የአደጋ ስጋት ደህንነት ደንብ ቁጥር 132/2014 እና መመሪያ ቁጥር 163/2017 ወደ ሙሉ ትግበራ ሊገባ መሆነ ተገለፀ
ነሐሴ 01/2018ዓ.ም
** አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ደንብ ቁጥር 132/2014 እና መመሪያ ቁጥር 163/2017 ያወጣው በከተማዋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የህንፃዎች ከፍታ፣ የኢንዱስትሪዎች መስፋፋትና የህዝብ ቁጥር እድገት ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመከላከልና የህይወትና ንብረት ደህንነትን ለማረጋገጥ መሆኑ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ደንብና መመሪያው ላይ ለህብረተሰቡ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በቀጣይ ተጠናክረው የሚሰሩ መሆኑን ገልጸው፣ ደንቡን ተላልፈው በሚገኙ አካላት ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ኮማንደር አህመድ መሐመድ በመግለጫቸው እንደተናገሩት የአደጋ ስጋት ደህንነት ደንብ ቁጥር 132/2014 እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአደጋ መከላከል ፣ ቁጥጥር ፣ ፍተሽና ብቃት ማረጋገጥ ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 163/2017 የከተማችንን ህብረተሰብ ህይወትና ንብረት ከአደጋ ስጋት ለመጠበቅ የወጣ ደንብና መመሪያ ነው።
የደንቡ ዋና ዓላማ በከተማዋ ውስጥ አደጋ እንዳይደርስ አስቀድሞ መከላከል እንደሆነ ገልጸው፣ ከዚህ ቀደም አደጋ ከደረሰ በኋላ ይደረግ የነበረውን የመከላከል ተግባር ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ ወደ መከላከል ያሸጋገረ አሰራር መሆኑን አብራርተዋል።
ኮማንደር አህመድ አያይዘውም መመሪያው ተፈጻሚ የሚሆነው በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ መሆኑን በመጠቆም፣ ተቋሙ በከተማዋ የሚገኙ ተቋማትን የሙያና የቴክኒክ ድጋፍ ከመስጠት ባለፈ የፍተሻና ቁጥጥር ስራ በማካሄድ የብቃት ማረጋገጫ (ሰርቲፋይድ) የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል።
በደንቡ መሠረት ማንኛውም የህዝብ መገልገያ ህንፃ፣ የንግድ ተቋም ወይም አደገኛ ንጥረ ነገሮችን የሚያከማች ድርጅት በየዓመቱ ከአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ደህንነት ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የመያዝ እና የማደስ ግዴታ ተጥሎበታል።
ተቋማትና የህንፃ ባለቤቶች ደረጃውን የጠበቀ የውሃ መቅጃ ሀይድራንት (Hydrant)፣ የእሳት ማጥፊያ ሲሊንደሮች፣ የጭስ ማወቂያዎችና የስፕሪንክለር ስርዓት የመገጠም እንዲሁም በህንፃ ዲዛይኖቻቸው ውስጥ የአደጋ ጊዜ ማምለጫ መንገዶችን የማካተት ግዴታ አለባቸው።
የተጣሉ የደህንነት መስፈርቶችን ሳያሟሉ በሚገኙና ህጉን በሚጥሱ አካላት ላይ እንደ ጥፋቱ ደረጃ ከብር 10,000.00 እስከ ብር 100,000.00 የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት የሚጣል ሲሆን፣ በተጨማሪም የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ያላስተካከሉ ተቋማት የንግድና ስራ ፈቃዳቸው እንዲታገድ ወይም እንዲሰረዝ የሚደረግ ይሆናል።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡

👍10❤6👏2
ባለስልጣኑ በከተማው የደንብ መተላለፎች ለመቀነስ የ2019 በጀት ዓመት እቅዱ ለዘርፎችና ለክፍለ ከተማ ፅ/ቤቶቹ ካስኬድ በማድረግ ተፈራረመ
ነሐሴ 07/2018ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2019 በጀት ዓመት እቅዱ የደንብ መተላለፎች ለመቀነስ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች በማስቀመጥ ከዘርፎች እና ክፍለ ከተሞች ጋር የካስኬዲንግ እቅድ መፈራረም መርሃ-ግብር አካሄደ።
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፣ ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት ሊያሰሩ የሚችሉ እቅዶችን በማቀድና በተሳካ ሁኔታ በማስፈጸም በከተማ ደረጃ ተሸላሚ መሆን መቻሉን ገልጸዋል። ለዚህ ስኬት የተቋም ግንባታ ስራዎች ተጠናክረው መሰራታቸው፣ ለአመራሩና ለኦፊሰሮች የተሰጡ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እንዲሁም ህብረተሰቡን ያሳተፉ እንቅስቃሴዎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።
ሻለቃ ዘሪሁን በቀጣይም ስራዎችን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ በርካታ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል። በዚህም መሠረት የተያዙ እቅዶችን እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ በማውረድ በየጊዜው መገምገም እንደሚገባ፣ ህብረተሰቡ ስለ አዋጁ፣ ደንብና መመሪያዎች በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው በማድረግ የደንብ መተላለፎችን አስቀድሞ መከላከል እንደሚያስፈልግና ደንብ በሚተላለፉ አካላት ላይ ደግሞ ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል።
በተጨማሪም ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረጉ የቅንጅት ስራዎችን ማጠናከር፣ አሰራርን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ማዘመን፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻልና ብልሹ አሰራርን በመታገል ህብረተሰቡን በቀናነት ማገልገል እንደሚገባ አሳስበዋል።
ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ በ2019 በጀት ዓመት በርካታ ዋና ዋና ስትራቴጂካዊ ግቦችን ለማሳካት ማቀዱን የባለስልጣኑ የእቅድና በጀት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ ገልጸዋል።
ከተያዙት ግቦች መካከል የእጩ ፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮችን ቁጥር በማሳደግ 2,380 አዲስ ምልምሎችን ማሰልጠን፣ ህግ በሚተላለፉ አካላት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድና የክትትል ስራዎችን በማጠናከር የደንብ መተላለፎችን (በ52%) መቀነስ ይጠቀሳሉ።
ከዚህ ጎን ለጎን በማህበረሰብ አደረጃጀቶች፣ በቤት ለቤት እና በቡና ጠጡ ውይይቶች የሚከናወኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ወደ 1.9 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ለማድረስ ታቅዷል።
ተቋሙ በማህበራዊና በበጎ አድራጎት ዘርፍ 20,000 ችግኞችን በመትከልና በመንከባከብ የአቅመ ደካማ ቤተሰቦችን ቤት በማደስ ላይ የሚገኝ መሆኑን እንዲሁም ማዕድ ማጋራት ለማከናወን አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል ።
ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ የተዘረጉትን አሰራሮችና የዲጂታላይዜሽን ስራዎች በውጤታማነት በመጠቀም አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ውብ እና ህግ የሚከበርባት ከተማ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑ ተገልጻል።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

❤12👍3
የሀዘን መግለጫ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የተቋሙ አማካሪ የነበሩት እና በምክትል ስራ አስኪያጅነት ተቋሙን የመሩት ወ/ሮ አበባ እሸቴ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል።
ወ/ሮ አበባ እሸቴ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው እለት ነሐሴ 7/2018 ዓ.ም ህይወታቸው በማለፉ ተቋሙ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለመላው ቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናቱን ይመኛል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን

😭69🙈3❤1
ባለስልጣኑ ወደ ወንዝ በካይ ፍሳሽ የለቀቁ 2 ተቋማት 700,000 ብር መቅጣቱ አስታወቀ
09-12 -2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ስሙ አዋሬ አደባባይ አካባቢ ጃንቦ ሪል እስቴት የሽንት ቤት ፍሳሽ ወደ ወንዝ በመልቀቁ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር በቅንጅት በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት 300,000/ሦስት መቶ ሺህ/ ብር ተቀጥቷል።
በተያያዘ ዜና በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ሪፌንቲ አካባቢ ሼንግዴይ ኪለይ እና ሲመንት ማኑፋክቸሪንግ የግል ማህበር ያልተጣራ የሲሚንቶ ፍሳሽ ወደ ወንዝ በመልቀቁ ከአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመሆን በደንብና ቁጥር 180/2017 መሰረት 400,000/አራት መቶ ሺህ/ ብር በመቅጣት ፍሳሹ እንዲቆም ተደርጓል።
የግልና የመንግስት ተቋማት እና ግለሰቦች መሰረተ ልማት ደህንነት በመጠበቅ ከአካባቢነ ከብክለት በመጠበቅ ስራቸው እንዲሰሩ እያሳሰበ ደንብ በሚተላለፉት ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።
ህብረተሰቡ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥሪውን ያቀርባል።
መረጃው፡- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ፦ https://linktr.ee/aacodeenforcement

👍3❤1