የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.5K subscribers
3.94K photos
13 videos
1 file
93 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ በላስቲክና ፌስታል ደንብ ቁጥር 13/83/2017 ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ

ሐምሌ/28/2018
**የአዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በደንብ ቁጥር 13/83/2017 በፕላስቲክና ፌስታል ብክለት ላይ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ።

ስልጠናውን ያስጀመሩት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅና የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ
ኃላፊ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው እንዳሉት ተቋሙ በከተማ አስተዳደሩ የሚወጡትን ደንቦች አስቀድሞ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር የደንብ መተላለፉን የሚጸየፍ ማህበረሰብን ለመገንባት በተለያዩ መንገዶች ስልጠናዎችን የሚሰጥ መሆኑን ገልፀው፤ ሰልጥኖ ለማሰልጠን ዝግጁ እንዲሆኑ አሳስበዋል።

ከአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከፍተኛ ከአከባቢ ጥበቃ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሙላቱ ወሰኑ ስለ ፌስታል ብክለት መከላከልና የሚያስከትሉት ጉዳቶች ገልፀው ደንቡ በሚተገበርበት ወቅት ስለሚወሰደው እርጃ በስፋት አብራርተዋል።

በስልጠናው ላይ የተገኙት የሰልጥኖ አሰልጣኞችም የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ትምህርታዊ እውቀትን የቀሰሙበትና ወደ ታች በመውረድ ለማሰልጠን ተገቢውን እውቀት እንዳገኙ ገልጸዋል።

መረጃው፡- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
6👍2
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የቢሮ ውስጥ እድሳቱን አጠናቆ አስመረቀ

ሐምሌ 28/2018ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ​ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤቱ የቢሮ ውስጥ እድሳት በማጠናቀቅ ለሰራተኞች እና ለተገልጋዮች ምቹ የስራ አካባቢ በመፍጠር አስመረቀ።

​የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በምርቃት ተገኝተው ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት የተቋም ግንባታና አደረጃጀትን ማሻሻል ከህብረተሰቡ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ፣ ለዜጎች ፍትሃዊና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልፀዋል።

​በምርቃት መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ ደንብ ማስከበር የደንብ መተላለፎችን በመቆጣጠር የተሰጠውን ተልዕኮ በውጤት ከመፈጸምና በኃላፊነት ከመወጣት ባሻገር ያከናወነው ይህ የተቋም ግንባታ ስራ የሚበረታታና ሌሎች ጽህፈት ቤቶችንም የሚያነሳሳ ነው ብለዋል።

​ዘገባው ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
👍113
ጠንካራ የሚዲያና ኮሙኑኬሽን ስራ ለተቋም ግንባታ መሠረት መሆኑ ተገለፀ

29/11/2018ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመራር ከሰራተኞችና ከሚያገለግሉት ማህበረሰብ ያለውን ተግባቦት ለማጠናከር ጂኦ-ስፓሻል ቴክኖሎጂ እና በሚዲያ አጠቃቀምና ተግባቦት ላይ ስልጠና ሰጠ።

የሚዲያና ኮሙኑኬሽን ስራ ለተቋም ግንባታ እና የአመራርነት ውጤታማነት ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅና የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ሀላፊ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ገልጸዋል።

ዘመኑ የመረጃ በመሆኑ ከዘመኑ ጋር ቴክኖሎጂ ስርዓት መሠረት መረጃዎች ጂኦ-ስፓሻል ቴክኖሎጂ ስርት በመተግበር የደንብ መሠስከበር ስርዓት ማጠናከር እንደሚገባ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ የውጭና የህዝብ ግነኙነት ኃላፊ ዋና ኢኒስፔክተር ፍፁም ብርሀኑ በስልጠው አስረድተዋል።

በሚዲያ አጠቃቀምና ተግባቦት ላይ ስልጠና የሰጡት የተቋሙ የኮሙኑኬሽን ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ ጠንካራ የህዝብ ግንኙነት ለመፍጠር እና የህብረተሰብ ድጋፍ ለማግኘት ወቅቱን የጠበቀ የተግባቦት ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑ ጠቁመዋል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣኑ የኮሙኑኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
3👏1
ባለስልጣኑ የመንገድ መሠረረተ ልማት ያበላሹ እና ወንዝ የበከሉ ተቋማትና ግለሰቦች ላይ የ455 ሺህ ብር የቅጣት እርምጃ ወሰደ

ሐምሌ 29/2018ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በልደታ ክፍለ ከተማ የከተማዋን ጽዳት፣ ውበት እና የሕዝብ ጤና ለማስጠበቅ በሚያደርገው የደንብ የማስከበር እንቅስቃሴ ደንብ ተላልፈው በተገኙ አካላት ላይ አስተዳደራዊ የገንዘብ ቅጣት እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።

​በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 በደንብ ቁጥር 180/2017 መመሪያ መሠረት የወንዙን ተፈጥሯዊ ይዘት ሊቀይሩ የሚችሉ ፈሳሾችን የያዘ ቆሻሻ ወደ ወንዝ በመልቀቅ አካባቢን የበከለው ፍቅሬ ኩንስፓኛ ድርጅት ላይ የ400,000 (አራት መቶ ሺህ) ብር የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት እርምጃ ተወስዶበታል።

​በተጨማሪም በክፍለ ከተማው በወረዳ 05 በህገ-ወጥ መንገድ አካባቢን ከግንባታ ማዕከል በሚወጡ ተሽከርካሪዎች ጎማ አፈር፣ ጭቃ እና ፍርስራሾችን በመያዝ አካባቢውን እና መንገዱንያበላው ፈለቀ እንዳሻው ኮንስትራከሰሽን እና አሽከርካሪው ላይ የ50,000 (ሃምሳ ሺህ) እና የ5/አምስት/ ሺህ ብር አስተዳደራዊ የቅጣት እርምጃ ተወስዷል።

​ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ማንኛውም ድርጅትም ሆነ ግለሰብ ሥራውን በሚያከናውንበት ወቅት የአካባቢ እና የወንዞችን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት እንዳለበት በማሳሰብ፣ የከተማዋን ደንብና መመሪያ በሚጥሱ አካላት ላይ የሚወሰደው አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

ህብረተሰቡ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው
👍52