የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.5K subscribers
3.96K photos
13 videos
1 file
93 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ "ደም መለገስ ህይወት መስጠት ነው" መሪ ቃል የደም ልገሳ መርሐ ግብር አከናወነ

02/11/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ከተማ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ጋር በመተባበር "ደም መለገስ ህይወት መስጠት ነው" በሚል መሪ ቃል ያዘጋጁት ታላቅ የደም ልገሳ መርሐ-ግብር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ተከናውኗል።

​በደም ልገሳ መርሐ-ግብር ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ባደረጉት ንግግር የደንብ ማስከበር ተቋም የከተማዋን ሰላምና ሥርዓት ከመጠበቅና ሕግን ከማስከበር ጎን ለጎን የሕዝብን ሕይወት ለመታደግና ወገንተኝነትን ለማሳየት በሚደረጉ መሰል የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ ሁልጊዜም ግንባር ቀደም ተሳታፊ መሆኑን ገልጸዋል።

አክለውም ደም መለገስ ለወገን ሕይወት መታደግ ብቻ ሳይሆን በራሱ ታላቅ ሰብአዊነትና የውስጥ እርካታ የሚገኝበት የበጎነት ማሳያ ነው በማለት በልገሳው ላይ በንቃት ለተሳተፉ የተቋሙ አመራሮች፣ የቢሮ ባለሙያዎችና ለደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ታላቅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

​የአዲስ አበባ ከተማ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ አስራት ንጉሴ በከተማችን የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ባህልን ለማሳደግና የማኅበረሰቡን ትብብር ለማጠናከር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ውጤታማ እየሆኑ መምጣታቸውን ጠቁመዋል።

የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አባላት የከተማዋን ደንብና ሥርዓት በቁርጠኝነት ከመጠበቅ ባለፈ በዛሬ ለሕይወት ሕይወት የሚሆነውን ደማቸውን በመለገስ ያሳዩት ወገንተኝነት እጅግ የሚያስመሰግንና ለሌሎች ተቋማትም ትልቅ አርአያ የሚሆን ነው ሲሉ ወ/ሮ አስራት ገልጸዋል።

​በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው በዚህ መርሐ-ግብር ላይ የሁለቱ ተቋማት አመራሮች፣ ሠራተኞች ፣ የክ/ከተማና የወረዳ ደንብ ማስከበር ኃላፊዎች እና ኦፊሰሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፣ የተሰበሰበው ደም በሕክምና ማዕከላት ለሚገኙና ደም ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ሕይወትን እንደሚታደግ ተገልጿል።

ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው
👍133👏3