎችን ሰጥተዋል።

ይህ የወርቃማ ሰኞ ማለዳም በአመራሩና በሰራተኛው መካከል ያለውን ቤተሰባዊነት እጅግ እያጠናከረና ምቹ የስራ ሁኔታን እየፈጠረ እንደሚገኝ አስታውሰዋል።

በዛሬው መድረክም የባለስልጣኑ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ይልማ በራስ የመተማመን /self confidence / በተመለከተ እውቀታቸውን በማካፈል የህይወትና የስራ ተሞክሯቸውን አስተማሪ በሆነ መልኩ አጋርተዋል።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍9
ባለስልጣኑ በከተማው የልማት ኮሪደር አስፓልት በቸልተኝነት የደንብ መተላለፍ የፈጸመ ድርጅት 300 ሺህ ብር መቅጣቱ አስታወቀ

የካቲት 17/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ዩኒቲ ሀውሲንግ የተባለ የህንፃ ግንባታ ድርጅት በኮሪደር ልማት በተሠራ እስፓልት ላይ ሃላፊነት በጎደለው ሁኔታ በማቆሸሹ በደንብ ማስከበር ባለስልጣን አፊሠሮች 300,000 /ሦስት መቶ ሺህ/ ብር መቀጣቱ ተገለፀ።

ድርጅቱ በተደጋጋሚ ግንዛቤ ተፈጥሮለት ከዚህ በፊት 100 ሺህ ብር የተቀጣ ሲሆን ድጋሚ ተመመሳሳይ ጥፋት በመፈጸሙ የቅጣቱ እጥፍ 200 ሺህ ብር በድምሩ 300,000 /ሦስት መቶ ሺህ/ ብር ተቀጥቶ ያቆሸሸውን ቦታ እንዲያፀዳ ተደርጓል ።

የከተማ አስተዳደሩ የልማት ኮሪደር ስራዋች አዲስ አበባን ውብ ጽዱ በማድረግ የከተማዉ ህዝብ እንዲጠቀምበት ፣የቱርስት መስህብና ከተማው ሌሎች በአለማችን የሚገኙ ከተሞች የደረሱበትን ዕድገት ደረጃ ለማድረስ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሌት ተቀን 7/24 በመሥራት ለህዝብ አገልግሎት በማዋል ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ማድረጉ ይታወቃል።

የአዲስ አበባ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በደንብ ተላላፊዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ በመግለጽ ልማት ወዳዱ የከተማችን ነዋሪዎች አጥፊዎችን መረጃ በመስጠት የጀመረውን ጥቆማ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አቅርቧል።

መረጃው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍71🕊1