"ባለፉት ዓመታት ያስመዘገብነውን ድል አጠናክረን ለማስቀጠል ዝግጁ ልንሆን ይገባል" — ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ
ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የደንብ መተላለፍ ክትትል ቁጥጥር እርምጃ አወሳሰድ ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት የነበረው ጥንካሬ ለማስቀጠል እና ክፍተቶች በማረም የ2019 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች አስቀመጠ ።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት የተመዘገቡ ውጤቶችንና ድሎችን በቀጣይም አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸው ለዚህ ውጤት መመዝገብ የፓራሚሊተሪ ኦፊሰሩ ሚና ከፍተኛ እንደነበር በመጥቀስ በቀጣይም ለላቀ ስራ ዝግጁ መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።
በ2018 በጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ውጤቶች ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በቅንጅት በመሰራታቸው የመጡ ናቸው ፤ የደንብ መተላለፍን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራውን በዘመናዊ መንገድ ለመምራት አሰራሮችን በቴክኖሎጂ የመደገፍ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ ገልጸዋል።
በቀጣይ በተለይም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት በመቅረፍና ብልሹ አሰራርን በጽናት በመታገል ህዝባዊ አገልግሎቱን ማጠናከር እንደሚገባ ተመላክቷል።
መሬት ባንክ የገቡ መሬቶችን በአግባቡ በመጠበቅና በመከላከል የመሬትን ወረራን መቶ በመቶ(100%) መቆጣጠር የተቻለበት መሆኑንና ሌሎች በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን እንዲቀንሱ በማድረግ በርካታ ተግባራት በበጀት ዓመቱ መከናወኑ በውይይቱ ተገልጿል።
ከከተማ እስከ ወረዳ ድረስ አመራር እና ሰራተኛ በመናበብ እየሰራ እንደሚገኝና በዚህም የተሻለ አፈጻጸም ማስመዘገቡንና በቀጣይም ይህን በማጠናከር የተሻለ ስራዎችን መስራት አንደሚገባ በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተቀምጧል ።
በበእለቱ ታቅደው የተፈጸሙ ክንውኖች ፣ ታቅደው ያልተከናወኑ ተግባራቶች ፣ በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ተግዳሮቶችን ለመፍታት የተከናወኑ መፍትሔዎች ቀርበው ውይይት ተደርገውበታል።
በመድረኩ የክፍለ ከተማ አስተባባሪ፣ የቁጥጥር ስራ አስተባባሪዎች፣ የግብረ ሀይል ቡድን መሪዎች እና የወረዳ ሽፍት መሪዎች ተገኝተዋል ።
ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።

👏10👍7❤3🥰2
ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍ የፈጸመውን ድርጅት መቅጣቱን አስታወቀ
ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ልዩ ቦታ አሮጌ ቄራ ተብሎ የሚጠራ ቦታ የቲኤንቲ /TNT CONSTRACTION/ ንግድ ስራዎች ድርጅት ከግንባታ ማዕከል የወጡ ተሽከርካሪዎች በጭቃ መንገድ በማበላሸታቸው ህጋዊ እርምጃ መወሰዱ ገለፀ ።
ተቋሙ ድርጊቱን ከፈጸሙ በኃላ በወቅቱ የነበረውን ዝናብ ተገን በማድረግ በጊዜው ሊሰወሩ ቢችሉም የአራዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ከልደታ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበርና ትራፊክ ማኔጅመንት ጽ/ቤት በጋራ በመሆን መንገድ ያበላሹ የTNT CONSTRACTION ንግድ ስራዎች ድርጅት መኪናዎችን 55,000 ብር ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል ።
ባለስልጣኑ ተቋማት ስራቸውን ሲያከናውኑ የህብረተሰቡ የጋራ ሀብት የሆኑ የኮርደር ልማትና በሌሎች አካባቢ የማገኙ የመንገድ መሠረተ ልማቶችን፣ለህዝብ የተሰሩ አረንጓዴ ስፍራዎች እና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶችን ደህንነት በመጠበቅ በሀላፊነት እንዲገለገል መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
ጊዜው ክረምት በመሆኑ ማህበረሰቡ አደጋ ላይ የሚጥሉ እና ለመሠረተ ልማት ጥንቃቄ ባለማድረግ ደንብ የሚተላለፉ የግልና የመንግስት ድርጅቶች እና ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታውቋል ።
ህብረተሰቡ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

👍7❤3
የመንገድ መሰረተ ልማት ደህንነትን ጥበቃና ጽዳት በተመለከተ የተቀናጀ የቁጥጥር ስርዓት ሊተገበር መሆኑ ተገለጸ
ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ የክረምት ወራት በመሆኑ የመንገድ መሰረተ ልማት ደህንነት እና ጽዳት ስራዎችን በተመለከተ የሚስተዋሉ የመንገድ መሠረተ-ልማቶች ጉዳት ለመከላከል በቅንጅት መስራት የሚያስችል የውይይት መድረክ አካሄዱ።
በውይይት መድረኩ የሁለቱም ተቋማት የማእከል እና የክፍለ ከተማ ኃላፊዎች በተገኙበት ጌዜው ክረምት በመሆኑ የከተማዋን የመንገድ መሰረተ ልማት በአንድአንድ ግዴለሽ የግንባታ ተቋማትና ግለሰቦች የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች ለመከላከልና ጽዳታቸው ማስጠበቅ በተመለከተ የሚተገበሩ አሰራሮች ላይ ውይይት ተደርጓል።
የመድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የክትትል ቁጥጥርና እርምጃ አወሳሰድ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከፍያለው ታደሰ አዲስ አበባ የሀገራችንና የአፍሪካ መዲና እንዲሁም የበርካታ አለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ በመሆኗ የጽዳትና የውበቷ ተግባር የሁሉንም ተሳትፎ የሚጠይቅ እና ለአፍታም መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ከፍያለው አክለውም ከተማችን በቅርቡ የምታስተናግደውን የCOP 32 ጉባኤ ጨምሮ ለተለያዩ ሁነቶች እንደሚካሄድ ጠቁመው በተለይም በግንባታ ተሽከርካሪዎች አማካኝነት ጎማቸው ሳያጸዱ የሚወጣ ጭቃ፣ አፈርና ያልተሸፈነ የህንጻ ግንባታ ተረፈ ምርት በአስፋልት መንገዶች ላይ የሚያደርሱትን ጉዳትና ማቆሸሽ በህጉ መሠረት ስርዓት ማስያዝና ተጠያቂነትን ማስፈን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በቅኝት የተገኙት ለሚ ኩራ፣ አራዳ፣ ቂርቆስ፣ ንፋስ ስልክ፣ አቃቂ፣ ቦሌ በሌሎችም ክፍለ ከተሞች በአስፋልት መንገዶች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመግታት የተቀናጀ የቁጥጥር ስራ እንደሚሰራ ተመላክቷል።
የአዲስ አበባ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ በበኩላቸው አሰራሩን ወደ ሙሉ ተግበራዊነት ከማስገባትና የትኛውም አይነት አስተዳደራዊ ቅጣት ከመጣሉ በፊት ህብረተሰቡና የሚመለከታቸው አካላት በቂ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ግንዛቤ የመፍጠር ስራው ከተከናወነ በኋላ ደንብ በሚተላለፉ አካላት ላይ የማስተካከያና የደንብ ማስከበር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ ተቋማት እና ግለሰቦች ከእኩይ ተግባራት እንዲታቀቡ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዘገባው :- የባለስልጣኑ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።

👍8