ባለስልጣኑ የመንገድ መሠረረተ ልማት ያበላሹ እና ወንዝ የበከሉ ተቋማትና ግለሰቦች ላይ የ455 ሺህ ብር የቅጣት እርምጃ ወሰደ
ሐምሌ 29/2018ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በልደታ ክፍለ ከተማ የከተማዋን ጽዳት፣ ውበት እና የሕዝብ ጤና ለማስጠበቅ በሚያደርገው የደንብ የማስከበር እንቅስቃሴ ደንብ ተላልፈው በተገኙ አካላት ላይ አስተዳደራዊ የገንዘብ ቅጣት እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 በደንብ ቁጥር 180/2017 መመሪያ መሠረት የወንዙን ተፈጥሯዊ ይዘት ሊቀይሩ የሚችሉ ፈሳሾችን የያዘ ቆሻሻ ወደ ወንዝ በመልቀቅ አካባቢን የበከለው ፍቅሬ ኩንስፓኛ ድርጅት ላይ የ400,000 (አራት መቶ ሺህ) ብር የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት እርምጃ ተወስዶበታል።
በተጨማሪም በክፍለ ከተማው በወረዳ 05 በህገ-ወጥ መንገድ አካባቢን ከግንባታ ማዕከል በሚወጡ ተሽከርካሪዎች ጎማ አፈር፣ ጭቃ እና ፍርስራሾችን በመያዝ አካባቢውን እና መንገዱንያበላው ፈለቀ እንዳሻው ኮንስትራከሰሽን እና አሽከርካሪው ላይ የ50,000 (ሃምሳ ሺህ) እና የ5/አምስት/ ሺህ ብር አስተዳደራዊ የቅጣት እርምጃ ተወስዷል።
ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ማንኛውም ድርጅትም ሆነ ግለሰብ ሥራውን በሚያከናውንበት ወቅት የአካባቢ እና የወንዞችን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት እንዳለበት በማሳሰብ፣ የከተማዋን ደንብና መመሪያ በሚጥሱ አካላት ላይ የሚወሰደው አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
ህብረተሰቡ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው

👍5❤2
"በቁርጠኝነትና በጥብቅ ዲሲፕሊን ህግ የማስከበር ተልዕኳችንን አጠናክረን እንቀጥላለን" ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተቋሙ በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት በቁርጠኝነትና በጥብቅ ዲሲፕሊን እየሰራ እንደሚገኝ በመግለጽ ስራዎችን በየጊዜው በመገምገም ያለውን ጥሩ አፈፃፀም በማስቀጠል የሚታዩ ክፍተቶችን በወቅቱ በማረም እንደሚሰራ ገለፁ።
በተለይ በክረምት ወራት የተከናወኑ የበጎ ፍቃድ ስራዎች፣ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ እና የደም ልገሳ ንቅናቄዎች አበረታችና ውጤታማ በመሆናቸው ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
ተቋሙ ማንኛውም አሰራር ከሌብነትና ብልሹ አሰራር የጸዳ ሊሆን እንደሚገባ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ ለተገልጋዮችም ሆነ ለሰራተኞች ምቹና ተስማሚ የሥራ አካባቢ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ዋና ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል።
ህብረተሰቡም ከደንብ መተላለፍ እንዲቆጠብና የደንብ ማስከበር ስራው አጋዥ እንዲሆን የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎችን አጠናክሮ መስራት አስፈላጊ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል ።
በዚህ የእቅድ ጊዜ ውስጥ 20,000 ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ 608 ዩኒት ደም በመለገስ እና የአቅመ ደካሞች ቤቶችን በማደስ አበይት የበጎ አድራጎት ስራዎች ተከናውነዋል።
የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች 100% ጥበቃ የተደረገላቸው ሲሆን፣ ለከተማው ህብረተሰብ ሰፊ የግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች መከናወኑንና በቀጣይም አሰራርን በዲጂታል (Smart Office) በማስደገፍ እና ቅሬታዎችን በ9995 የጥሪ ማዕከል በፍጥነት የመፍታት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ እቅዱን ያቀረቡት ኮለኔል አድማሱ አብራርተዋል።
በመጨረሻም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ90 ቀናት የልዩ ትኩረት ዕቅዱ የተመዘገቡ ስኬቶችን በማስቀጠል፣ የበጀት ዓመቱን የልማትና የደንብ ማስከበር ግቦች ስማርት አሰራሮችን በመተግበርና ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት በላቀ ሁኔታ እንደሚያስፈጽም ተገልጿል።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

❤2👍2