የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
997 subscribers
1.5K photos
4 videos
1 file
51 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ በ2017 በጀት ዓመት በመጀመሪያ ሩብ አመት የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ገመገመ

27/01/2017ዓ.ም
**አዲስ አበባ*

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 የመጀመሪያ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የባለስልጣኑ የበላይ ኃላፊዎች በተገኙበት ከማዕከሉ ፕሮሰስ ካውንስል አባላት ጋር በዛሬው እለት ተገምግሟል ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍ ክትትል ፣ ቁጥጥርና እርምጃ አወሳሰድ ዘርፍ እና የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍና የድጋፍ ሰጪ ዳይሬክተሮች የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አፈጻጸም ሪፖርት በዝርዝር የቀረበ ሲሆን በሩብ ዓመቱ የታዪ ክፍተቶች ያጋጠሙ ችግሮችን እና ጠንካራ ጎኖች ቀርበው ውይይት ተደርጓል ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በሩብ ዓመቱ የተከናወኑ ስራዎች በጥንካሬ የሚገለፁ መሆናቸው ገልፀው በቀጣይ ሁሉም ሰራተኞች እና በየደረጃው ያሉ አመራሮች በቁርጠኝነት በመስራት አሁን ላይ የተገኘውን ውጤት በማስቀጠል ከተማችን ደንብ መተላለፎች የቀነሰባት ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ዘገባው:-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው ።
በቅድሚያ የረዳን ፈጣሪ ይመስገን
እንኳን ደስ አለን፣ እንኳን ደስ አላችሁ,!

በደቡብ ኮሪያ ሴኡል ከተማ የ2024 ስማርት ሲቲ ሊደርሺፕ ሽልማት ከ72 ሀገሮችን እና ከ115 አቻ ከተሞች አስተዳደር ከንቲባዎች መካከል ምርጥ የአመራር ሸልማት በማግኘታችን በከተማ አስተዳደሩ ስም እንኳን ደስ አለን፣ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ።

ይህ ያስመዘገብነው ውጤት በከተማችን በተሰሩ እና በህዝባችን ተሳትፎ እና ቅንጅት የተገኘ ውጤት በመሆኑ ለዚህ ወጤት መገኘት አስተዋፅኦ ያደረጉ አካላትን ሁሉ እያመሰገንኩ፣ በደቡብ ኮሪያ 2024 ሴኡል ስማርት ሲቲ ሊደርሺፕ የእውቅና ሸልማት ስለተበረከተልንም እናመሰግናለን።

ለህዝባችን ሰርተን በምናገኘው እውቅና ሁሉ ተመስጋኙ ሁሌም ከጎናችን በመሆን የልማቱ ዘዋሪ እና ተጠቃሚ የሆናችሁ የከተማችን ነዋሪዎች መሆናችሁን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ።
በድጋሚ እንኳን ደስ አለን፣ እንኳን ደስ አላችሁ

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባረክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከፍተኛ የመንገድ መጨናነቅ ሲፈጥር የነበረው የጦር ሃይሎች አደባባይ ድልድይ ስር ህገ-ወጥ ንግድ መፅዳቱ ተገለፀ

03/02/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በጦር ኃይሎች አደባባይ ድልድይ ስር የነበሩ ህገ-ወጥ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ቦታውን ለእግረኛ ምቹ በማድረግ ህገወጥነት እንዲቀነስ ማድረጉን የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት አስታወቀ።

ክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ተወካይ አቶ አብረሀም የአካባቢው ገጽታ ሲያበላሽ፣ መንገድ ሲያጨናንቅና የትራፊክ አደጋ ሲፈጥር የነበረውን ችግር አሁን ላይ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ና ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ቦታውን በማጽዳት ለእንቅስቃሴ ምቹ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል ።

የኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 9 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዱኛ ካራ እንደገለፁት ከዚህ ቀደም ቦታው ላይ ህገወጥ ንግድ በሰፊው የነበረበት በመሆኑ የእግረኛ መንገድና ድልድይ ውስጥ ከፍተኛ የመንገድ መጨናነቅ ሲፈጥር የነበረው መሆኑ ገልፀዋል።

በተግባሩ የተሳተፉ የባለስልጣኑ ኦፊሰሮች በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ በአዋጅ በተሰጣቸው ሀላፊነት መሰረት የተሰራው ልማት ለታለመለት አላማ እንዲውል ደንብ የማስከበሩን ስራ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው ከዚህ በፊት ቦታው ህገወጥ ንግድ እግረኛ ተሽከርካሪ ለመተላለፍ ሲቸገሩ እንደነበር ገልፀው አሁን በነፃነት እንድንሄድ ላደረጉት ለደንብ ማስከበር አባላት አመስግነዋል።

ዘገባው:-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
ኦፊሰሮች 17ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን እየተከበረ ይገኛል

       ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም

ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ለሉዓላዊነታችን ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሐሳብ ነው የሚከበረው የዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በክፍለ ከተሞች ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኦፊሰሮች ወታደራዊ ሰልፍ ታጅቦ እየተከበረ ይገኛል ።