የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.5K subscribers
3.96K photos
13 videos
1 file
93 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በህ-ወጥ መንገድ ለገበያ ሊቀርብ የተዘጋጀ ስጋ መያዙ ተገለፀ

06/09/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**


በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ​በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በወረዳ 11 ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት በተካሄደው ድንገተኛ ኦፕሬሽን በድብቅ የታረደና ለገበያ ሊቀርብ የነበረ ከፍተኛ መጠን ያለው የእንስሳት ስጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተገለፀ።

​ኦፕሬሽኑ የተካሄደው በወረዳ 11 ልዩ ቦታው ቀጠና 01 "ሰው ለሰው እድር ቤት" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን፣ ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በተደረገ ጥብቅ ፍተሻ ጤንነታቸው ያልተረጋገጡ 13 የታረዱ በጎች፣ 14 ፍየሎች እንዲሁም ፅዳቱ ያልተጠበ 312 ኪሎ ግራም ስጋ ተይዟል።

​የወረዳው የደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተክሉ ምንዳ እንደገለጹት የተያዘው ስጋ እንዲወገድ ለአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የተረከበ ሲሆን ድርጊቱን የፈጸሙ ግለሰቦችም በህግ እንዲጠየቁ ተደርጓል።

ኃላፊው አክለውም ህብረተሰቡ መሰል ህገ-ወጥ እርዶችንም ሆነ ማንኛውንም የደንብ መተላለፍ ሲመለከት በነፃ ስልክ መስመር 9995 ጥቆማ በመስጠት ከተቋሙ ጎን እንዲቆም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው
👍6
ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ በከተማችን በሰላም እንዲጠናቀቅ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ መሆኑ ተገለፀ

12/09/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቅድመ ምርጫ በምርጫ እለት እና በድህረ ምርጫ ወቅት የተቀናጀና የተጠናከረ የጥበቃና የሰላም ግንባታ ተግባራትን በማከናወን ሰላማዊ ምርጫ እንዲከናወን የውይይት መድረክ አካሄደ ።

ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ እጅግ ሰላማዊ ፣ ነጻ ፣ ፍትሀዊና ተዓማኒ በማድረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታውን ወደ ላቀ ደረጃ ማሻገር እንደሚገባ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ገልጸዋል ።

አክለውም የደንብ ማስከበር አመራርና ኦፊሰር ምርጫው በከተማችን በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ የሚገኙ ሲሆን ይሄንንም በቀጣይ በምርጫ እለት እና በድህረ ምርጫ ወቅት አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

ለሀገራችን ሰላም እና ደህንነት በጋራ መቆም እንደሚገባ በመድረኩ ተገልጿል ።

ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው
👍1512👏2😢1
ባለስልጣኑ በቀጣይ አምስት ዓመት የደንብ መተላለፎች የቁጥጥር ስራው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለመተግበር እንደሚሰራ ገለፀ

ግንቦት 28 2018 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2022 ዓ ም ራዕዩንና ለማሳካትና ስማርት ሲቲ ለመፍጠር የተጀመረውን ጉዞ እውን ሊያደርግ የሚያስችል የአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድ ላይ ውይይት ተደረገ።

በውይይቱ ተቋሙን በቴክኖሎጂ በማላቅ በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን በመቀነስ በ2022 ዓ.ም አዲስ አበባ ከተማን ለአፍሪካ ከተሞች ተምሳሌት እንድትሆን ባለስልጣኑ ያስቀመጠውን ራእይ እውን የሚያደርግ ነው ሲሉ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ገልጸዋል።

ባለስልጣኑ በቀጣይ አምስት አመት የደንብ መተላለፎች የቁጥጥርና ሂደቶች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመተግበር በከተማ የሚስተዋሉ ደንብ መተላለፎችን በመቀነስ ለነዋሪዎቿ እንዲሁ ለእንግዶቿ ምቹና ሰላማዊ የሆነች አዲስ አበባን ለመረጋገጥ መሆኑ በእቅዱ ተመላክቷል።

ባለስልጣኑ በማዕከል የተጀመረው የቴክኖሎጂ አገልግሎቶች በማላቅ እስከ ታችኛው መዋቅር ተደራሽ በማድረግ የተቋሙን ራዕይና ተልእኮ ባለ ድርሻ አካላትና ህብተሰቡ የሚሳተፉበት ስልት መነደፉን በውይይቱ ተመላክቷል።

ባለስልጣኑ በቀጣይ እውጤት ተኮር ስራዎችን በማከናወን የተገልጋይ ፍላጎትን መሠረት ያደረገ አገልግሎት አሰጣጥ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተገልጿል።

መረጃው:- የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
9👍7