የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.75K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ በሁለተኛው የብልጽግና መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ከሰራተኞቹ ጋር ውይይት አካሄደ

06/06 /2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን "ከቃል እስከ ባህል" በሚል መሪ ቃል በ2ኛ የብልፀግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ከማዕከሉ ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ።

በውይይት መድረኩ የሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ዙሪያ የተዘጋጀው ሰነድ በባለስልጣኑ የስነ-ምግባርና የጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዬብ ከበደ ቀርቧል።

በመድረኩም የፓርቲው የጉባዔ ውሳኔዎችና የቀጣይ አቅጣጫዎች በዝርዝር ቀርበዉ ሰፊ ዉይይት ተደርጓል የብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ላይ ቀጣይ ትኩተረት ሊሰጣቸው እንደሚገቡ አቅጣጫ በተቀመጠባቸው ነጥቦች በዝርዝር ቀርበዋል፡፡

በውይይቱ የባለስልጣኑ አመራር እና ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን ጠንካራ ተቋም መገንባት፣ ብሄራዊ ገዥ ትርክትን ማጠናከር ፣ የኢኮኖሚ እና ልማትን ከማፋጠን፣ ማህበራዊ ብልጽግና ከማረጋገጥ ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራዎችን መሠራቱ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ፓርቲው በአጭር ጊዜ በኢኮኖሚ ፣ በማህበራዊ እና በዲፕሎማሲው ረገድ አመርቂ ለውጦች ማምጣት ተችሏል ቀጣይነት እንዲኖረው ሁሉም የመንግስት ሰራተኛ የሚጠበቅበትን ሃላፊነት መወጣት ይኖርበታል ብለዋል።
👍6👏2🥰1
ባለስልጣኑ በቀጣይ ለሚሰጠው የ6ኛ ዙር የፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና በተመለከተ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር የስልጠና እቅድ ውይይት አደረገ ::

6 - 06 2017
አዲስ አበባ

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በቀጣይ ለሚሰጠው 6ተኛ ዙር ፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና ስርአተ ትምህርት እና አጠቃላይ የስልጠና ሂደቱን እቅድ ላይ የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ውይይት አድርጓል::

ስልጠና በንድፈ ሀሳብ እና በአካል ብቃት የጎለበተ ህጉን ከቃል በበለጠ መሬት ላይ ማስከበር የሚችል ኦፊሰር ከማፍራት አንፃር ጉልህ ሚና አለው ያሉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በስልጠናው ዘርፈ ብዙ ልምድ ካለው ተቋም ጋር መስራታችን በንድፈ ሀሳብ በአካል ብቃትም የጎለበተ የሰው ሀይል ለመገንባት ጉልህ ሚና አለው ብለዋል::

አጠቃላይ የስልጠና ሂደቱን በሚመለከት ስርአተ ትምህርቱን እና አጠቃላይ የበጀት እቅድ ሰነድ በስልጠናና ጥናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በወ/ሮ ላቀች ሃይሌ የቀረበ ሲሆን በሰነዱም ስለ ስልጠናው አላማ፣ የጊዜ ሰሌዳ፣ የሰው ሀይል ትንተና፣ስለ ትምህርት እና ፈተና አሰጣጥና የምዘና ሂደት እንዲሁም የግብአት እና በጀት ጉዳዮች ቀርበው ውይይት ተደርጓል::

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ም/ጀነራል መስፍን አበበ በመጡት አመራሮች በእውቀት እና በአካል የዳበረ የሰው ሀይልን ይዞ እንደተቋም ለመራመድ ታስቦ ይህ ስልጠና መዘጋጀቱ መልካም መሆኑ ገልጸው ይህ እቅድ እንዲሳካ ዩኒቨርሲቲው የበኩሉን እንደሚወጣ ገልጸዋል ::

በመጨረሻም ከቤቱ የተነሱትን ሀሳብ እና አስተያየቶች የጋራ በማድረግ ወደ ትግበራ እንደሚገባ ተገልጿል።
👍16👏4
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በየ15 ቀኑ የሚታተመው ትምህርታዊ አምድ
👍21🥰3👏1
ባለስልጣኑ የወርቃማ ሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር አከናወነ።

10 -06 -2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሰኞ ማለዳ ከስራ ገበታ በፊት የሚያካሂደው የእውቀት ሽግግር ፕሮግራም የባለስልጣኑ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት አካሄደ፡፡

የመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ 38 የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ከአመራሩ ጀምሮ እስከ ኦፊሰሩ የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባሙ መወጣትና መፈጸም ችሏል ለዚህም ለሰራው መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን በማቅረብ መጪው ሳምንት ስራዎቻችን በአግባቡ የምንወጣበት የደስታ ሳምንት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል ።

በዕለቱ የባለስልጣኑ የስታንዳርዳይዜሽን ዝግጅት፣ አገልግሎት አሰጣጥድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ቀጸላ የራሳቸውን የህይወትና የትምህርት እና የስራ ተሞክሮና ልምዳቸውን ለሌሎች አስተማሪ በሆነ መልኩ አጋርተዋል።

ባለስልጣኑ ሁልጊዜ አዳዲስ ሀሳቦችን ፣ተግባራትን ለማወቅ በሞመከር ጥረት ውስጥ ማለፍ ዉጤታማና ስኬታማ እንደሚያደርግ ገልጸዋል ፡፡

በተጨማሪም በመድረኩ የተቀናጀ የሲቪል ሰርቪስ መረጃ አያያዝ ስርዓት" (ICSMIS ) ሲስተሙን የመጠቀሚያ ስም እና ማለፊያ ቃል በማዘጋጀት የዓመት እረፍትና የስራ ልምድ በሲስተም የሚጠየቅ መንገድ መመቻቸቱን የሰው ሀብት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ይልማ ገልጸዋል

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍122👏2