የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.5K subscribers
3.95K photos
13 videos
1 file
93 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
"ለተገልጋይ እና አገልጋይ ምቹ የስራ አካባቢ በመፍጠር የአገልግሎት እርካታን ማረጋገጥ" እንደሚገባ ተገለጸ።

​ ሐምሌ 9 ቀን 2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በማዕከል የተጀመረው ምቹ የስራ አካባቢን የመፍጠር እና የአገልግሎት አሰጣጥን በማቀላጠፍ የመልካም አስተዳደር ተምሳሌትነቱን ለማረጋገጥ በየደረጃው በሚገኙ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ ጽህፈት ቤቶች የተለያዩ የሪፎርም ስራዎች አጠናክሮ በማስቀጠል በዛሬው እለት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የሰራውን የቢሮ ማዘመን ስራ ተመርቆ ለዘመናዊ አገልግሎት ዝግጁ አድርጓል።

​የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ቢሮውን በማዘመን ምቹ የስራ አካባቢን ለመፍጠር በአዲስ መልኩ ያደራጀውን ቢሮ የማስመረቅ እንዲሁም አዲሱ የፓራ ሚሊተሪ የደንብ ልብስ ለተገልጋዮቹ የማስተዋወቅ መርሀ ግብር በዛሬው እለት አካሂዷል።

​በመርሀ ግብሩ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፣ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ፣ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው እንዲሁም የ11ዱም ክ/ከተሞች ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሀላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

​የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት ለተገልጋይና አገልጋዩ ምቹ የስራ ቦታ በመፍጠር የአገልግሎት እርካታን ማረጋገጥ ያስፈልጋል በማለት በቀጣይም ይህ የሪፎርም ስራ ይበልጥ ተጠናክሮ በሌሎች ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

ዋና ስራ አስኪያጁ አክለውም ከማእከል ጀምሮ የዘመነ ተቋም መገንባቱን ገልጸው ወቅቱን የዋጀ በቴክኖሎጂ የታገዘ ብሎም ዘመናዊነት የተላበሰ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ በበኩላቸው የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ባደረጋቸው የሪፎርም ስራዎች እና በሚያከናውናቸው ተግባራቶች በከተማዋ የለውጥ አብነት መሆን ችሏል ለዚህም በህብረተሰቡ ዘንድ ስለ ተቋሙ ይሰነዘር የነበረውን አሉታዊ አመለካከት እንዲቀየር አድርጓል ብለዋል።

የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ይህ የተቋም ለውጥ ፍሬያማ እንዲሆን የአማራሩና ሰራተኛው ውህደት ትልቅ ሚና እንደነበረው ገልጸው አሁንም በአገልግሎት አሰጣጥ ብሎም በሪፎርም ስራዎች ሞዴል ሆነን ተልእኮዎቻችንን በስኬት እንወጣለን ብለዋል።

የክፍለ ከተማው የደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሻምበል ኦባድ ጁና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ በአዲስ መልኩ የተደራጀውን ቢሮ እና የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮችን አዲስ የደንብ ልብስ አስተዋውቀዋል።

ኃላፊው አክለውም ይህ ማሻሻያ በቀጣይ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሳለጥና መልካም አስተዳደርን በላቀ ደረጃ ለማረጋገጥ ያለውን ፋይዳ ገልጸው፣ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

​በመጨረሻም በምረቃ ስነ ስረአቱ የታደሙት የየክ/ከተማደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሀላፊዎች ከአመራር ቁርጠኝነት ጨምሮ ጥሩ ተሞክሮ እንዳገኙ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል

ዘገባው:- የባለስልጣኑ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው
👍122
እንኳን ደስ አላችሁ!!! እንኳን ደስ አለን!!!

ድርብ ደስታ!!! ድንቅ ስኬት!!!

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2018 በጀት ዓመት ከተቋማት (የካቢኔ አባል ካልሆኑ) በጣም ከፍተኛ ውጤት በማምጣት አንደኛ ደረጃ በመውጣት የዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና ሽልማት ተበርክቶለታል ።

ይህ ውጤት እንዲመዘገብ ከፍተኛ ሚና የነበራችሁ የማዕከል የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮቻችን፣ጠዋትና ማታ የምትለፉ ኦፊሰሮቻችን ፣መላው የተቋማችን ሰራተኞች፣ የከተማችን ነዋሪዎች፣ ባለድርሻ አካላት በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!
👍2720👏6
የባለስልጣኑ ስኬቶች ድንገተኛ ሳይሆን በትጋትና የመስራትና የስትራቴጄክ ዕቅድ ሥራዎች ውጤት መሆኑ ተገለፀ

13/11/2018

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2018 በጀት ዓመት በተካሄደው የተቋማት የሥራ አፈፃፀም ምዘና (ካቢኔ አባል ካልሆኑ ተቋማት) ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ እንደ አምናው ሁሉ ዘንድሮም አንደኛ ደረጃ በመያዝ የላቀ ስኬቱን አስመዝግቧል።

ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ይህንን ታላቅ ድልና ስኬት ከተቋሙ አመራር እና ሰራተኞች ጋር በዛሬው ዕለት በደመቀ ሁኔታ በማክበር ስኬቱ ማስቀጠል የሚቻልበት ስልተ ተመላክቷል።

​የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በመድረኩ እንደገለጹት፣ “ይህ ተከታታይ እና ወርቃማ ድል ሊገኝ የቻለው ከላይ እስከ ታች ባለው ሙሉ የአመራር፣ የሰራተኛና የፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ያልተቆጠበ ጥረት፣ የተቀናጀ አሰራር፣ የላቀ የቡድን መንፈስ እና ለከተማችን ያለን ከፍተኛ ፍቅር ውጤት በመሆኑ እንኳን ደስ አለን፤ እንኳን ደስ አላችሁ!” ብለዋል።

​የባለስልጣኑ ስኬቶች ድንገተኛ ሳይሆን በትጋትና በዕቅድ የመራናቸው ሥራዎች ውጤት ናቸው ፤በ2018 በጀት ዓመት ያስመዘገብነው አንደኛ ደረጃ ከተማ አስተዳደሩ የተጣለብንን አደራ በብቃት መወጣታችንን የሚያረጋግጥ መሆሁ ገልፀዋል።

በቀጣይም ይህንን የስኬት ጉዞ ሳናቋርጥ የከተማችንን የደንብ ማስከበር ሥራ ይበልጥ በማዘመንና የደንብ ጥሰቶችን በመቀነስ የተገኘውን ድል አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ገልጸዋል ።

​በዕለቱ የደስታው ተካፋይ የሆኑት የባለስልጣኑ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ ሰራተኞችና ኦፊሰሮች በተገኘው አንጸባራቂ ውጤት የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገልጸው፣ የተጀመረውን ውጤታማ የጋራ አሰራር በቀጣይም አጠናክረው ለማስቀጠል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
👍175