"በቁርጠኝነትና በጥብቅ ዲሲፕሊን ህግ የማስከበር ተልዕኳችንን አጠናክረን እንቀጥላለን" ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተቋሙ በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት በቁርጠኝነትና በጥብቅ ዲሲፕሊን እየሰራ እንደሚገኝ በመግለጽ ስራዎችን በየጊዜው በመገምገም ያለውን ጥሩ አፈፃፀም በማስቀጠል የሚታዩ ክፍተቶችን በወቅቱ በማረም እንደሚሰራ ገለፁ።
በተለይ በክረምት ወራት የተከናወኑ የበጎ ፍቃድ ስራዎች፣ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ እና የደም ልገሳ ንቅናቄዎች አበረታችና ውጤታማ በመሆናቸው ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
ተቋሙ ማንኛውም አሰራር ከሌብነትና ብልሹ አሰራር የጸዳ ሊሆን እንደሚገባ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ ለተገልጋዮችም ሆነ ለሰራተኞች ምቹና ተስማሚ የሥራ አካባቢ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ዋና ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል።
ህብረተሰቡም ከደንብ መተላለፍ እንዲቆጠብና የደንብ ማስከበር ስራው አጋዥ እንዲሆን የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎችን አጠናክሮ መስራት አስፈላጊ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል ።
በዚህ የእቅድ ጊዜ ውስጥ 20,000 ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ 608 ዩኒት ደም በመለገስ እና የአቅመ ደካሞች ቤቶችን በማደስ አበይት የበጎ አድራጎት ስራዎች ተከናውነዋል።
የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች 100% ጥበቃ የተደረገላቸው ሲሆን፣ ለከተማው ህብረተሰብ ሰፊ የግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች መከናወኑንና በቀጣይም አሰራርን በዲጂታል (Smart Office) በማስደገፍ እና ቅሬታዎችን በ9995 የጥሪ ማዕከል በፍጥነት የመፍታት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ እቅዱን ያቀረቡት ኮለኔል አድማሱ አብራርተዋል።
በመጨረሻም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ90 ቀናት የልዩ ትኩረት ዕቅዱ የተመዘገቡ ስኬቶችን በማስቀጠል፣ የበጀት ዓመቱን የልማትና የደንብ ማስከበር ግቦች ስማርት አሰራሮችን በመተግበርና ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት በላቀ ሁኔታ እንደሚያስፈጽም ተገልጿል።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

❤2👍2
የአደጋ ስጋት ደህንነት ደንብ ቁጥር 132/2014 እና መመሪያ ቁጥር 163/2017 ወደ ሙሉ ትግበራ ሊገባ መሆነ ተገለፀ
ነሐሴ 01/2018ዓ.ም
** አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ደንብ ቁጥር 132/2014 እና መመሪያ ቁጥር 163/2017 ያወጣው በከተማዋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የህንፃዎች ከፍታ፣ የኢንዱስትሪዎች መስፋፋትና የህዝብ ቁጥር እድገት ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመከላከልና የህይወትና ንብረት ደህንነትን ለማረጋገጥ መሆኑ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ደንብና መመሪያው ላይ ለህብረተሰቡ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በቀጣይ ተጠናክረው የሚሰሩ መሆኑን ገልጸው፣ ደንቡን ተላልፈው በሚገኙ አካላት ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ኮማንደር አህመድ መሐመድ በመግለጫቸው እንደተናገሩት የአደጋ ስጋት ደህንነት ደንብ ቁጥር 132/2014 እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአደጋ መከላከል ፣ ቁጥጥር ፣ ፍተሽና ብቃት ማረጋገጥ ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 163/2017 የከተማችንን ህብረተሰብ ህይወትና ንብረት ከአደጋ ስጋት ለመጠበቅ የወጣ ደንብና መመሪያ ነው።
የደንቡ ዋና ዓላማ በከተማዋ ውስጥ አደጋ እንዳይደርስ አስቀድሞ መከላከል እንደሆነ ገልጸው፣ ከዚህ ቀደም አደጋ ከደረሰ በኋላ ይደረግ የነበረውን የመከላከል ተግባር ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ ወደ መከላከል ያሸጋገረ አሰራር መሆኑን አብራርተዋል።
ኮማንደር አህመድ አያይዘውም መመሪያው ተፈጻሚ የሚሆነው በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ መሆኑን በመጠቆም፣ ተቋሙ በከተማዋ የሚገኙ ተቋማትን የሙያና የቴክኒክ ድጋፍ ከመስጠት ባለፈ የፍተሻና ቁጥጥር ስራ በማካሄድ የብቃት ማረጋገጫ (ሰርቲፋይድ) የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል።
በደንቡ መሠረት ማንኛውም የህዝብ መገልገያ ህንፃ፣ የንግድ ተቋም ወይም አደገኛ ንጥረ ነገሮችን የሚያከማች ድርጅት በየዓመቱ ከአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ደህንነት ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የመያዝ እና የማደስ ግዴታ ተጥሎበታል።
ተቋማትና የህንፃ ባለቤቶች ደረጃውን የጠበቀ የውሃ መቅጃ ሀይድራንት (Hydrant)፣ የእሳት ማጥፊያ ሲሊንደሮች፣ የጭስ ማወቂያዎችና የስፕሪንክለር ስርዓት የመገጠም እንዲሁም በህንፃ ዲዛይኖቻቸው ውስጥ የአደጋ ጊዜ ማምለጫ መንገዶችን የማካተት ግዴታ አለባቸው።
የተጣሉ የደህንነት መስፈርቶችን ሳያሟሉ በሚገኙና ህጉን በሚጥሱ አካላት ላይ እንደ ጥፋቱ ደረጃ ከብር 10,000.00 እስከ ብር 100,000.00 የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት የሚጣል ሲሆን፣ በተጨማሪም የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ያላስተካከሉ ተቋማት የንግድና ስራ ፈቃዳቸው እንዲታገድ ወይም እንዲሰረዝ የሚደረግ ይሆናል።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡

👍10❤6👏2