የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.15K subscribers
1.96K photos
5 videos
1 file
55 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ ወቅቱን መሠረት ያደረገ የደንብ መተላለፎች ለመቆጣጠር የሚቻልበት ስልቶች በመንደፍ ውይይት አካሄደ ።

ህዳር 29/2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ወቅቱን መሠረት ያደረገ የደንብ መተላለፎች መቆጣጠር የሚቻልበት ስልቶች በመንደፍ ከ11ዱንም የክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ።

በውይይት መድረኩ የደንብ መተላለፎችን መቆጣጠር እንዲቻል በባለስልጣኑ የተነደፈው ስልት በሰነድ የባለስልጣኑ የቁጥጥር፣ክትትል፣እርምጃ አወሳሰድ እና ሰርቪላንስ ዳይሬክቶሬት አቶ ግሩም ወ/መስቀል የባለስልጣኑ እና የክፍለ ከተማ አመራሮች በተገኙበት አቅርበዋል።

በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና-ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደገለፁት ህገ-ወጥ ስራ ሰርተው እርምጃ የተወሰደባቸው ባለሀብቶች እና ደላሎች በመቀናጀት የተቋሙን ስም በማጥፋት ላይ መሆናቸውን በመግለፅ አመራሩና ሰራተኛው በህገ-ወጦች ወሬ ሳይዘናጋ በቁርጠኝነት ህገወጦችን የመከታተል እና የመቆጣጠር ስራው ማጠናከር እንዳለበት ገልፀዋል።

ዋና ስራ አሰኪያጁ አክለውም የሚሰራ ሰው ወቀሳ አያጣውም የኛ ተግባር ከህገ ወጦች ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ በመሆኑ ከህገ- ወጦች መቼም ምስጋና አንጠብቅም ለማህበረሰባችን ጥቅም ሁሌም ታማኝ መሆን አለብን ብለዋል።

በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ ለተቋማችን የተሠጠውን ትኩረትና ተልዕኮ በመረዳት ተልዕኮአቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው ለክፍለ ከተማ አመራሮች አሳስበዋል።

የተነደፈው ስልት በቀጣይ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች እንደ አካባቢው ሁኔታ በታቀደው መሠረት ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል።

ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማዎች ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ!

ዘገባው፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
ባለስልጣኑ ደንበኞችን መሠረት ያደረገ አገልግሎት ለመስጠትና የሠራተኞችን ቤተሰባዊነት ለማጠናከር የሰኞ ማለዳ ውይይትና ሰራተኛው በጋራ ቁርስ የመመገብ ተግባር አስጀመረ።

ታህሳስ 01/2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ፕሮግራሙ ሲያስጀምሩ እንደገለፁት አመራሩን እና ሰራተኛው በህብረት በመሰብሰብ በጥሩ የስራ መንፈስ ሰኞ ቀን ስራዎችን ለመጀመር እንዲያስችል እና ባለጉዳይን በፈገግታና በመልካም ስነምግባር ለማስተናገድ ሲባል የተዘጋጀና ተግባሩ ከከንቲባ ጽ/ቤት ተሞክሮ የተወሰደ መሆኑ ገልፀዋል።

በፕሮግራሙ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጁ ሻለቃ ዘሪሁን የህይወት ተሞክሮ እና የስራ ልምዳቸውን አነቃቂ በሆነ መንገድ ለሠራተኛው አካፍለዋል።

በቀጣይም በየሳምንቱ ሰኞ ማለዳን ስራ ከመጀመር በፊት በመገናኘት በዚሁ መልካም መንፈስ ሠራተኛው ወደ ስራው እንዲሠማራ ለማድረግና ደንበኞችን መሠረት ያደረገ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚሠራ ምክትል ስራ አስኪያጁ አቶ ደሳለኝ ፉፋ ገልፀዋል።

የተቋሙ ሰራተኞች በተግባሩ መደሰታቸውና የተቋሙ አመራር እና ሰራተኛው ተቀራርበው እንዲሰሩ የሚያግዝ መሆኑ ገልፀዋል።

በእለቱ የተቋሙ አመራሮች እና ሰራተኞች በጋራ ቁርስ በመመገብ የስራ ሰዓት ከመድረሱ ወደ ስራ ገበታቸው ተሠማርተዋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
ህገ-ወጥ እርድ በማካሄድ በነበሩ ግለሰቦች ላይ ላይ እርምጃ ተወሰደ።

ታህሳስ 01/2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ **

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ቄራ በረት አካባቢ ከንጋቱ 11:30 ሰዓት ላይ የደንብ ማስከበር አባሎች ከማህበረሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሠረት ከፖሊስ አባላት ጋር በመሆን በህገ-ወጥ መንገድ ሶስት በሬዎች በመኖሪያ ቤታቸው ግቢ ውስጥ እርድ ሲያከናውኑ ተገኝተው 735 ኪሎ ግራም ስጋ እንዲወገድ ለቄራ ድርጅት ገቢ መደረጉን የወረዳው የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ወረደ አቸነፍ ገልፀዋል።

እርዱ እያስፈፀመ በነበረው ግቢ ግለሰቦቹ በተደራጀ መንገድ መረጃ የሚናገር ሰው ከውጭ በማስቀመጥ የደንብና የፖሊስ አባላት ሲርስባቸው የስጋ አከፋፋዩና አራጆቹ ስጋውን ጥለው የተሰወሩ ሲሆን የግቢው ባለቤት ላይ በደንብ ቁጥር 150/2015 መሠረት 15,000 ብር በመቅጣት ባመለጡት ላይ ከፖሊስ ጋር በመሆን ክትትል እየተደረገ መሆኑ የወረዳው የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሽፍት አስተባባሪ አቶ ገመቹ ቡርቃ ገልፀዋል።

በተያያዘ ዜና በአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር የኮልፌ ቀራኒዪ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ውስጥ በተልምዶ ልዩ ቦታው 2 ቁጥር ማዞሪያ /ቆሬ/ አካባቢ ህገ ወጥ የእንስሳት እርድ ሲፈጽም የነበረው ድረጅት ላይ በደንብ ማስከበር ቁጥጥር ኦፊሰሮች ክትትል በማድረግ ተይዟል።

ድርጅቱ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ከመድረሳቸው በፊት 1 በሬ በህገወጥ መንገድ አርደው በኩርቱ ፌስታል በማድረግ ወደ ድርጅታቸው ሊከፋፈል የነበረ 91 ኪሎ ግራም ስጋ ወደ ለቄራዎች ድርጅት እንዲወገድ ያስረከቡ መሆኑን የኮ/ቀ/ክ/ከ/ የወረዳ 01 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መላኩ ደጀን ተናግረዋል።

ድርጊቱ ሲፈፅም የነበረ ድርጅት ቤቱን እንዲታሸግ በማድረግ 15000/አስራ አምስት ሺህ/ ብር እንዲቀጣ ተደርጓል።

የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ብቻቸውን ያለህብረተሰቡ አጋዥ በድብቅ እና በስውር ስፍራዎች ሁሉ የሚደረጉ ህገወጥ ተግባራት ሁሉ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ስለሆነ ህብረተሰቡ ጤንነቱን ያልተረጋገጠ ስጋ በማቅረብ የህብረተሰቡን ጤና ችግር ውስጥ የሚጥሉ ግለሰቦችን እና ድርጅቶችን በማጋለጥ ማህበራዊ ሀላፊነቱን እንዲወጣ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥሪውን ያቀርባል።

ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማዎች ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ!

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
በሕዝብ ንቅናቄ መድረክ ከህብረተሰቡ በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ከአጠቃላይ ኦፊሰሩ ጋር ውይይት ተካሄደ።

ታህሳስ 02/2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ **

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በሁሉም ክፍለ ከተማዎች ባካሄደው የህዝብ ንቅናቄ መድረኮች ላይ ከህብረተሰቡ በተነሳው የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችና የተለያዩ አስተያየቶች ላይ ከአጠቃላይ ከባለስልጣኑ ኦፊሰሮች ጋር በአራት ክላስተሮች ውይይት አካሄደ።

በአራቱም ክላስተሮች የውይይት መድረክ በመጎብኘት ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንዳሉት በዛሬው ዕለት ተቋሙ በተለያዩ 4 ክላስተሮች ውይይት እየተደረገ መሆኑን ገልፀው ተቋማችን የህብረተሰብ አገልጋይ ተቋም እንደመሆኑ መጠን ጠንካራ ጎናችንን በማሳደግ ክፍተቶቻችንን የሚሞላ ውጤታማ ውይይት እንደተደረግ ተናግረዋል።

ዋና ስራ-አስኪያጁ አክለውም በተቋሙ የተነሱና መስተካከል የሚገባቸውን ችግሮች ለመፍታትና ከተማ አስተዳደሩ የሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት ባለስልጣኑ በትጋት እንደሚሰራ ተገልጿዋል።

በአራት ክላስተር የተካሄዱትን መድረኮች የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች የመሩት ሲሆን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ክላስተር መድረክ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፣ የጉለሌ ክ/ከተማ ክላስተር መድረክ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ፉፋ የቦሌ ክ/ከተማ ክላስተር መድረክ ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አበባ እሸቴ እና የቂርቆስ ክ/ከተማ ክላስተርን መድረክ የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ መርተውታል።

በመድረኩም በህዝብ ንቅናቄ መድረኮች ላይ ከህብረተሰቡ በተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች መሠረት የውይይት መነሻ ሰነድ ተዘጋጅቶ ቀርቧል።

በሰነዱም ከህብረተሰቡ የተነሱና ተቋሙ መፍታት ካለበት ጥያቄዎች መካከል ለአብነት የደንብ መተላለፍና ተያያዥ ህገ-ወጥ ተግባራት ከመከሰታቸው በፊት አስቀድሞ ከመከላከልአንፃር፤የቅድመ ግንዛቤ ስራዎች ላይ ለውጥ ሊያመጣ በሚችል መሌኩ ከመስራት አንፃር፣ በሁሉም የደንብ መተላለፎችና አከባቢዎች ላይ ወጥ በሆነ መልኩ በዘላቂነት እርምጃ አለመውሰድና በአንዳንድ ኦፊሰሮች ላይ የሚታይ የስነ-ምግባርና ችግሮች ዙሪያ ይገኙበታል።

የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጁ አቶ ደሳለኝ ፋፉ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከጊዜ ወደ ጊዜ እራሱን እያሻሻለ እና የከተማዋን ችግር ለመፍታት ሌት ተቀን እየሰራ ያለ ተቋም ነው፤ ለዚህም ኦፊሰሩ ትልቅ ድርሻ አለው፤ህዝብ የሰጠንን አደራ እና ኃላፊነት በመልካም ስነምግባር እንዲሁም በእውቀት በመምራት የህዝብ አገልጋይነታችን በተግባር ልናረጋግጥ ይገባል ብለዋል።

የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ከህብረተሰቡ የተነሱ ችግሮችን በአግባቡ በመወያየትና በመግባባት በባለስልጣኑ መፈታት ያለባቸውን ችግሮች በመለየት እና መፍትሔ በመስጠት ህብረተሰቡ በባለስልጣኑ ላይ ያለውን ተቀባይነት እንዲጨምር በማድረግ በጋራ አብሮን ሚሰራበትን መንገድ በማመቻቸት በከተማችን የሚታየዉን የደንብ መተላለፍና ተያያዥ ህገወጥ ተግባራት እንዲቀንስ በማድረግ ከተማችንን ውብ እና ለነዋሪዎች ምቹ ማድረግ ይገባናል ብለዋል ።

የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ በማጠቃለያ ንግግራቸው ለተቋሙ በአዋጅ የተሰጡትና በዋናነት የምናከናውናቸው በዘጠኙ የደንብ መተላለፎች በመከታተል እና በመቆጣጠር በህጋዊ መንገድ የሚሰራውን ማህበረሰባችን በአግባቡ ለማገልገል ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆን እንደሚገባ ገልፀዋል።

በመድረኮቹ ተቋሙ ከፍተኛ ኃላፊነት በመውሰድ ለኦፊሰሩ ደረጃውን የጠበቀ የደንብ ልብስ በማቅረቡ ኦፊሰች ከፍተኛ ምስጋናው አቅርበዋል።

በመጨረሻም በአራቱም መድረኮች ኦፊሰሮች በርካታ ሀሳቡና አስተያየቶች ያነሡ ሲሆን በባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የቀጣይ ስራ የትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኮቹ ተጠናቀዋል።

ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማዎች ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ!

ዘገባውየአዲስ :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
"የዘመነ የንግድ ስርዓት፣ ለላቀ ገቢ እድገት!"
------------
በተቀናጀና ንቁ የህዝብ ተሳትፎ በከተማችን ፍትሃዊ እና ዘመናዊ የንግድ ስርዓት እናሰፍናለን!’

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች " የዘመነ የንግድ ስርዓት፣ ለላቀ ገቢ እድገት!" በሚል መሪ ሀሳብ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

በንግዱ ዘርፍ የታዩ ለውጦችና የንግዱ ማህበረሰብ ሚና የመድረኩ ዋና የውይይቱ አጀንዳ ሲሆን ሀገራችን እና ከተማችን ባስመዘገቡት ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ስኬቶች እና እያጋጠሙ ባሉ ፈተናዎች ዙሪያ ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር መግባባት ላይ ተደርሷል።

የንግዱ ማህበረሰብ አስተዳደሩ ያስቀመጣቸውን ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት እንቅፋት የሆኑ ተግዳሮቶችን በመገንዘብ ችግሮቹን ለመፍታት በሚደረገው ጥረትም የበኩላቸውን አስተዋፆኦ ለማበርከት ከምንም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

ህግንና ሥርዓትን አክብረው የሚነግዱ ነጋዴዎች በሀገር ልማት ላይ ያላቸውን አዎንታዊ ሚና በተገቢው በመገንዘብ ህገወጥ ንግድን በመከላከል ላይ የድርሻቸውን ሚና እንዲጫወቱም መልዕክት ተላልፏል፡፡

መረጃው፦ የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ነው።
ባለስልጣኑ ልምዱን እና ተሞክሮውን ለልዑካን ቡድን አጋራ!

ታህሰስ 10/2016 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመራሮች በሰነድ በተደገፈ መረጃ ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ልዑካን ቡድን በተቋም አደረጃጀት፣በአሰራር፣ በመመሪያ ዝግጅት ፤በሰው ሃይል አደረጃጀት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በተመለከተ ባለስልጣኑ ያለውን ልምድና ተሞክሮ አጋርቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በተሞክሮ ማጋራቱ ወቅት እንተገለጹት ተቋሙ የከተማዋን ገጽታ ለመቀየር የራሱን ድርሻ ለመወጣት በርካታ ስራዎች ማከናወኑን ገልጸው በዚህም ውጤት መገኘቱን በመግለጽ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ከዚህ ልምድ በመውሰድ እና ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ አደረጃጀት መፍጠር እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

ዋና ስራ አስኪያጁ ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ተቋሙ በሚያደርገው ልማታዊ የለውጥ እንቅስቃሴዎች በሚችለው ሁሉ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ለልዑካን ቡድኑ ገልታላቿል፡፡

ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ።

ዘገባው :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
በቁማር ቤቶች ላይ የተወሰደው እርምጃ በትምህርት ቤቶች አካባቢ እና ከህግ ውጪ ሲሰሩ የነበሩ መሆኑን ተገለፀ።

ታህሰስ 11/2016 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ጉዳዩን አስመልክቶ ከኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በቆይታቸው በቁማር ቤቶች ላይ የተወሰደው እርምጃ በትምህርት ቤቶች አቅራቢያ ከ200 ሜትር ራዲየስ በታች የቤትንግ ስፖርት ውርርድ በማጫወት እና በውርርድ ቤት ውስጥ ከተፈቀደው ውጪ ቁማር በማጫወት፣ ጫት በማስቃም፣ ሺሻ በማስጨስ እና አልኮል የሚሸጡ መሆኑን ከህብረተሰቡ ከደረሰ ጥቆማ እና በጥናት መረጋገጡ ገልጸዋል።

ዋና ስራ አስኪያጁ አክለውም ከ21 ዓመት በታች የሆኑ ተማሪዎችና ታዳጊዎችን በማወራረድ ተማሪዎች ትምህርታቸው ከማስተጓጎል በተጨማሪ በሌብነት ውስጥ እንዲገቡ ማድረጉ ከህብረተሰቡ በተደረገው ውይይት መነሳቱ ገልፀዋል።

የደንብ መተላለፎችን በተደጋጋሚ ሲፈጽሙ የተደረሰባቸው ከ3240 በላይ የቤቲንግ እስፖርት አወራራጅ ድርጅቶች የማወራረጃ ቤታቸው የማሸግ እርምጃ የተወሰደ መሆኑን እና ደንብ የማስከበር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

በመግለጫቸው በትምህርት ቤቶች አቅራቢያ ከ200 ሜትር ራዲየስ በታች የቤትንግ ስፖርት ውርርድ በማጫወት የተሰማሩ ግለሰቦች የንግድ ዘርፋቸውን በመቀየር በህጋዊ መንገድ የንግድ ስራቸውን እንዲያከናውኑ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም ዋና ስራ አስኪያጁ ህብረተሰቡ መረጃ በመስጠት ላደረገው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።

ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ።

ዘገባው :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
በአዲሱ ደንብ ቁጥር 150/2015 ላይ ለደንብ ማስከበር በጎ ፍቃደኞች ግንዛቤ ተፈጠረ።

ታህሳስ 12ቀ/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከሁሉም ክፍለ ከተማ ለተውጣጡ በጎ ፍቃደኞች በአዲሱ ደንብ ቁጥር 150/2015 ላይ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አዳራሽ ግንዛቤ ሰጠ።

የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅና የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው ለከተማዋ የደንብ መከበር ከፍተኛ አስተዋፅዖ እያበረከታችሁ ያላችሁ የተከበራችሁ የበጎ ፍቃደኞች ተወካዮቻችን እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።

ባለስልጣኑ ባለፉሁት ዓመታት ደንብ ቁጥር 54/2005 ሲያስፈፅም መቆየቱን አስታውሰው፤ አሁን ላይ የከተማዋን እድገት ተከትሎ የሚፈፀመው የደንብ መተላለፍ በመወሳሰቡ ምክንያት ጥናት በማድረግ ደንቡን ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል።

በዛሬው መድረክም ከተቋሙ ጋር አጋር በመሆን ከፍተኛ ሀገራዊ ድርሻችሁን ለምትወጡ በጎ ፍቃደኞቻችን አዲሱን ደንብ 150/2015 በዝርዝር በማስጨበጥ በቀጣይም በላቀ መልኩ የደንብ መተላለፍን በጋራ ለመከላከል እንድንተጋ አደራ እያልኩኝ፤ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፉ በህዝብ ንቅናቄ መድረክ፣ ቤት ለቤትና ቡና በጠጡ እንዲሁም በትምህር ቤትና በሞንታርቦ የሚሰጠውን ግንዛቤ አጠናክሮ በማስቀጠል የደንብ መተላለፍና ህገ-ወጥ ተግባራትን ይከላከል ብለዋል።

አዲሱን ደንብ ቁጥር 150/2015 ሰነዱን የግንዛቤ ማስጨበጥ ባለሙያ ወ/ት አስናቁ አየሁ በዝርዝር አቅርበዋል።

ተሳታፊ በጎ ፈቃደኞችም ደንቡ የሚያሰራና ለሁሉም ህብረተሰብ ማስጨበጥ እንደሚገባ ጠቁመው፤ ከፅዳትና ተያያዥ ጉዳዮች ጋርም እንደ በጎ ፍቃደኛ በተጨባጭ ለውጥ ያመጣ መሆኑን ተናግረዋል።

በጎ-ፈቃደኞቹ ከሽንት ጋር በተያያዘ ቅጣቱ እንዳለ ሆኖ የሚመለከተው አካል የህዝብ መፀዳጃ ቤትን ማስፋት ላይ መስራት እንደሚገባ፤በትምህርት ቤቶች አከባቢ የሚሰጡ የንግድ ፍቃድ ላይ በምንሰጠው ጥቆማ መሠረት በአስቸኳይ እርምት ሊወሰድ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አበባ እሸቴም ተቋሙ ያለ ህብረተሰቡ እና በጎ ፍቃኞች ተሳትፎ በከተማዋ የሚስተዋለውን የደንብ መተላለፍ መከላከል አይቻልምና በቀጣም በተጠናከረ መልኩ ለመስራት እኛም የምትጠቁሙን እና የምትሰጡንን አስተያየት ተቀብለን በጋራ የደንብ መተላለፍና ህገ ወጥ እንቅስቃሴ እንከላከላለን ብለዋል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
ባለስልጣኑ በማህበራዊ ሚድያ አጠቃቀም ዙሪያ ለተቋሙ ሰራተኞች ስልጠና ሰጠ።

ታህሰስ 12/2016 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የማህበራዊ ሚድያ አጠቃቀምን በተመለከተ ለተቋሙ የማዕከል ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ስልጠናው ማህበራዊ ሚድያን ተገቢ በሆነ መንገድ እንድንጠቀምና የተሻለ የመግባባት ክህሎት እንድናዳብር አቅም እንደሚፈጥር ተናግረዋል ።

አክለውም በዚህ ዘመን ማህበራዊ ሚድያ ያለው አቅም ከፍተኛ እንደመሆኑ በአግባቡ የማንጠቀም ከሆነ ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ፣ፖለቲካዊ እና ስነልቦናዊ ጉዳት እንደሚያስከትል በመገንዘብ የምንጠቀማቸውን ማህበራዊ ሚድያዎች በጥንቃቄ ልንጠቀምባቸው እንደሚገባ ገልፀዋል ።

በማህበራዊ ሚድያ አጠቃቀም እና በአግባቡ ካልተጠቀምን የሚያመጣው ተጽዕኖ ዙሪያ የተዘጋጀውን ስልጠና የባለስልጣኑ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሲኒየር ባለሙያ በሆኑት በአቶ ሚሊዮን ካሳሁን የተሰጠ ሲሆን የማህበራዊ ሚዲያ ምንነት፣ አይነቶች ፣ የማህበራዊ ሚዲያ መቼ እና ለምን አላማ መጠቀም አንደሚገባ እንዲሁም ኃሰተኛ መረጃዎችን አንዴት በቀላሉ ማወቅ እንደሚቻል በዝርዝር አስረድተዋል ።

የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በስልጠናው ማጠቃለያ ንግግራቸው አንደተናገሩት በተለያዩ የአለም ክፋሎች በዚህ ሰዓት ብዙ ቴክኖሎጂ አየተጠቀሙ መሆኑ በመግለፅ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀሙን በመገንዘብ ለመልካም ነገሮች ስንጠቀም ለሰው ልጆች ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል ።

በተጨማሪም የተቋሙ ሰራተኞች የባለስልጣኑ የሶሻል ሚዲያ ገጾች አባል እና ተከታይ በመሆን በተቋሙ በሚሰሩ ስራዎች ሀሳብና አስተያየት መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በመጨረሻም ከስልጠና ተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች በባለሙያው ምላሽና አስተያየት በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል ።

ዘገባው ፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዛሬ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል የሆነውን የጨበራ ዝሆን ዳና ሎጅን መርቀው ከፍተዋል።

በዚሁ ጊዜ የተገኘው እውቁ ዓለም አቀፍ ሼፍ ማርከስ ሳሙኤልሰን፤ የተሰራው ሎጅና በአካባቢው ያለው የተፈጥሮ ኃብት እጅግ የሚደንቅ መሆኑን ተናግሯል።

በአካባቢው ያለው መልክዓ-ምደር፣ የእንስሳት ኃብት እንዲሁም ሌሎች የሕዝቡ ባህል ለሀገሪቱ የቱሪዝም ዘርፍ እድገት ትልቅ ኃብት እንደሚሆን ነው የገለጸው።

ኢትዮጵያ ውስጥ ለቱሪስት መዳረሻነት የሚውሉ በርካታ ሥፍራዎች መኖራቸውን ገልጾ እነዚህን ሥፍራዎች ይበልጥ አልምቶ መጠቀም እንደሚገባ ጠቁሟል።

የኢትዮጵያ የዳያስፖራ አባላት በውጭ ሀገራት ኢትዮጵያን ለተቀረው ዓለም በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማድረጋቸውን ጠቁሟል።

አሁን ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ የዳያስፖራው አባላት ወደ ሀገራቸው በመምጣት ያላቸውን ልምድና ክህሎት ማካፈል አለባቸው ብሏል።

የሼፍ ማርከስ ሳሙኤልሰን ባለቤት ማያ ኃይሌ በበኩሏ፤ የጨበራ ዝሆን ዳና ሎጅ የሚገኝበት ሥፍራና እንዲሁም የተሰራው ሎጅ ሳቢ መሆኑን ገልጻለች።

የዳያስፖራው አባላት አሁን ላይ ወደ አገራቸው መጥተው ለሀገራቸው እድገት የበኩላቸውን መወጣት አለባቸው ማለቷን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

መረጃው:- የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ታህሳስ 12//04/2016 ዓ.ም ሊሰጥ ለነበረው የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተና ለመፈተን በስፍራው ለተገኛችሁ እና የከተማ አስተዳደሩን አቅጣጫ በፍፁም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በመቀበል ውሳኔውን ላከበራችሁ ሰራተኞች በሙሉ የላቀ ምስጋናውን እያቀረበ ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ ጠይቋል።

በቀጣይም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ፈተና ቅዳሜ ታህሳስ 20/04/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑንም ቢሮው አስታውቋል።

የከተማ አስተዳደሩ የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተና ለአመራሮች ፣ ለባለሙያዎች እና ለሰራተኞች ፈተና እንዲሰጡ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ኃላፊነት በመስጠት ባሳለፍነው ሳምንት አርብ ቀን ማለትም በ 12/04/2016 ዓ.ም ፈተና ለመፈተን ሙሉ ዝግጅቱን ቢያጠናቅቅም ፈተናው የ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ባጋጠመው ቴክኒካል ችግር ምከንያት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ አይዘነጋም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን በእለቱ ከረፋዱ 5:00-11:30 በፍጹም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እና በትእግስት የፈተናውን መሰጠት ስትጠባበቁ ለነበራችሁ የ ከተማ አስተዳደሩ ሰራተኞች በሙሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የላቀ ምስጋናውን እያቀረበ ነገር ግን በእለቱ በሰራተኛው ላይ ለደረሰው መጉላላት እና እንግልት ሁሉ ይቅርታ ጠይቋል።

በተያያዘም ተፈታኞች በተረጋገጠ ሰላም አና በተረጋጋ ስሜት ፈተናውን እንዲወስዱ የተለመደ ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን ላሳየው እና የሰላም አርበኛ ለሆነው የመንግስት ሰራተኛ በሙሉ ቢሮው ምስጋናን አቅርቧል።

በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩን አቅጣጫ በመቀበል የትራንስፖርት አቅርቦት በማመቻቸት፣የትራንስፖርት ፍሰቱን በማሳለጥ እና ሰላም እና ፀጥታን በማስጠበቅ ሙሉ ድጋፍ ላደረጋቸው ባለድርሻ አካላት በሙሉ ቢሮ ከፍ ያለ ምስጋናውን አቅርቧል።

በቀጣይም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ፈተና ቅዳሜ ታህሳስ 20/04/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን እያስታወቀ ተፈታኞች ከዚህ ቀደም በ ኦረንቴሽን ወቅት የተቀመጡ መስፈርቶችን በሙሉ አሟልተው ለፈተና እንዲገኙ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል።

በተመሳሳይም የተዘጋጀው ፈተና በቴክኒክ ችግር ምክንያት በመሰረዙ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይቅርታ መጠየቁም አይዘነጋም።

መረጃው:-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ነው።
ለአራት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቀቀ።

**አዲስ አበባ**
16/04/2016 ዓ.ም

"ከእዳ ወደ ምንዳ" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ የፕብሊክ ሰርቪስ እና የፍትህ ልዩ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ አባላት ለተካታተይ አራት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል፡፡

ስልጠናው በሃብት ፈጠራ፣ በገዢ ትርክቶች፣ በሰላም እሴት ግንባታ፣ በአገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቫንት ግንበታ እና የሰላም ባህልን አመለካከት የመገንባት እና የመምራት ክህሎት ጉዳዮች በተመለከተ ውጤታማ ስልጠናዎች ተሰጥተዋል፡፡

ስልጠናው ሲጠናቀቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፍት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ የተኙ ሲሆን አባላቱ ከልዩነት ይልቅ የጋራ የሚያደርጉንን ገዥ ትርክቶችን በማንፀባረቅ ሕብረ-ብሔራዊ አንድናታችንና ሰላማችንን ማጽናት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

በስልጠናው የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የበሀገራች ብልጽግና ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎች አየተሰሩ መሆኑ በመግለጽ በኢኮኖሚ የበለጸገች ሃገር ለመገንባት በሚደረገው ጥረት አባላቱ የራሱን ድርሻ መወጣት እንዳለበተ አሳስበዋል፡፡

የስልጠናው የተሳታፊ የሆኑ አባላት በበኩላቸው በስልጠናው በቂ ግንዛቤ ማግነታቸውን ገልጸው ሕብረ-ብሄራዊ አንድነትን ለመገንባትና ስልጡን እና ስነምግባር ያለው የሲቪል ሰራተኛ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ሁሉ በቁርጠንነት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም አባላቱ በተሰጠው ስልጠና መሠረት በቀጣይ ተግባራዊ የሚደረጉ ባለ አራት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣትና ለተግባራዊነቱ ቃል በመግባት ስልጠናው ተጠናቋል።

ከስልጠናው መጠናቀቅ በኋላ አባላቱ አንድ ላይ በመሆን የኢትዮጵያ አንድነት ማሳያ የሆነው የአድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት ጉብኝት አድርገዋል።

በጉብኝቱ የአድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት ለኢትዮጵያውያንና የጥቁር ህዝብ ቅርስ እና የአንድነት የጀግንነት ማህተም መሆኑ እና ብ
ማሳያ መሆኑ የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ገልፀዋል፡፡

መረጃው፦ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው ።
በቅርቡ በህገ ወጥ መንገድ ሲሰሩ እርምጃ በተወሰደባቸው የቤቲንግ ቤቶችን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተካኔደ።

ታህሳስ 18/4/2016 ዓ.ም (አዲስ አበባ )

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በቅርቡ በቤቲንግ ስፖርት ቤቶ ላይ የሚስተዋሉ አላግባብ ጸጥታን የሚያደፈርሱ ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጪ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ቤቶች ላይ እርምጃ መውሰዱ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ጉዳዩን አስመልክቶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በራስ አምባ ሆቴል ውይይት ተካኒዷል።

መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በመድረኩ ላይ እንደገለፁት፦አዲስ አበባ ከተማ በየግዜው የኢኮኖሚ ግብይትን በማዘመን የምትታወቅ ከተማ እንደ መሆኗ መጠን በንግድ ና ነጋዴው መካከል ባለው ስርዓት ውስጥ ሀገራዊ ፍይዳው የጎላ መሆኑን ጭምር በመጠቆም ከቅርብ ግዜ ጀምሮ ግን ህግና ስርዓትን ባልጠበቀ መልኩ የሚንቀሳቀሱ ማህበረሰቡ ላይ ማህበራዊ ጫና በመፍጠር ተቀባይነት የሌላቸው እየተበራከቱ ከመምጣታቸው ባሻገር ከተማውን የሁከት ብጥብጥ የጸረ ሰላም ሀይሎች መሰብሰቢያ የተለያዩ የፖለቲካ አጀንዳ ማስፍፊያ እየሆኑ መምጣታቸውን ጠቁመዋል ።
ሀላፊዋ አያይዘውም ህጋዊ ሆነው ስርዓትን ባልጠበቀ መልኩ በሚሰሩ በቀጣይ እርምጃው እንደሚቀጥል በመጠቆም በቀጣይ እርምጃ የተወሰደባቸውን የቤቲንግ ቤቶቹን በተመለከተ መደረግ ስላለበት ጉዳይ አስፈጻሚው አባል የሚሰጠውን አቅጣጫ እናሳውቃለን ሲሉ ተደምጠዋል ።

በጉዳዩ ላይና በቀረበው ሰነድ ላይ ከተሳታፊዎቹ ለቀረበው ሀሳብና አስተያየት ከሚመለከተው አካል ምላሽ ተሰቶበት ውይይቱ ተጠናቋል።

ዘገባው፦የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዩች ነው።