የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.08K subscribers
1.67K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ኢሬቻ - ፈጣሪ ለድንቅ ሥራው የሚመሰገንበት በዓል

መስከረም 24/2017

"ኢሬቻ" ማለት ፈጣሪን (ዋቃ)ን ማመስገን ማለት ነው። ኢሬቻ ለምለም እና እርጥብ ሳር ተይዞ ፈጣሪ (ዋቃ) የሚመሰገንበት ሆኖ የበረከት፣ የመብዛት እና የመፍካት ሕይወትን የሚያመላክት ነው።

በዓሉ የምስጋና፣ የሰላም እና የይቅርታ መገለጫ ተደርጎም ይወሰዳል። የተጣላ ታርቆ፣ ቂሙን ትቶ በንፁህ ልቦና ፈጣሪ ንፁህ ወዳደረገው የውኃ አካል ይኬዳል።

ኢሬቻ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ከክረምቱ የዝናብ፣ የብርድ እና የጨለማ ወቅት ወደ ብርሃናማው በጋ እንዲሁም ከዘመን ወደ ዘመን በሰላም ላሸጋገረው ፈጣሪው (ዋቃ) ምስጋና የሚያቀርብበት ትልቁ በዓሉ ነው።

በዓሉ መስከረም መጨረሻ ላይ የሚከበር ሲሆን የኦሮሞ ሕዝብም ፈጣሪ (ዋቃ) ለሰጣቸው በረከት እና ላደረገለት ምሕረት ምስጋና የሚያቀርብበት ነው።

ማኅበራዊ ደረጃ እና የዕድሜ ልዩነት ሳይፈጠር የኦሮሞ ሕዝብ የኢሬቻ በዓልን ለዘመናት በጋራ ሲያከብር እንደቆየ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ማኅበረሰቡ ከየአካባቢው ተጠራርቶ በአካባቢው ወደሚገኝ ወንዝ (ውኃማ ስፍራ) በመትመም ለፈጣሪው (ዋቃ) ምስጋና ያቀርባል። እነዚህ የውኃ አካላት የተቀደሱ ናቸው ብሎም ያምናል።

በበዓሉ ላይ ከመቶ ሺዎች በላይ የሚሆኑ የኦሮሞ ተወላጆች፣ ከሌሎች ክልሎች የሚመጡ ታዳሚዎች፣ ቱሪስቶች እና የተለየዩ የብሔረሰብ ተወካዮች ይሳተፋሉ።

በዓሉ በአዲስ አበባ፣ በቢሾፍቱ እና በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት እና በተለያዩ ሥርዓቶች ይከበራል። በተጨማሪም፣ የኦሮሞ ዳያስፖራ አባላት በሚገኙበት የተለያዩ የዓለም ሀገራትም ጭምር በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል።

በቢሾፍቱ ሆረ ሀርሰዲ እና በአዲስ አበባ ሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓላት ላይ የሚሳተፉ ታዳሚያን እርጥብ ሳር በእጃቸው በመያዝ ወደ ሐይቁ ዳርቻ በመጠጋት ለምለሙን እና እርጥቡን ሳር በውኃ እየነከሩ ራሳቸው ላይ ይረጫሉ፤ አንዳንዶች ደግሞ ውኃ ውስጥ ገብተው ይጠመቃሉ።

ኢሬቻ የገዳ ሥርዓት አንዱ አካል ሲሆን በኦሮሞ ማኅበረሰብ ዘንድ ለዘመናት ሲከበር መቆየቱ ይነገራል።

“ሆረ ፊንፊኔ” የኢሬቻ በዓል ከ150 ዓመታት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ሲከበር እንደቆየ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ይህ በዓል በተለያዩ ተፅዕኖዎች ምክንያት ተቋርጦ የቆየ ሲሆን ከ150 ዓመታት በኋላ በ2012 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ዳግም መከበር ጀምሯል።

በዓሉ ላይ አባ ገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎች እና ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፋሉ።

በጥቅሉ የኢሬቻ በዓል የኦሮሞ ሕዝብ የደረሱ አዝዕርት፣ አትክልት እና ፍራፍሬዎችን ለመሰብሰብ ዝግጅት የሚደረግበት እና በዚህም ሕዝቡ ደስታውን የሚገልጽበት ነው።

ኢሬቻ ፈጣሪ (ዋቃ) የሚመሰገንበት ብቻም ሳይሆን የኦሮሞ ሕዝብ አዲሱን ብርሃናማ ዓመት በደስታ የሚቀበልበት በመሆኑ ሁሉም ቤተሰቦች፣ ጓደኛማቾች እና ዘመድ አዝማድ ከያሉበት ተጠራርተው በአንድነት፣ በፍቅር እና በደስታ የሚያከብሩት በዓል ነው።

በበዓሉ ላይ ልጃገረዶች እና ጎረምሶች በባህላዊ ልብስ አጊጠው ባህላዊ ጭፈራ እያሳዩ ይደሰታሉ፤ የተለያዩ ባህላዊ ዘፈኖችን እየተቀባበሉ ያሰማሉ።

በተለይም ምስጋና ወደሚያቀርቡበት ውኃማ ስፍራ ሲያቀኑ የተለያዩ ጣዕም ያላቸውን ባህላዊ ዜማዎች ያዜማሉ፤ በዚህም ለፈጣሪያቸው ምስጋናን ያቀርባሉ። በበዓሉ ላይ ወንድማማችነት፣ እርቅ እና ሰላምም ይንፀባረቅበታል።

ኢሬቻ ከበዓልነቱ ባለፈ በርካታ ቱሪስቶች የሚታደሙበት እንደመሆኑ የአገርን ገጽታ ከመገንባት ባለፈ ለምጣኔ ሀብት ዕድገት ያለው ጠቀሜታ የጎላ እንደሆነ ይነገራል።
👍41
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሆረ ፊንፊኔ ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን ገልጸዋል::

የሆረ ፊንፊኔ በዓል በስኬት መጠናቀቅ የአባገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች እንዲሁም የከተማችን ነዋሪዎች ላበረከቱት አስተዋጽዖ ከንቲባ አዳነች አመስግነዋል::

በተጨማሪ በከተማዋ የሚገኙ ሆቴሎች እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ቀን እና ምሽት በቂ አቅርቦት እና አገልግሎት ለእንግዶቹ በመስጠት ለበአሉ በድምቀት መጠናቀቅ ትልቅ ድርሻ የተጫወቱ መሆኑን የገለጹት ከንቲባ አዳነች በ5ቱም በር ያለው የከተማችን ነዋሪ የወንድማማች እና እህትማማች መንፈስን ተላብሶ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት እንግዶቹን በፍቅር መቀበሉን ጨምረው ገልጸዋል::

ከንቲባ አዳነችች አቤቤ በዓሉ በድምቀቅ እንዲጠናቀቅ አስተዋፅዖ ያበረከቱ የከተማችን ነዋሪዎችን፣ ወጣቶችን፣ የጸጥታ አካላትን እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የከተማ አስተዳደሩን አመራሮች አመስግነዋል::
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የተሻሻሉ የቅጣት እርከኖችን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ ከተማን በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ፣ጽዱና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የአረንጓዴ ስፍራዎች ፣ፓርኮች መንገዶች እና የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እየተገነቡ ይገኛሉ፡፡

ይህንን ተከትሎ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነትና የልማቶቹን ዘላቂነት ለማስቀጥል ያግዛሉ የተባሉ አዳዲስ ደንቦች ይፋ ተደርገዋል፡፡

ደንቦችን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና የአዲስ አበባ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ በጽዳትና ተያያዥ ህገ-ወጥ ተግባራት ዙሪያ ቀድሞ ሲጠቀምበት በነበረው ደንብ ቁጥር 150/2015 ላይ የነበረውን የቅጣት እርከኖቹን በማሻሻል ወደ ተግባር መግባቱን ተናግረዋል።

የቅጣት እርከኖቹን ለህብረተሰቡ ዝርዝር መረጃ በመስጠት በመረጃ እጦት ለቅጣት እንዳይዳረግ ግንዛቤ መፍጠር ይገባል ብለዋል።

በዚህም ከ2ሺ ብር እስከ 100ሺህ ብር የቅጣት እርከኖች በግለሰቦችና በተቋማት ላይ መጣሉን ተናግረዋል።

በዚህም መሠረት :-

*ማንኛውም ሰው ያመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ በግቢው ውስጥ በአግባቡ አለመያዝ፤በዓይነት አለመለየት፤ ማዝረክረክ፤ ለጤናና የአካባቢ ገጽታ በሚጎዳ መልኩ ማከማቸት፤ ለግለሰብ 2 ሺህ ብር ለድርጅት 50 ሺህ ብር

*ማንኛውም የጽዳት አገልግሎት ሰጭ ድርጅት/ማህበር ደረቅ ቆሻሻ ሲሰበስብ ገጽታ ካበላሸ 25 ሺህ ብር

*በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ለደንበኛው ተገቢውን አገልግሎት ካልሰጠ 50 ሺ ብር

*ከጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ እውቅና ውጭ የአገልግሎት ክፍያ ከደንበኛው ከተቀበለ 50 ሺ ብር

*ጊዜያዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስቀመጫ ቦታዎችን እስከ 5 ሜትር ዙሪያ ድረስ ጽዱ ካላደረገ 50 ሺ ብር

* ማንኛውም በመንገድ የሚንቀሳቀስ ሰው የሲጋራ ቁርጥራጭ፣ የሶፍት ወረቀት፣ ፌስታል፣ የጫት ገለባ፣ የፍራፍሬ ተረፈ-ምርቶች፣የትራንስፖርት ቲኬት፣የሞባይል ካርዶችን፣ የማስቲካና ከረሜላ ሽፋኖች፣ የመሳሰሉት ጥቃቅን ደረቅ ቆሻሻን ባልተፈቀደ ቦታ ወይም በፓርኮች፣ በአረንጓዴ ቦታ፣ በኮሪደር ከጣለ 2 ሺ ብር

*ከመኖሪያ ቤት ወይም ከድርጅት ግቢ ውጭ ያለውን የአካባቢ ንጹህና አረንጓዴ አድርጎ አለመጠበቅ ከመኖሪያ ቤት አጥር ግቢ ውጭ እስከ 5 ሜትር ርቀት አለማጽዳት፤20 ሺ ብር

*ከድርጅት/ተቋም አጥር ግቢ ውጭ እስከ 10 ሜትር አለማጽዳት፤ 100 ሺ ብር

*ወቅታዊና ልዩ ዝግጅት አከናውኖ በዓሉ ሲጠናቀቅ በዕለቱና ወዲያው ዝግጅቱ የተከናወነበትን አካባቢ ከቆሻሻ ያላጸዳ የፕሮግራሙ አዘጋጅ፤ 50 ሺ ብር

*ዓመታዊ፤ ወርሃዊና ሳምንታዊ የእምነት በዓላት ሲከናወኑ ዝግጅቱ ሲጠናቀቅ የዝግጅቱ ባለቤት በዕለቱና ወዲያው አካባቢውን ካላጸዳ፤20 ሺ ብር የሚቀጡ መሆኑም ተመላክቷል ።
👍3
በሩብ ዓመቱ በእቅድ መሰረት ቀን ከሌት በመስራት ውጤት ውጤታማ ስራዎች መሰራቱ ተገለፀ

መስከረም 26/2017 ዓ.ም
*አዲስ አበባ*

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የልደታ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤቱ በ2017 በጀት የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀሙ ገመገ።

በመድረኩ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ፣የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፣ የባለስልጣኑ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፍሁን አሉላ እና የክ/ከተማው የፅ/ቤቱ ሃላፊ እና ሌሎች አመራሮች እንዲሁም ጠቅላላ የክፍለ ከተማው ኦፊሰሮች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የልደታ ክፍለ ከተማ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ያለፉትን የአደባባይ በዓላት ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቁ እቅድ በማውጣት ውይይት በማድረግ እንዲሁም ከተለያዮ የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት የደንብ ማስከበር ፅ/ቤቱ በርካታ ስራዎች በአግባቡ ስራችሁን ስለተወጣችሁ ውጤት ተገኝቷልና እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በበኩላቸው ባለስልጣኑ በከተማ አስተዳደሩ ኃላፊነቶች ተሰቶት እየሰራ የሚገኝ ተቋም መሆኑን ገልፀው ያለፉትን የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት ላይ እንዲሁም በልማት ኮሊደር ስራዎች ላይ የሰራናቸው ስራዎች ይበል የሚያሰኙ መሆናቸውን ገልፀው በቀጣይም በደንብ መተላለፎች በመከላከሉም ረገድ የተሻለ ለውጥ ለማምጣት በዚሁ ትጋት ልንሰራ ይገባል ብለዋል።

በእለቱ ልደታ ክፍለ ከተማ ለነዋሪዎች ውብ፣ ፅዱ እና ምቹ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልፀው፤ባሳለፍነው ሩብ ዓመት የደንብ መተላለፎችን ከመቀነስ አንፃር እቅድ ይዘን ቀን ከሌት በመስራት ውጤት መገኘቱና ለቀጣይ ወራት ስራዎች ለማሳካት እቅድ ከማቀድ ጀምሮ የቅድመ ዝግት ተግባራት መከናወኑ የተናገሩት የፅ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ካሴ ናቸው ።

በእለቱ የፅ/ቤቱን የሩብ አመት አፈፃፀም በሰነድ የቅድመ መከላከል እና ስልጠና ስራዎች አስተባባሪ አቶ ሙሉቀን እንየው የቀረበ ሲሆን በሰነዱ ላይ ውይይት ተካሂዷል።

በመጨረሻም ጉልህ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላትና ፅ/ቤቱ ለሚያሳድጋቸው ልጆች የምስጋና እና ስጦታ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።

ዘገባው:- አዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍3