የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
992 subscribers
1.5K photos
4 videos
1 file
51 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
የባለስልጣኑ እየሰጠ ያለው የፖራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ህግና መመርያን ተከትለው እንዲሰሩ የሚያስችል መሆኑ ተገለፀ

10 - 02 - 2017 ዓ.ም
*አዲስ አበባ*

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በተለያዮ ርዕሰ ጉዳዬች ዙሪያ የሚሰጠውን የሁለተኛ ዙር ስልጠና ሁለተኛ ቀን የአቅም ግንባታ ስልጠና በሁሉም ክፍለ ከተሞች በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ ውሏል ።

ሰልጠናው በዛሬው እለት በዲስፕሊን መመሪያ ቁጥር 3/2015 ዓ.ም ዙርያ እና በተሻሽው በደንብ ቁጥር 167/2016 ዓ.ም ላይ በተሻሻሉ የቅጣት እርከኖቹን ላይ የዲስፕሊን ጥፋቶች እና በቅሬታ አቀራረብ ሂደቶች ላይ የተሰጠ ሲሆን በነገው ዕለትም ስልጠናው የሚቀጥል ይሆናል ።

የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ ኮ/ር አህመድ መሐመድ እና የስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ላቀች ሀይሌ ስልጠናው የሚሰጥ በትሂደት ጉብኝት በማድረግ ሰልጣኞችና አሰልጣኞች አበረታተዋል ።

በስልጠናው የደንብ ጥሰቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የስነ ምግባር ግድፈት እንዳይፈፅሙ ፣ በስነ ምግባር የታነፁ እንዲሆኑና ህግና መመርያን ተከትለው እንዲሰሩ የሚያስችል መሆኑ የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ ኮ/ር አህመድ መሐመድ ገልፀዋል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎች ስልጠናው በእውቀትና መብትና ግዴታቸው ለመስራትናለስራቸው እጅግ አስፈላጊ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ከመድረክ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ዘገባው :- የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
ባለስልጣኑ ልምዱን እና ተሞክሮውን ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ልዑካን ቡድን አባላት አጋራ

ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ለመጡ የልዑካን ቡድን አባላት በተቋም አደረጃጀት፣በኮሪደር ልማት አሰራር፣ በመመሪያ ዝግጅት ፤በሰው ሃይል አደረጃጀት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በተመለከተ ባለስልጣኑ ያለውን ልምድና ተሞክሮ አጋርቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል-ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ንጉሴ በልምድ ማጋራቱ ወቅት የተቋሙ አደረጃጀት እና ያጋጠሙ ችግሮች ከሚመለከተው አካል በመነጋገር የተፈታበት ሂደት እና ተቋሙ በማጠናከር የከተማዋን ገጽታ በመቀየር ሂደት በርካታ ስራዎች ማከናወኑን ለልዑካን ቡድኑ አባላት ገልፀዋል።

በልምድ ልውውጡ የባለስልጣኑ ዳይሬክተሮች እንደየስራ ክፍላቸው አሰራሮች እና የተቋሙ ተሞክሮዎች የገለጹ ሲሆን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከተቋሙ ልምድ በመውሰድ እና ተግባራዊ በማድረግ ተጨባጭ ውጤት ማምጣት እንደሚችሉ ለልዑካን ቡድኑ አባላት አስረድተዋል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የልዑካን ቡድን አባላት ተቋሙ የተደራጀበት እና ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በመነጋገር እየሰራ ያለው ውጤታማ ስራዎች አድንቀው የወሰዱት ተሞክሮ ጠቃሚ እና ልምዱን በከተማቸው ተግባራዊ በማድረግ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ።

ዘገባው :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።