የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.5K subscribers
3.94K photos
13 videos
1 file
93 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
የባለስልጣኑ አመራር እና ሰራተኞች በአንድ ጀምበር 8 መቶ ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል አሻራቸውን እያኖሩ ይገኛሉ

ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመራሮች እና ሰራተኞች በአንድ ጀምበር 8 መቶ ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል አሻራቸውን እያኖሩ ይገኛሉ።

በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በአንድ ጀምበር ብቻ 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የተያዘው ግብ ለማሳካት በአንድ ላይ በመሰለፍ የታሪክ አካል እየሆኑ ይገኛሉ።

ዛሬ የምትተከለው እያንዳንዷ ችግኝ ለምግብ ዋስትና፣ ለውሃ ሀብት ጥበቃ፣ ለምግብ አቅርቦትና ለቀጣይ ትውልድ ንጹህ አየር ዋስትና ናት።

ዛሬ የምንተክለው ችግኝ፣ ነገ የምንሰበስበው አረንጓዴ ተስፋ ነው።

የትም ይሁኑ የት፣ በሚኖሩበትና በሚሠሩበት አካባቢ ቢያንስ አንድ ችግኝ በመትከል የዚህ ታሪካዊ ዕለት አካል ይሁኑ።

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን!
👍31
የባለስልጣኑ አመራር እና ሰራተኞች በአንድ ጀምበር 8 መቶ ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል አሻራቸውን አኖሩ

ዛሬ የምትተከለው እያንዳንዷ ችግኝ ለምግብ ዋስትና፣ ለውሃ ሀብት ጥበቃ፣ ለምግብ አቅርቦትና ለቀጣይ ትውልድ ንጹህ አየር ዋስትና ናት።

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን!
👍5👏21
ባለስልጣኑ የእጩ አመራሮች የመሪነት እና የክህሎት ማሳደጊያ ስልጠና መካሄድ ጀመረ

ሐምሌ 28/2018ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰር ለተወጣጡ እጩ አመራሮች የመሪነት እና የክህሎት ማሳደጊያ ስልጠና መካሄድ ጀምሯል።

​ስልጠናው እንደ መሪ የማሰብ፣ የማቀድ እና የመፈጸም ክህሎትን ለማዳበር ያለመ ሲሆን በዋናነት የመሪነት ክህሎትን፣ የተከታይነት ባህሪያትን፣ የስሜት ብልህነትን፣ የመሪነት ንድፈ-ሀሳቦችን እና ስልቶችን፣ የማበረታቻ ስልቶችን እና ሌሎች ጠቃሚ የመሪነት ፅንሰ-ሀሳቦችን ያካተተ ነው።

​በስልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ በ2018 በጀት ዓመት በአፈጻጸሙ አንደኛ በመሆን የተሸለመ መሆኑን አስታውሰው ይህ ስልጠና ከተማችን እያሳየች ያለችውን ፈጣን እድገት በሚመጥን መልኩ ተቋሙን በዘመናዊ አሰራር እና በእውቀት የሚመራ በተግባር የሚታይ የአመራር ብቃትን የተላበሰ፣ በመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ ጥብቅ እርምጃ የሚወስድ እና የአገልግሎት እርካታን የሚያረጋግጥ ብቁ እና ንቁ እጩ አመራሮችን ለማፍራት ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።

​ የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ስልጠናው ለአራት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ በመግለጽ ሰልጣኞች ስልጠናውን በከፍተኛ ንቃት፣ ተነሳሽነት እና ጥብቅ ዲስፕሊን እንዲከታተሉ አሳስበዋል።

ይህ ስልጠና ተቋሙ የወደፊት ተተኪ መሪዎችን በማፍራት የተቋሙን ዘላቂ እድገት ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወትም ገልፀዋል።

​ባለስልጣኑ ይህንን ስልጠና በማካሄድ ብቁ እና ንቁ አመራሮችን በማፍራት የከተማዋን እድገት ለማፋጠን እና የህዝብ አገልግሎትን ለማሻሻል ያለውን ቁርጠኝነት ያሳኘ መሆኑ ተገልጿል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡
👍65