የመንገድ መሰረተ ልማት ደህንነትን ጥበቃና ጽዳት በተመለከተ የተቀናጀ የቁጥጥር ስርዓት ሊተገበር መሆኑ ተገለጸ
ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ የክረምት ወራት በመሆኑ የመንገድ መሰረተ ልማት ደህንነት እና ጽዳት ስራዎችን በተመለከተ የሚስተዋሉ የመንገድ መሠረተ-ልማቶች ጉዳት ለመከላከል በቅንጅት መስራት የሚያስችል የውይይት መድረክ አካሄዱ።
በውይይት መድረኩ የሁለቱም ተቋማት የማእከል እና የክፍለ ከተማ ኃላፊዎች በተገኙበት ጌዜው ክረምት በመሆኑ የከተማዋን የመንገድ መሰረተ ልማት በአንድአንድ ግዴለሽ የግንባታ ተቋማትና ግለሰቦች የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች ለመከላከልና ጽዳታቸው ማስጠበቅ በተመለከተ የሚተገበሩ አሰራሮች ላይ ውይይት ተደርጓል።
የመድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የክትትል ቁጥጥርና እርምጃ አወሳሰድ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከፍያለው ታደሰ አዲስ አበባ የሀገራችንና የአፍሪካ መዲና እንዲሁም የበርካታ አለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ በመሆኗ የጽዳትና የውበቷ ተግባር የሁሉንም ተሳትፎ የሚጠይቅ እና ለአፍታም መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ከፍያለው አክለውም ከተማችን በቅርቡ የምታስተናግደውን የCOP 32 ጉባኤ ጨምሮ ለተለያዩ ሁነቶች እንደሚካሄድ ጠቁመው በተለይም በግንባታ ተሽከርካሪዎች አማካኝነት ጎማቸው ሳያጸዱ የሚወጣ ጭቃ፣ አፈርና ያልተሸፈነ የህንጻ ግንባታ ተረፈ ምርት በአስፋልት መንገዶች ላይ የሚያደርሱትን ጉዳትና ማቆሸሽ በህጉ መሠረት ስርዓት ማስያዝና ተጠያቂነትን ማስፈን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በቅኝት የተገኙት ለሚ ኩራ፣ አራዳ፣ ቂርቆስ፣ ንፋስ ስልክ፣ አቃቂ፣ ቦሌ በሌሎችም ክፍለ ከተሞች በአስፋልት መንገዶች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመግታት የተቀናጀ የቁጥጥር ስራ እንደሚሰራ ተመላክቷል።
የአዲስ አበባ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ በበኩላቸው አሰራሩን ወደ ሙሉ ተግበራዊነት ከማስገባትና የትኛውም አይነት አስተዳደራዊ ቅጣት ከመጣሉ በፊት ህብረተሰቡና የሚመለከታቸው አካላት በቂ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ግንዛቤ የመፍጠር ስራው ከተከናወነ በኋላ ደንብ በሚተላለፉ አካላት ላይ የማስተካከያና የደንብ ማስከበር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ ተቋማት እና ግለሰቦች ከእኩይ ተግባራት እንዲታቀቡ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዘገባው :- የባለስልጣኑ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።

👍8
በከተማዋ ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር የሚደረጉ የተቀናጁ የቅድመ መከላከል ሥራዎች በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ
ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የቅመ መከላከል ስራዎች አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት የግንዛዜ አሰጣጥ ስልቶች በተመለከተ የውይይት መድረክ ተካሄ።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለፈው በጀት ዓመት የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልና በግምገማው የታዩ ክፍተቶችን በማረም በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል። በተለይም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት በመቅረፍና ብልሹ አሰራርን በጽናት በመታገል የምንሰጠውን አገልግሎት ማፋጠንና ህብረተሰቡን ዝቅ ተብሎ ማገልገል እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው እንደገለጹት ባለፈው በጀት ዓመት በከተማዋ ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር የደንብ መተላለፍ ድርጊቶችን በቅድመ መከላከል ሥራዎች ለማስቀረት ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ በመሰራታቸው በርካታ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል።
በተቋሙ የተመዘገቡ ስኬቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን በዘላቂነት ለመቅረፍ የቅድመ መከላከልና የስልጠና ሥራው ቁልፍ ሚና እንዳለው በመጠቆም በተያዘው በጀት ዓመትም የከተማዋን ጽዳት ውበትና ሰላም ለማስጠበቅ የሚያስችሉ የተቀናጁ የቅድመ መከላከል ሥራዎች ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሠራ ገልጸዋል ።
አክለውም በከተማችን የሚገኙ የህብረተሰብ አካላት የደንብ መተላለፍ እንዳይፈጽም እና እንዲጸየፍ ለማድረግ እየተሰጡ ያሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ማጠናከር አስፈላጊ ነው ሲሉ ገልጸዋል ።
በመድረኩ ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የቀጣይ የቅድመ መከላከልና የግንዛቤ ስራዎች ስራ የትኩረት አቅጣጫ በባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ተቀምጠዋል ።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡

❤8👍3
የባለስልጣኑ አመራር እና ሰራተኞች በአንድ ጀምበር 8 መቶ ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል አሻራቸውን እያኖሩ ይገኛሉ
ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመራሮች እና ሰራተኞች በአንድ ጀምበር 8 መቶ ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል አሻራቸውን እያኖሩ ይገኛሉ።
በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በአንድ ጀምበር ብቻ 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የተያዘው ግብ ለማሳካት በአንድ ላይ በመሰለፍ የታሪክ አካል እየሆኑ ይገኛሉ።
ዛሬ የምትተከለው እያንዳንዷ ችግኝ ለምግብ ዋስትና፣ ለውሃ ሀብት ጥበቃ፣ ለምግብ አቅርቦትና ለቀጣይ ትውልድ ንጹህ አየር ዋስትና ናት።
ዛሬ የምንተክለው ችግኝ፣ ነገ የምንሰበስበው አረንጓዴ ተስፋ ነው።
የትም ይሁኑ የት፣ በሚኖሩበትና በሚሠሩበት አካባቢ ቢያንስ አንድ ችግኝ በመትከል የዚህ ታሪካዊ ዕለት አካል ይሁኑ።
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን!

👍3❤1