ባለስልጣኑ ከEMA Tower ጋር የቢሮ ኪራይ የውል ስምምነት ተፈራረመ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለተቋሙ ሰራተኞች እና ተገልጋዮች ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር ከEMA Tower ጋር የቢሮ ኪራይ ውል ስምምነት በዛሬው ዕለት በባለስልጣኑ ዋና ሰራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን በኩል በጥር 7/2016 ዓ.ም ተፈራርሟል ።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በስምምነቱ ላይ እንደተናገሩት አሁን ያለንበት አካባቢ ለሰራተኞቻችን እና ለተገልጋዮች ለትራንስፖርት እና በቂ አገልግሎት ለመስጠት አመቺ ባለመሆኑ በሰራተኞች ተደጋጋሚ ጥያቄ መሠረት አካባቢው ለመቀየር ማስፈለጉ ገልፀዋል።
ዋና ሰራ አስኪያጁ አያይዘው እንደገለጹት ለሰራተኛው እና ለተገልጋዩ ማግኘት የሚገባውን አገልግሎት በአግባቡ ለመስጠትና ተጠቃሚ አንዲሆን በማሰብ ኮሚቴ በማዋቀር ለሰራተኛውና ለሰራ አምቺ ይሆናል ተብሎ የታሰበውን ቦታዎች በማየትና በመምረጥ ከህንፃው ባለቤት ጋር ከስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል ።
አዲሱ ህንፃ ለሰራተኞቹ ልጆች የህጻናት ማቆያ ቦታ፣ ካፍቴርያ፣ እስከ 300 ሰው የሚይዝ የመሠብሰቢያ አዳራሽ እና ሌሎች አስፈላጊ የስራ ክፍሎች እንደሚኖሩት ተገልጿል።
በቀጣይ ቢሮው አሁን ካለበት የቦታ እና የህንፃ ቅያሪ ዝውውር ሲያደርግ በተለያዩ ማስታወቂያዎች ለህብረተሰቡ የሚገለጽ መሆኑ ተጠቁሟል ።
ዘገበው ፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

የባለስልጣኑ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ የ6ወር እቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የስልጠናና የቅድመ መከላከል ዙርፍ የ2016 በጀት ዓመት የ6ወር እቅድ አፈጻጸሙን ከማዕከል እስከ ወረዳ ካሉ የዘርፉ ኦፊሰሮችና ሰራተኞች ጋር የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በተገኙበት በቂርቆስ ክ/ከተማ መሰብሰቢያ አዳራሽ የግምገማ መድረክ አካሂዷል ።
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለሥልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አበባ እሸቴ እንደተናገሩት ስራዎችን ከማዕከል እስከ ወረዳ ተናበን እና ተቀናጅተን በመሰራታች በ2016 በጀት ዓመት በ6ወር የተሻሉ ሰራ መከናወኑን በመግለፅ በእቃዳችን መሰረት ምን ሰራ አከናወንን የሚለዉን በጋራ በማየት ያመጣነውን ጥሩ ተግባራት ለማስቀጠል በሰራ የታዪ ክፍተቶችን በመለየት በቀጣይ ጠንክረን በመስራት ክፍተቶችን በመሙላት የቅድመ መከላከል ስራችን በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ገልጸዋል ።
የስልጠናና የቅድመ መከላከል ዙርፍ የ2016 በጀት ዓመት የ6ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የባለስልጣን የቅድመ መከላከልና ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ስርካለም ጌታሁን አቅርበዋል ።
በሪፖርቱ የዘርፉ ዋና ዋና ስትራቴጂክ ግቦችና አላማዎች ፣ በ6ወር የተከናወኑ ተግባራት ፣ ጥንካሬዎች እና ክፍተቶችና በቀጣይ በትኩረት ሊከናወኑ የሚገቡ ተግባራት ተካተዋል
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶበት ቀጣይ የሰራ አቅጣጫ በባለሥልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ሰጥተው መድረኩ ተጠናቋል ።
ዘገባው ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

ጨለማን ተገን በማድረግ ከ500 ካሬ ሜትር በላይ የተወረረ መሬት ተቀለበሰ።
08/05/2016 ዓ.ም
*አዲስ አበባ*
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በወረዳ 02 ልዩ ስሙ ጀርመን አደባባይ አከባቢ ጨለማን ተገን በማድረግ ከ500 ካሬ ሜትር በላይ መሬት በወረረ ግለሰብ ላይ እርምጃ ተወሰደ።
ጥር 07/2016 ዓ.ም ከለሊቱ 9:00 ሰዓት ገደማ አንድ ግለሰብ ውስን ሀብት የሆነውን የህዝብና የመንግስት መሬት ከህግ አግባብ ውጪ በኃይል በመውረር አጥሮ መጋዘን በመስራትና ኮንቲነር በማስቀመጥ መሬት የወረረውን ግለሰብ የወረዳው የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ወረራውን መቀልበሱን የወረዳ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈቀደ ዲዳ ለባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ገልፀዋል።
ሀላፊው በህገ-ወጥ መንገድ እና በሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ስራ ላይ በማይሆኑበት የለሊቱን ጊዜ በመጠቀም ወረራ የተፈፀመበትን መሬት ሙሉ በሙሉ በማፅዳት የወረረውንም ግለሰብ በህግ አግባብ ተጠያቂ ለማድረግና መሬቱን ወደ መሬት ባንክ ስርዓት ለማስገባት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ ተቋማት ጋር እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል።
በመጨረሻም ህብረተሰቡ በህገወጥ መንገድ ጉልበትቱና ሀብቱን ከማባከን እና በህግ ተጠያቂ ከመሆን እራሱንና ቤተሰቡን እንዲጠብቅ በማሳሰብ ህጋዊ አሰራር በመከተል ስራዎቹ ማከናወን አንደሚገባ አቶ ፈቀደ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዘገባው፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።

👍1
Channel name was changed to «የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን»
Channel name was changed to «የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa CodeEnforcement»
Channel name was changed to «የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority»
የጥምቀት በዓል ሀይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ ባማረና በደመቀ መልኩ እንዲከበር ዛሬ ከሀይማኖት አባቶችና የከተማችን ነዋሪዎች ጋር ተወያይተናል።
ጥምቀት ወደ ከተማችን የሚመጡ የውጭ ሀገር ጎብኚዎችን የሚስብ የቱሪስት መዳረሻ እና በዩኒስኮ የተመዘገበ የሀገራችን መድመቂያ ታላቅ በዓል በመሆኑ፣ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲከበር ሁሉም የበኩሉን አስተዋፅዖ ሊወጣ ይገባዋል።
በዓሉ የሰላምና የፍቅር በመሆኑ በሰላም፣ በመከባባርና መደጋገፍ እንድናከብረው ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን !
ጥር 10/2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ 2016 ዓ.ም የጌታችን እና የመድሀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ /አደረሰን።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሠላም አደረሳችሁ እያለ፤በዓሉ የሠላም፣የፍቅር እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ ይመኛል።
የጥምቀት በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እምነታቸውን በነፃነት በአደባባይ ወጥተው በጋራ የሚያከብሩበት ፣የእርስ በርስ ግንኙነታቸውን የበለጠ የሚያጠናክሩበት ፣መንፈሳዊ እሴቶቻቸውን የሚያዳብሩበት እና ማህበረሰባችን ተቻችሎና ተከባብሮ በጋራ መኖርን ለመላው የዓለም ህዝቦች ተምሳሌትነቱን የሚያሳዩበት ታላቅ በዓል ነው።
የጥምቀት በዓል ከሃይማኖታዊ በዓል በተጨማሪ በዩኔስኮ ከማይዳሰሱ የአለም አቀፍ ቅርስነት መመዝገቡ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ትልቅ እድል የከፈተ ነው።
ከዚህም በመነሳት በዓሉ የፍቅር፣ የአብሮነትና የሰላም እንደመሆኑ መጠን ሁላችንም በጋራ ፣በመተሳሰብ፣ በአንድነት በዓሉ ሀይማኖታዊ ይዘቱንና ኢትዮጵያዊ ዕሴቶቻችንን በጠበቀ መልኩ ሊናከብረው ይገባል።
በዓሉ ስናከብር በከተማው የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች እና ተያያዥ ህገ ወጥ ተግባራት እንዳይፈጸም እና በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የበኩልን ድርሻ እንዲወጣ አደራ ማለት እወዳለሁ፡፡
መልካም የጥምቀት በዓል !
ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ዋና ሥራ-አስኪያጅ

የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱት የደንብ ማስከበር አመራሮች፣ኦፊሰሮች እና ሰራተኞች ምስጋና ቀረበ።
ጥር 14/2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ሰራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ከከተራ ቀን ጀምሮ አስከ ትላንትናው የቅዱስ ሩፋኤል በዓል ድረስ እንደ አካባቢው ሁኔታ በቀን ፀሐይ እና የሌሊት ብርዱን ችለው በዓሉን በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የደንብ ማስከበር አመራሮች፣ ኦፊሰሮች እና ሰራተኞች ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል ።
በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ የደንብ ማስከበር አባላት ከጸጥታ አካላት፣ከሀይማኖት አባቶች፣ ከከተማው ነዋሪዎች እና ከበጎ-ፍቃደኛ ወጣቶች ጋር በመቀናጀትና በመናበብ ውጤታማ ስራዎች መስራታቸው ሻለቃ ዘሪሁን ገልፀዋል።
ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ የደንብ ማስከበር አመራሮች፣ ኦፊሰሮች እና ሰራተኞች ከበዓሉ መከበር አስቀድሞ በበዓል አከባበሩ የጸጥታ ችግሮች እንዳይፈጠር መወያየታቸው እና መግባባት ላይ መድረሳቸው አስታውሰው በውይይቱ መሰረት ተሰርቶ ውጤት ማምጣቱ ገልፀዋል።
በመጨረሻም የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ የተሰራው የተናበበ እና የቅንጅት ስራ በሌሎች ስራዎቻችን በማስቀጠል የከተማችን የደንብ መተላለፎች በመከላከል ዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ እድገት ማረጋገጥ ይኖርብናል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ዘገባው ፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።