የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.5K subscribers
3.96K photos
13 videos
1 file
93 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር አካሄደ

23/10/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን "ተስፋን እንትከል " በሚል መሪ ቃል የክረምት በጎ ፍቃድ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርዓ ግብር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በብሔረ ጽጌ ፓርክ አካሂዷል ።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደገለጹት ይህ የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር በጠቅላይ ሚኒስትራችን እና በከተማችን ከንቲባ የተጀመረውን የ90 ቀን የክረምት እቅድ ለማስቀጠል ተቋሙ የጀመረው ስራ መሆኑን ጠቁመዋል።
አክለውም ባለስልጣኑ ባለፈው ዓመት 18 ሺህ ችግኞችን የተከለ ሲሆን፣ በዘንድሮው ዓመት ተጨማሪ 2 ሺህ በመጨመር በአጠቃላይ 20 ሺህ ችግኞችን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ እንደሚተክል አስታውቀዋል።

ተስፋን መትከል ማለት ዛሬ ላይ ሆኖ ነገን ብሩህ አድርጎ ማየት ማለት ነው፤ ነገ ብሩህ የሆነ ብልጽግናን ማየት ማለት ነው። ዛሬ የተከልነውን ነገ ፍሬውን እንለቅማለን ሲሉ ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል ።

ከችግኝ ተከላው በተጨማሪም ተቋሙ የደም ልገሳ፣ የማዕድ ማጋራት እና ሌሎች የበጎ አድራጎት ስራዎችን በቀጣይ እንደሚያከናውን አረጋግጠዋል።

​የመርኃ ግብሩ የክብር እንግዳ የሆኑት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አህመድ ሀሰን የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ስያሜውን ቀይሮ በህዝብ ዘንድ የነበረውን የእምነት ጉድለት በማረምና የሪፎርም ስራዎችን በብቃት በመተግበር ዛሬ ለደረሰበት የላቀ ደረጃ ላይ መብቃቱን ገልጸዋል።

ይህ መርኃ ግብር ልምላሜን፣ የከተማችንን አረንጓዴነት፣ የነዋሪዎቿን ምግብ እና ተስፋን የምንተክልበት በመሆኑ ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን የበኩላችንን ኃላፊነት መወጣት ይጠበቅብናል ሲሉ አቶ አህመድ ገልጸዋል ።

ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው
👍143
የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አአገልግሎት አሰጣጥ የሪፎርም ስራ በወረዳ ፅ/ቤቶቹ መተግበር መጀመሩ ተገለፀ

25/10/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ለሰራተኞች ለተገልጋዮች ምቹ የስራ አከባቢ በመፍጠር ያከናወነውን የሪፎርም፣ የተቋም ግንባታ ስራዎች ከማዕከል አስከ ወረዳ የሚገኙ ኃላፊዎች በተገኙበት የቢሮ ጉብኝት ተካሂዷል ።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እየተከናወነ የሚገኘው ምቹ የስራ አከባቢን የመፍጠር እና የሪፎርም ስራዎች የተሰጠንን ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት የሚያግዝ የሰራተኛውን የስራ ተነሳሽነት የሚጨምር እንዲሁም የምንሰጠው ቀልጣፋ አገልግሎት የተገልጋዩን ማህበረሰብ እርካታ የሚጨምር መሆኑን ገልጸዋል ።

አክለውም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ ምቹ የስራ አከባቢ በመፍጠር አአገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ማዘመንና ቀልጣፋ ማድረግ እንደሚገባና እየተከናወኑ የሚገኘው የሪፎርም ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል ።

ወረዳው በከተማ ደረጃ የተጀመረውን የሪፎርም ስራ በማስቀጠል ለሰራተኞች እና ለተገልጋዮች ምቹ የስራ አከባቢ በመፍጠር እንዲሁም ስራዎችን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግና የደንብ መተላለፎችን በዘመናዊ መንገድ ለመከታተል ከኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በመተባበር የሁኔታዎች መከታተያ ክፍል አዘጋጅቷል
በተጨማሪም ለሰራተኞቹ ምቹ የማደሪያ ክፍል፣ ልብስ መቀየሪያ ፣ ምግብ ማብሰያ ክፍልና ሻወር ቤት አዘጋጅቷል ።

የጉብኝቱ ተሳታፊዎች አሁን በወረዳው የታየው አበረታች አፈጻጸም በሚሰሩበት አካባቢዎች ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባው በመሆኑ የተጀመረውን የሪፎርምና የተቋም ግንባታ ሥራ በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል በቁርጠኝነት የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል ።
👍107👏4