የባለስልጣኑ ስኬቶች ድንገተኛ ሳይሆን በትጋትና የመስራትና የስትራቴጄክ ዕቅድ ሥራዎች ውጤት መሆኑ ተገለፀ
13/11/2018
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2018 በጀት ዓመት በተካሄደው የተቋማት የሥራ አፈፃፀም ምዘና (ካቢኔ አባል ካልሆኑ ተቋማት) ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ እንደ አምናው ሁሉ ዘንድሮም አንደኛ ደረጃ በመያዝ የላቀ ስኬቱን አስመዝግቧል።
ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ይህንን ታላቅ ድልና ስኬት ከተቋሙ አመራር እና ሰራተኞች ጋር በዛሬው ዕለት በደመቀ ሁኔታ በማክበር ስኬቱ ማስቀጠል የሚቻልበት ስልተ ተመላክቷል።
የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በመድረኩ እንደገለጹት፣ “ይህ ተከታታይ እና ወርቃማ ድል ሊገኝ የቻለው ከላይ እስከ ታች ባለው ሙሉ የአመራር፣ የሰራተኛና የፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ያልተቆጠበ ጥረት፣ የተቀናጀ አሰራር፣ የላቀ የቡድን መንፈስ እና ለከተማችን ያለን ከፍተኛ ፍቅር ውጤት በመሆኑ እንኳን ደስ አለን፤ እንኳን ደስ አላችሁ!” ብለዋል።
የባለስልጣኑ ስኬቶች ድንገተኛ ሳይሆን በትጋትና በዕቅድ የመራናቸው ሥራዎች ውጤት ናቸው ፤በ2018 በጀት ዓመት ያስመዘገብነው አንደኛ ደረጃ ከተማ አስተዳደሩ የተጣለብንን አደራ በብቃት መወጣታችንን የሚያረጋግጥ መሆሁ ገልፀዋል።
በቀጣይም ይህንን የስኬት ጉዞ ሳናቋርጥ የከተማችንን የደንብ ማስከበር ሥራ ይበልጥ በማዘመንና የደንብ ጥሰቶችን በመቀነስ የተገኘውን ድል አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ገልጸዋል ።
በዕለቱ የደስታው ተካፋይ የሆኑት የባለስልጣኑ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ ሰራተኞችና ኦፊሰሮች በተገኘው አንጸባራቂ ውጤት የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገልጸው፣ የተጀመረውን ውጤታማ የጋራ አሰራር በቀጣይም አጠናክረው ለማስቀጠል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

👍17❤5
"ባለፉት ዓመታት ያስመዘገብነውን ድል አጠናክረን ለማስቀጠል ዝግጁ ልንሆን ይገባል" — ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ
ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የደንብ መተላለፍ ክትትል ቁጥጥር እርምጃ አወሳሰድ ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት የነበረው ጥንካሬ ለማስቀጠል እና ክፍተቶች በማረም የ2019 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች አስቀመጠ ።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት የተመዘገቡ ውጤቶችንና ድሎችን በቀጣይም አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸው ለዚህ ውጤት መመዝገብ የፓራሚሊተሪ ኦፊሰሩ ሚና ከፍተኛ እንደነበር በመጥቀስ በቀጣይም ለላቀ ስራ ዝግጁ መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።
በ2018 በጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ውጤቶች ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በቅንጅት በመሰራታቸው የመጡ ናቸው ፤ የደንብ መተላለፍን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራውን በዘመናዊ መንገድ ለመምራት አሰራሮችን በቴክኖሎጂ የመደገፍ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ ገልጸዋል።
በቀጣይ በተለይም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት በመቅረፍና ብልሹ አሰራርን በጽናት በመታገል ህዝባዊ አገልግሎቱን ማጠናከር እንደሚገባ ተመላክቷል።
መሬት ባንክ የገቡ መሬቶችን በአግባቡ በመጠበቅና በመከላከል የመሬትን ወረራን መቶ በመቶ(100%) መቆጣጠር የተቻለበት መሆኑንና ሌሎች በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን እንዲቀንሱ በማድረግ በርካታ ተግባራት በበጀት ዓመቱ መከናወኑ በውይይቱ ተገልጿል።
ከከተማ እስከ ወረዳ ድረስ አመራር እና ሰራተኛ በመናበብ እየሰራ እንደሚገኝና በዚህም የተሻለ አፈጻጸም ማስመዘገቡንና በቀጣይም ይህን በማጠናከር የተሻለ ስራዎችን መስራት አንደሚገባ በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተቀምጧል ።
በበእለቱ ታቅደው የተፈጸሙ ክንውኖች ፣ ታቅደው ያልተከናወኑ ተግባራቶች ፣ በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ተግዳሮቶችን ለመፍታት የተከናወኑ መፍትሔዎች ቀርበው ውይይት ተደርገውበታል።
በመድረኩ የክፍለ ከተማ አስተባባሪ፣ የቁጥጥር ስራ አስተባባሪዎች፣ የግብረ ሀይል ቡድን መሪዎች እና የወረዳ ሽፍት መሪዎች ተገኝተዋል ።
ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።

👏10👍7❤3🥰2