የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.5K subscribers
3.96K photos
13 videos
1 file
93 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
የከተማችን ስነ-ምህዳር ጤንነት በማስጠበቅ የደንብ መተላለፎች ለመከላከል ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ

06/10/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና የአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በደንብ 180/2017 ወንዝና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች ብክለት መከላከልና በአዋጅ ቁጥር 1383/2017 ስራዎች ዙሪያ በተመለከተ የውይይት መድረክ ተካሄደ ።

በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር እሸቱ ለማ ከተማችንን ንጹህ ውብ ለነዋሪዎቿ ምቹ ለቱሪስት መስብ የአፍሪካ ተምሳሌት እንድትሆን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ህብረተሰቡን በማሳተፍ በመስራትና የግንዛቤ ስራዎች በስፈት በመከናወኑ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል።

የፕላስቲክ ምርቶች /ፌስታሎች / በተፈጥሮ ለረጅም ጊዜ ሳይበሰብሱ የሚቆዩ በመሆናቸው የአከባቢ ስነምህዳር ብሎም የሰዎች እና የእንስሳት የጤና ጠንቅ በመሆናቸው ህብረተሰቡ እነዚህን የጤና ጠንቅ የሆኑ ምርቶችን ባለመጠቀም አጠቃላይ የስነምህዳር ጤንነትን በማስጠበቅ ሂደት የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ዶ/ር እሸቱ ገልጸዋል ።

የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ ወንዞችን እና የወንዙ ዳርቻዎችን ከብክለት ጽዱ ለማድረግ ሁለቱም ተቋማት በጋራ በመቀናጀት ለመከላከልና የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት በርካታ ተግባራትን በጋራ በማከናወን አመርቂ ስራ መሰራቱንና በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልጸዋል ።

አክለውም ከቅጣትና ከደንብ ማስከበር ባለፈ፣ ህብረተሰቡ ስለ አካባቢ ጥበቃና ስለ ቆሻሻ ጉዳት በቂ ግንዛቤ አግኝቶ ቆሻሻን የሚፀየፍ ትውልድ እንዲፈጠር በትኩረት መስራት እንደሚገባና ህግንና ደንብን ተላልፈው አካባቢን በሚበክሉ አካላት ላይ ጥብቅ የደንብ ማስከበር ስራ እንደሚሰራና ተጠያቂነት እንደሚሰፍን አስገንዝበዋል።

በመድረኩ በደንብ 180/2017 የወንዝ ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል በአዋጅ ቁጥር 1383/2017 በጋራ የተሰሩ ጥቅል ስራዎች ሪፖርት እና የፕላስቲክ ከረጢት አምራቾችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የህግ ተከባሪነት የመስክ ሪፖርት ቀርቧ ውይይት ተካሂዷል ።

በአዋጅ 1383/2017 የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ ላይ የፕላስቲክ ብክለትን ለመቀነስ አዋጁን ለመተግበር በተደረጉ የቅጣት እርምጃዎች ህግን ባለመክበር 60 አካላት በድምሩ 1.3 ሚሊዮን ብር መቀጣታቸው በሰዱ ተገልጿል ።

ከተማችን ከአካባቢ ብክለትና ከደንብ መተላለፍ የጸዳች ለማድረግ ከላይ አስከ ታች ያለው መዋቅር በቅንጅትና በቁርጠኝነት ሊሰራ እንደሚገባ በመድረኩ ተገልጿል

ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
12👍9👏1
ባለስልጣኑ የፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮች የሥልጠና ማጠቃለያ እና አዲስ የደንብ ልብስ ትውውቅ አደረገ

13/10/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮች የሥልጠና ማጠቃለያ እና የደንብ ልብስ ትውውቅ ፕሮግራም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አበቤ እንዲሁም የከተማው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት አካሂዷል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አበቤ የከተማ አስተዳደሩ ተቋሙን ለማደራጀት የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል።በዚም አግባብ ባለስልጣኑ እራሱን በአስራር፣ በሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ አዘምኖ ለሌሎች ተቋማት ጭምር ተምሳሌት በመሆን ላይ ይገኛል ይህን አርአያነቱን አጠናክሮ በመቀጠል እራሱን ብራንድ ተቋም በማድረግ የከተማዋን ራዕይ እውን ለማድረግ እየሰራ ይገኛል ብለዋል ።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደገለጹት ተቋሙ ራሱን በዕውቀት፣ በቴክኖሎጂና በሰለጠነ የሰው ኃይል ለመገንባት ሰፊ የሪፎርም ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል። በዚህም በ2017 በጀት ዓመት ከከተማ አስተዳደሩ የተሰጠው እውቅና ለበለጠ ስራ መነሳሳትን የፈጠረ መሆኑን አስታውሰዋል።

​በ2018 በጀት ዓመት የተቋሙን አመራሮችና አባላት አቅም ለመገንባት በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ፣ በሰንዳፋና አዳይቱ ማሰልጠኛ ማዕከላት በ10 ተከታታይ ዙሮች የንድፈ ሃሳብና የተግባር ስልጠና ተሰጥቷል።
በዚህ ስልጠና ላይ 7,893 የፓራ ሚሊተሪ አባላት እና 148 አመራሮች በድምሩ 8,039 ሰልጣኞች ተሳትፈው ስልጠናቸውን በስኬት ማጠናቀቃቸው ሻለቃ ዘሪሁን ገልጸዋል።

የአቅም ግንባታ ስልጠና አባላቱ ከህዝብ ጋር በክብርና በሰላማዊ መንገድ እንዲግባቡ፣ ህግና ስርዓትን ያለ ምንም አድልዎ እንዲያስከብሩ፣ እንዲሁም የተሟላ ስነ-ምግባርና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክህሎት ኖሯቸው ህዝብን በታማኝነት እንዲያገለግሉ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተመላክቷል።

ተቋሙ እየገነባው ካለው ዘመናዊ አደረጃጀትና ሙያዊ ስነምግባር የሚመጥን አዲስ የደንብ ልብስ በዛሬው ዕለት በይፋ አስተዋውቋል።

ይህ አዲስ የደንብ ልብስ አለም አቀፍ ተሞክሮዎችንና ደረጃዎችን መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ ሲሆን አባላቱም ይህንን አዲስ የደንብ ልብስ ሲለብሱ ትልቅ ህዝባዊ አደራ መሸከማቸውን ተገንዝበው በኃላፊነት ስሜት መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

ከዚሁ ጎን ለጎን፣ በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ላይ በንቃት ለመሳተፍ የ90 ቀን እቅድ ተይዞ ወደ ስራ መገባቱ ተገልጿል። በዚህም አቅመ ደካማ ወገኖች የመኖሪያ ቤት ግንባታ፣ የአረንጓዴ አሻራ፣ የወላጆችን ማዕድ ማጋራት፣ የደም ልገሳ እና የአደጋ ስጋት ቅነሳ ተግባራት በዋናነት እንደሚከናወኑ ተጠቁሟል።

በዕለቱ በስራ ላይ እያሉ የአካልና የጤና ጉዳት የደረሰባቸው አባላትና የሰማዕታት ቤተሰቦችም በልዩ ክብር እንደሚታሰቡና የሚደረግላቸውን ድጋፍ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው

ጠንካራ የአገልግሎት ስርዓት ያላቸው ፣ ስነምግባር የተላበሱ ፣ አገልጋይ ባለሙያዎችን እና አመራሮችን የመፍጠር ተቋማዊ የሪፎርም ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ፦ https://linktr.ee/aacodeenforcement
5👍1
ባለስልጣኑ የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ ያለአግባብ በኮሪደር ልማት ላይ የለቀቁ አልፎዝ ፕላዛ እና ሳሚ ህንፃ /800,000/ስምንት መቶ ሺህ ብር መቅጣቱን ገለፀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13፣ ልዩ ቦታው ኢምፔሪያል አካባቢ የሚገኘውአልፎዝ ፕላዛ እና "ሳሚ ህንፃ" ከፍተኛ የሽንት ቤት ፍሳሽ ወደ ተገነባው የኮሪደር መስመር በመልቀቅ አካባቢውን በመበከላቸው አስተዳደራዊ የገንዘብ ቅጣት ተቀጥተዋል።

ቅጣቱ የከተማ አስተዳደሩ ባወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል ደንብ) መሰረት፣ ህግ በመተላለፋቸው እያንዳንዳቸው 400,000 (አራት መቶ ሺህ) ብር በድምሩ 800,000 (ስምንት መቶ ሺህ) ብር የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ።

የተወሰደው እርምጃ የከተማዋን ውበት ለመጠበቅ እና የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የወጡ ደንቦችን ለማስከበር የተጀመረው ጥብቅ ቁጥጥር አካል መሆኑ ተገልጿል።

ባለስልጣኑ ማንኛውም ተቋም እና ግለሰብ መሰል የብክለት ተግባራትን ከመፈጸም እንዲቆጠብ እና የወጡ ህጎችን እንዲያከብሩ ጥሪው አስተላልፏል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የደንብ መተላለፍ ድርጊት በሚፈፅሙ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ የሚወሰደው እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል።

ባለስልጣኑ መረጃውን ለሚሰጡት የህብረተሰብ ክፍል እያመሠገነ ሁሉም ነዋሪዎች ደንቡን ተላልፎ የሚገኝ አካል ሲመለከት በነፃ የስልክ መስመር 9995 ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን አስተላልፏል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
👏7👍3
ባለስልጣኑ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር የሚዲያ ስራዎች የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ

16/10/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የሚያከናውናቸውን ተግባራት ወደ ህብረተሰቡ ተደራሽነቱን ለማስፋት ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር በ2019 በጀት ዓመት በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተፈራርመዋል።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የተቋማቸው ራዕይ ለማሳካትና የተቋሙ መረጃዎች ወደ ሰፊው ማህበረሰብ ለማስፋት ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋር የስራ ስምምነት መፈራረም ማስፈለጉን አብራርተዋል፡፡

ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር እየተሰሩ የሚገኙት ፕሮግራሞች ከተቋም ገጽታ ግንባታ፣ ደንብ መተላለፎችን ከመከላከል እና ግንዛቤ ከመፍጠር አንጻር መልካም ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል

የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን ዲባባ ተቋሙ ከከተማዋ ልማትና እድገት ጋር አብሮ በማደግ ላይ ያለ ተወዳዳሪና የሌሎች ሚዲያ ተምሳሌት ለመሆኑን እየሰራ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።

ተቋሙ በኤኤምኤን ቴሌቭዥን፣ በኤኤምኤን ፕላስ፤በሬዲዮ፣ በሕትመት እንዲሁም በዲጂታል ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን በፍጥነት እና በጥራት ተደራሽ በማድረግ የብዙኃን አንደበት ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ ተናግረዋል

ተቋሙ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ቋንቋዎች መረጃዎችን ለአድማጭ ተመልካች እያቀረበ መሆኑን ገልጸው ሚዲያው ከተቋሙ ጋር በጋራ በመሆን ባከናወናቸው ስራዎች የባለስልጣኑን የግንዛቤ አድማስ ማስፋት የተቻለ መሆን ጠቅሰው፤ በቀጣይ የአቀራረብ ይዘቱን በማሻሻል ይበልጥ ሳቢ በማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍116👏1