ባለስልጣኑ "ደም መለገስ ህይወት መስጠት ነው" መሪ ቃል የደም ልገሳ መርሐ ግብር አከናወነ
02/11/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ከተማ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ጋር በመተባበር "ደም መለገስ ህይወት መስጠት ነው" በሚል መሪ ቃል ያዘጋጁት ታላቅ የደም ልገሳ መርሐ-ግብር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተከናውኗል።
በደም ልገሳ መርሐ-ግብር ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ባደረጉት ንግግር የደንብ ማስከበር ተቋም የከተማዋን ሰላምና ሥርዓት ከመጠበቅና ሕግን ከማስከበር ጎን ለጎን የሕዝብን ሕይወት ለመታደግና ወገንተኝነትን ለማሳየት በሚደረጉ መሰል የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ ሁልጊዜም ግንባር ቀደም ተሳታፊ መሆኑን ገልጸዋል።
አክለውም ደም መለገስ ለወገን ሕይወት መታደግ ብቻ ሳይሆን በራሱ ታላቅ ሰብአዊነትና የውስጥ እርካታ የሚገኝበት የበጎነት ማሳያ ነው በማለት በልገሳው ላይ በንቃት ለተሳተፉ የተቋሙ አመራሮች፣ የቢሮ ባለሙያዎችና ለደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ታላቅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ አስራት ንጉሴ በከተማችን የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ባህልን ለማሳደግና የማኅበረሰቡን ትብብር ለማጠናከር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ውጤታማ እየሆኑ መምጣታቸውን ጠቁመዋል።
የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አባላት የከተማዋን ደንብና ሥርዓት በቁርጠኝነት ከመጠበቅ ባለፈ በዛሬ ለሕይወት ሕይወት የሚሆነውን ደማቸውን በመለገስ ያሳዩት ወገንተኝነት እጅግ የሚያስመሰግንና ለሌሎች ተቋማትም ትልቅ አርአያ የሚሆን ነው ሲሉ ወ/ሮ አስራት ገልጸዋል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው በዚህ መርሐ-ግብር ላይ የሁለቱ ተቋማት አመራሮች፣ ሠራተኞች ፣ የክ/ከተማና የወረዳ ደንብ ማስከበር ኃላፊዎች እና ኦፊሰሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፣ የተሰበሰበው ደም በሕክምና ማዕከላት ለሚገኙና ደም ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ሕይወትን እንደሚታደግ ተገልጿል።
ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው
።

👍13❤3👏3
"ምቹ የስራ ቦታ መፍጠር የላቀ አፈጻጸምን ለማረጋገጥ አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነው" ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በማዕከል የተጀመረው ምቹ የስራ አካባቢን የመፍጠር እና የአገልግሎት አሰጣጥን በማቀላጠፍ የመልካም አስተዳደር ተምሳሌትነቱን ለማረጋገጥ በየደረጃው በሚገኙ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ ጽህፈት ቤቶች የጀመራቸውን የተለያዩ የሪፎርም ስራዎች አጠናክሮ በማስቀጠል በዛሬው እለት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ መተግበሩን አስታወቀ።
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ቢሮውን በማዘመን ምቹ የስራ አካባቢን ለመፍጠር በአዲስ መልኩ ያደራጀውን ቢሮ የማስመረቅ እንዲሁም አዲሱ የፓራ ሚሊተሪ የደንብ ልብስ ለተገልጋዮቹ የማስተዋወቅ መርሀ ግብር በዛሬው እለት በታላቅ ድምቀት አካሂዷል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፣ የክፍለ ከተማው የጽህፈት ቤት ኃላፊ ሻምበል ኦባድ ጁናን፣ የወረዳ የደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት "ምቹ የስራ ቦታ መፍጠር የላቀ አፈጻጸምን ለማረጋገጥ አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነው" ካሉ በኋላ፣ በቀጣይም ይህ የሪፎርም ስራ ይበልጥ ተጠናክሮ በሌሎች ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
በበጀት አመቱ ተቋሙን ከተማዋ ከያዘችው የዘመናዊ ከተማነትና የልማት ጉዞ ጋር በማስተሳሰር ወደ ላቀ ከፍታ ማሸጋገር እንደሚገባም አሳስበዋል።
የክፍለ ከተማው የደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሻምበል ኦባድ ጁና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ በአዲስ መልኩ የተደራጀውን ቢሮ እና የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮችን አዲስ የደንብ ልብስ አስተዋውቀዋል።
ኃላፊው አክለውም ይህ ማሻሻያ በቀጣይ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሳለጥና መልካም አስተዳደርን በላቀ ደረጃ ለማረጋገጥ ያለውን ፋይዳ ገልጸው፣ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በዕለቱ መርሃ ግብር ላይ በሰንዳፋ እና በአዳይቱ በተሰጡ ስልጠናዎች ላይ ለተሳተፉ አካላት የዕውቅና ምስክር ወረቀት የተሰጠ ሲሆን ክፍለ ከተማው ለሚያሳድጋቸው ህጻናትም የድጋፍና የስጦታ ማበርከት ስነ-ስርዓት ተከናውኗል።
ዘገባው:- የባለስልጣኑ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው

👍4