የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.5K subscribers
3.94K photos
13 videos
1 file
93 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ በአራዳ ክፍለ ከተማ ያስገነባው የአቅመ ደካማ ቤት አጠናቆ ለባለቤቶቹ አስረከበ

12/12/2018 ዓ.ም
** አዲስአበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የአራዳ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በስሩ የሚገኙ ወረዳዎችን በማስተባበር በክፍለ ከተማው ወረዳ 04 ለሚገኙ አቅመ ደካማ ነዋሪ መኖሪያ ቤት ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቱ አስረክቧል።

በምርቃቱ መርሐ ግቡሩ የተገኙት የአራዳ ክፍለ ከተማ ም/ስራ አስፈፃሚ አቶ አብዲ ሙሉነህ ደንብ ማስከበር ለከተማው ህዝብ ደራሽ በመሆን የሀገሩን ልማት ለማስቀጠል ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በትጋት እንደሚሰራ በመግለፅ ዛሬም በበጎ ተግባራ በክፍለ ከተማው ላስቀመጠው አሻራ ምስጋና አቅርበዋል ።

በፕሮግራሙ የአራዳ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ኃላፊ ሻምበል ኑርልኝ ገ/ኪዳን የክረምት በጓ ፈቃድ ስራዎች ከሆነው ሰው ተኮር ተግባር የአቅመ ደካማ ቤት በመገንባት በ27 ቀናት ሰርቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቷ ማስረከቡን ገልፀዋል ።

አክለውም የአራዳ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ባሉ 8 ወረዳዎች ከሚሰራቸው የደንብ መተላለፍ መከላከልና መቆጣጠር በተጨማሪ ሰው ተኮር ስራዎች አንዱ የስራው አካል አድርጎ እንደሚሰራ በመጠቆም ለዚህም 1,454,200 ብር በማውጣት የወ/ሮ ከበቡሽ ሸዋ ቤት አፈርሶ መገንባቱን ተናግረዋል ።

ቤቱ የተገነባላቸው ወ/ሮ ከበቡሽ ሸዋ ከ5 በላይ ቤተሰብ ይዘው የሚኖሩበት ቤት ቀደም ሲል ዝናብና ፀሀይ የሚፈራርቅበት የነበረና ለመኖር ፈታኝ እንደነበር በመግለፅ ለተደረገላቸው ነገር ሁሉ ለደንብ ማስከበር ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አበርክተዋል።

በመድረኩ የተሳተፉት የአራዳ ክፍለ ከተማ የበጓ ፈቃድና ህብረተሰብ ተሳትፎ ኃላፊ ወ/ሮ ፀጋነሽ ታምራት ደንብ ማስከበር በክፍለ ከተማው ከተለዮ የአቅመ ደካማ ቤት አንዱ የሆነውን ቤት በአጭር ጊዜ አፍርሶ ከማደስ ባሻገር የተለያዩ ቁሳቁሶችን በማሟላት ለወገን ደረሽነቱን በማስመስከሩ እጅግ የሚበረታታ ነው ሲሉ ገልፀዋል ።
በመጨረሻም ለበጓ አድራጎት ስራው ተሳታፊ ለነበሩ አካለት የምስክር ወረቀት በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡፡፡
4👍2
ባለስልጣኑ በ2019 በጀት አመት የደንብ መተላለፎችን በ54.3 ፐርሰንት ለመቀነስ ማቀዱ ተገለፀ

14/12/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2019 በጀት አመት እቅድ ላይ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከማዕከል ሰራተኞች ጋር የተቋሙ ስኬት በማስቀጠል የደንብ መተላለፎች ለመቀነስ በተነደፉ ስልቶች እና እቅዶች ላይ ውይይት ተደረገ።

በውይይቱን የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በ2019 በጀት አመት የቀደውን እቅድ በትጋትና በቁረጠኝነት በመስራት በከተማችን የደንብ መተላለፍ እንዲቀንስና በተነደፉ ስልቶች እና እቅዶች መሠረት በትጋት በመፈፀም በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት ሁሌም ዝግጁ መሆን እንደሚገባ ገልጸዋል።

የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ በበጀት ዓመቱ የደንብ መተላለፍ የሚፀየፍ ማህበረሰብ ለመፍጠር በርካታ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች እንደሚሰጡና በቴክኖሎጂ በታገዘ የደንብ መተላለፍ በመከላከል በመቆጣጠር በ9 የደንብ መተላለፎች ላይ በ54.3 ፐርሰንት ለመቀነስ መታቀዱ ተናግረዋል።

በቀጣይ ከሁለት ሺህ በላይ አዲስ የፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮችን መልምሎ ስልጠና በመስጠት ወደ ተቋሙ በመቀላቀል እና በስራ ላይ ያሉትን ከ7000 በላይ ነባር የፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰር በማስልጠን የሰው ሃይሉ ለማብቃት እንደሚሰራ በተነደፈው ስልት ተመላክቷል።

በመድረኩ በ2018 በጀት አመት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ዳይሬክተሮች ቡድን መሪዎችና ፈፃሚዎች ምስጋናና እውቅና በመስጠት ለመላው የተቋሙ አመራሮች እና ሰራተኞች ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በከተማ ደረጃ 1ኛ እንዲወጣና ተሸላሚ እንዲሆን ላበረከቱት አስተዋፅኦ ምስጋናና እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
👍121
ባለሥልጣኑ የደንብ መተላለፍ ቁጥጥር አሰራሩን ለማዘመን የመገናኛ ሬዲዮ እና የመስክ ካሜራ ቴክኖሎጂ ግዢ ለመፈፀም ውይይት አካሄደ

15/12 /2018ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በ2019 በጀት ዓመት ቴክኖሎጂን በመጠቀም የደንብ መተላለፎች ለመቀነስ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቱ ለማጠናከር የሚረዱ መሣሪያዎችና አስፈላጊ የደንብ ልብስ ለመግዛት ውይይት አካሄደ።

​የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን የተቋሙ አላማዎችንና ስትራቴጂካዊ ግቦችን ለማሳካት የሚረዱ ግባቶች ግልጽ ቀልጣፋ እና ውጤታማ የግዥ ስርዓት ለመዘርጋት ግባቶች እንደሚገዙ ገልጸዋል።

ተቋሙ የሀብት ብክነትን በማስወገድ፣ በጀትና ጊዜን በቁጠባ በመጠቀም ለአገልግሎት አሰጣጡ አስፈላጊ የሆኑ ዘመኑን መሠረት ያደረጉ ስራን የሚያቃልሉ እና የተሰጠንን ተልዕኮ ለማሳካት የሚረዲ ግባቶች ግዢ በወቅቱና በትክክለኛ ጥራት እንዲገዛ አሳስበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን አሰራሩን ከጊዜ ወደ ጊዜ በማዘመን በዘንድሮ በጀት ዓመት የመገናኛ ሬዲዮ እና የካሜራ ቴክኖሎጂ ግዢ እንደሚፈፀም ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ገልፀዋል።

የተቋሙን የግዢ ፍላጎት እቅድ ያቀረቡት የግዢ ዳይሬክቶሬት ወ/ሮ እፀህይወት ፅጌ በተቋሙ የተጀመረው ከወረቀት ነፃ አገልግሎት ለማስቀጠልና ለማዘመን ከሁሉም የስራ ክፍል ፍላጎት መሰብሰቡን ገልፀዋል።

መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍32