የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.5K subscribers
3.96K photos
13 videos
1 file
93 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በማዕከል የተጀመረው የሪፎርም ስራዎች አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል አስታወቀ

18/10/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰር እና አመራር ስልጠና ማጠቃለያ ፤ አዲሱን የፓራ ሚሊተሪ የደንብ ልብስ ምርቃት ፕሮግራም በከተማው በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት "ከስልጠና ወደ ስምሪት ፤ በዕውቀትና በቁርጠኝነት " በሚል መሪ ቃል የስራ ስምሪት መድረክ አካሄደ ።

በመድረኩ የተገኙት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አሕመድ ሀሰን ደንብ ማስከበር ባለፋት አመታት ራሱን በማዘመን በፊት ይነሳ የነበረውን ስም በማደስ ክፍተቶችን በማረም በህብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ ቀን ከለሊት ጠንክሮ በመስራት ውጤታማ በመሆን ለሌሎች አርአያ እየሆነ ይገኛል ሱሉ ተናግረዋል ።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ መቶ አለቃ ቦጋለ አለሙ በማዕከል የተጀመረው የሪፎርም ስራዎች አጠናክሮ እንደሚያስቀጥሉ በመግለፅ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ፣ በሰንዳፋና አዳይቱ ማሰልጠኛ ማዕከላት በ10 ተከታታይ ዙሮች የንድፈ ሃሳብና የተግባር ስልጠና የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት 681 የፓራ ሚሊተሪ አባላት እና አመራሮች ተሳትፈው ስልጠናቸውን በስኬት ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል።

ተቋሙ እየገነባው ካለው ዘመናዊ አደረጃጀትና ሙያዊ ክብር ጋር የሚመጥን አዲስ የደንብ ልብስ ያሳመረቀ ሲሆን በዛሬው ዕለት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የክፍለ ከተማው ዋና ሰራ አስፈጻሚ እና ሌሎች የክፍለ ከተማው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት አዲሱን የፖራ ሚሊተሪ የደንብ ልብስ አስተዋውቋል።

የማህበራዊ ችግር ለገጠማት በክፍለ ከተማው የምታገለግል የደንብ ማስከበር ኦፊሰር ድጋፍ የተደረገ ሲሆን የሚደረግላቸውን ድጋፍ በቀጣይም እንደሚቀጥል ተገልጿል።

ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው
11👍5
በበጀት አመቱ የደንብ መተላለፎች በ81.3% መቀነስ መቻሉ ተገለፀ ።

20/10/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከክፍለ ከተማና ወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎች አስቀምጧል ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት ጠንካራ አፈፃፀሞችን ያስመዘገበ መሆኑን ገልጸው፣ የተገኙ ስኬቶችን ይበልጥ ለማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን በ2019 በጀት ዓመት ለመሙላት መድረኩ መዘጋጀቱን አስገንዝበዋል።

​ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ በበጀት ዓመቱ ካከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል በተለይ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ በሕግ ማስከበር፣ በተቋም ግንባታ እና በሰው ኃይል አቅም ማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ርቀት መጓዙ ተገልጿል።

ቀደም ሲል አናሎግ የነበረውና በቀን ለ12 ሰዓታት ብቻ አገልግሎት ይሰጥ የነበረው የ9995 የጥሪ መስመር ወደ ዲጂታል በመቀየር፣ በአሁኑ ወቅት በአምስት ቋንቋዎች የ24 ሰዓት ሙሉ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገልፆ በቀን ከ200 እስከ 300 የሚደርሱ ጥቆማዎችን በመቀበል፣ ከሕዝብ በሚገኝ መረጃ ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ የመፈፀም አቅምን ለማሳደግ ለነባር ኦፊሰሮች እና አመራሮች በኢትዮጽያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በሰንዳፋ እና በአዳይቱ የመፈጸም አቅምን የሚያሳድጉ ጠንካራ ስልጠናዎች ተሰጥተዋል።

​በኮሪደር ልማት የተሰሩ መሰረተ ልማቶችን ከመጠበቅ አንፃር ተቋሙ ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል። ከዚህ ባለፈም ከመሬት አስተዳደር ጋር በተያያዘ ወደ መሬት ባንክ የገቡ መሬቶችን ሙሉ በሙሉ ማስከበር የተቻለ ሲሆን፣ ከ9ኙ የደንብ ጥሰቶች (የጎዳና ንግድ፣ የደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ፣ ሕገ-ወጥ ማስታወቂያ እና ሌሎችም) ጋር በተያያዘ በተደረገ ጠንካራ ስራ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ81.3% ብልጫ ያለው ውጤት ተመዝግቧል ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2018 በጀት ዓመት በእቅድ አፈጻጸም የተከናወኑ አበይት ተግባራት ፣ የገጠሙ ተግዳሮቶች ፣ የተወሰዱ የመፍትሄ ሪፖርት በባለስልጣኑ እቅድና በጀት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል ።

በመድረኩ የ2019 በጀት ዓመት መሪ እቅድ እና የቀጣይ 90 ቀናት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

በመጨረሻም በመድረኩ የተሳተፉ አመራሮችና ዳይሬክተሬቶች በቀረበው ሪፖርት እና እቅድ ላይ ሀሳብናና ጥያቄዎች አቅርበው ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቶበት ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ዋና ስራ አስኪያጁ አስቀምጠዋል ።

ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው
👍81👎1