"በከተማው ላይ ሰላም ወዳዱን ማህበረሰብ ያሳተፈ ስራ በመሰራቱ ሰላምና ደህንነቱ የተጠበቀ ከተማ ማስፈን ተችሏል"ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ
ሚያዝያ 29 /2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህግ ማስከበርና መልካም አስተዳደር ክላስተር የ2018 በጀት የ9ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙን ገምግሟል ።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊና የክላስተሩ ሰብሳቢ በግምገማው መድረክ ላይ እንዳሉት በበጀት አመቱ ከከተማው ማህበረሰብ ጋር በቅንጅት በመሰራቱ በርካታ ውጤት ያለው ስራዎች እንደተሰሩ ጠቁመው አዲስ አበባ ከተማ ለዜጎቿ ደህንነት የጸጥታ አጠባበቅ የህግ የበላይነት ለማስፈን ክላስተር በመፍጠርና በቂ ዕቅድ አዘጋጅቶ በርካታ ከሰላምና ፀጥታ ፣ ከደንብ ማስከበር ፣ ከፍትህ ስርአት ፣ ከኢኮኖሚ አሻጥር ፣ ከትራፊክ ደህንነት እና መሰል ተግባራት ላይ ውጤት ያለው ስራ መስራት ተችሏል ብለዋል።
የህግ የበላይነትን ማስፈን በመቻሉ አህጉራዊ አለማቀፍዊ ጉባኤዎች ትላልቅ ሁነቶች የአደባባይ በዓላት በሰላም ተከብረው እንዲውሉና ከስጋት ነጻ የሆኑ ቅድመ የወንጀል መከላከል ትኩረት ያደረጉ ስራዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻሉና ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል ያሉት የቢሮ ኃላፊዋ የጸጥታው መዋቅር መላው ሰላም ወዳዱን ማህበረሰብ በማሳተፍ የወንጀል ምጣኔን ቅነሳ መሰረት ያደረገ የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ የህግ የበላይነት የሰፈነባት የጠላት ሀይሎች ሴራ የማክሸፍ አዋኪ ድርጊቶችን የመከላከያና የመቆጣጠር ስራዎችም መሰራታቸው አብራርተዋል ።
በከተማው ላይ ሰላምና ደህንነት እንዲቀጥል የከተማውን ነባራዊ ሁኔታ የተረዳ የሰላም ሰራዊት የማደራጀት ስምሪት በመስጠት ህገ ወጥ የደንብ ጥሰቶችን መከላከል ህብረተሰቡንም የሰላም ባለቤት በማድረግ ህገ ወጥነትንም የሚጸየፍ ማህበረሰብ በመገንባት ነዋሪው ተባባሪነቱን የጨመረበት ፣ የኮሪደር ልማቱ በህገ ወጦች እንዳይበላሹና ስርቆት እንዳይኖር በጋራ መስራት፣ የኢኮኖሚ አሻጥር የሚፈጽሙ ግለሰቦች ወደ ህጋዊ የግብይት ስርዓት እንዲገቡ የማስቻል ፣ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎች የመቆጣጠርና የመከላከያ ስራዎች መስራት ላይ የተሰሩ ስራዎችን ማስቀጠልና መወሰድ ያለባቸውን ጥንቃቄዎች ከክላስተሩ አባላት ተነስተው ውይይትም ተደርጓል።
በመጨረሻም አሁን ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ እንደ ምክንያት በመጠቀም የነዳጅ ሁኔታን መነሻ በማድረግ ከህግ ስርአት ውጪ የሆኑትን ወደ ስርዓቱ እንዱገቡ የማድረግ ፣ በከተማው ላይ በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከሌብነትና ብልሹ አሰራር የጸዳ ታማኝነት ግልጽነት ያለው ለህብረተሰቡ ግልጽ የሆነ አሰራር መዘርጋት ፣ በፍትህ ስርዓቱ መሰረት ወንጀልንና ወንጀሎተግባር በቀጣይ ትኩረት ተደርገው የሚሰሩ ዋና ዋና ነጥቦች እንዲሆኑ አቅጣጫ ተቀምጧል።
በዘጠኝ ወራት ውስጥ የአዲስ አበባ አስተዳደር የህግ ማስከበርና የመልካም አስተዳደር ክላስተር ምን ምን ጉዳዩችን አከናወኑ የሚሉትን ሀሳቦች በዝርዝር ያብራሩት ወ/ሮ አለም ጸሀይ ማሞ ክላስተር የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ ናቸው
ሪፖርቱን መነሻ በማድረግ ከክላስተሩ ቋሚ ኮሚቴዎች ለተነሱት ሀሳብና አስተያየት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የክላስተሩ ሰብሳቢ ምላሽና ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ሰተዋል።

👍3❤2👏1
ባለስልጣኑ በኮሪደር መሠረተ ልማት ላይ ጉዳት ያደረሱ የግንባታ ድርጅትና ሹፌሮች 410,000 ሺህ ብር መቀጣቱ አስታወቀ
02/09/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ማህሙድ ሙዚቃ ቤት አካባቢ በልማት ኮሪደር በተሰራው የመንገድ መሠረተ ልማት ላይ ጉዳት ያደረሱ የግንባታ ድርጅትና ሹፌሮች በድምሩ 410,000 ሺህ ብር መቀጣቱ አስታወቀ መቅጣቱን አስታወቀ ።
ቅጣቱ ጉዳት ያደረሱት ምንሀር ኮንስትራክሽን የግንባታ ድርጅት 300,000/ሦስት መቶ ሺህ/ ብር ሲቀጣ አሽከርካሪዎቹ እንደ ጥፋታቸው በድምሩ 110,000/አንድ መቶ አስር ሺህ ብር ተቀጥተው በድምሩ 410,000 ሺህ ብር በመቅጣት ለከተማው ልማት ስራ እንዲውል የተደረገ ሲሆን ያቆሸሹትን አስፖልት ወዲያውኑ እንዲያፀዱ ተደርጓል።
ባለስልጣኑ በከተማው ደንብ የሚተላለፉ እና መሠረተ ልማት የሚያበላሹ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ላይ በህጉ መሠረት የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል ።
ማህበረሰቡ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ተቋሙ ጥሪውን ያቀርባል።
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

👍7
ባለስልጣኑ ወንዞችና የወንዞች ዳርቻ የበከለው ዲሊኦፖል ኢንተራሽናል ሆቴል 600,000(ስድስት መቶ ሺህ) ብር መቅጣቱ አስታወቀ
03/09/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በካይ የፍሳሽ ቆሻሻን ወደ ወንዝና የወንዝ ዳርቻ የለቀቀው ዲሊኦፖል ኢንተራሽናል ሆቴል ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር 600,000/ስድስት መቶ ሺህ/ ብር የቅጣት እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።
ድርጊቱ በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ባንቢስ አከባቢ ወደ ወንዝ የሽንትቤት ፍሳሽ በመልቀቅ ብክለቱን ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምርመራ በመረጋገጡ ከዚህ ቀደም እርምጃ የተወሰደ ሲሆን አሁንም በድጋሚ በመልቀቁ የቅጣቱን እጥፍ ተቀቷል።
ከቅጣቱ በተጨማሪ ብክለቱ ለማስቆም ችግሩ እስኪስተካከል የሆቴሉ የችግሩ መንስኤ የሆኑ መጸዳጃ ቤቶቹ እንዲታሸግ መደረጉ ተገልጿል።
ባለስልጣኑ በከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ወንዝና የወንዝ ዳርቻዎች እየለሙ መሆኑ በመግለፅ ወንዞቹን በመበከል ለታለመለት አላማ እንዳይውል በሚያደርጉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች የሚወስደው አስተዳደራዊ እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል አሳውቋል።
ባለስልጣኑ ከተማው ነዋሪዎችና ተቋማት በደንቡ ዙሪያ ሰፊ ግንዛቤ መፍጠሩ አስታውሶ ነዋሪዎችና ተቋማት ከመሰል ተግባራቸው እንዲታቆጠቡ አሳስቧል።
ህብረተሰቡ ለማንኛውም አይነት የደንብ መተላለፍ በነፃ ስልክ 9995 መረጃና ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

👍9👏4
ባለስልጣኑ በኮሪደር መሠረተ ልማት ላይ የደንብ መተላለፍ ለሚፈጽሙ ግለሰቦችና ድርጅቶች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳሰበ
05/09/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በኮሪደር መሰረተ ልማት ላይ ህገወጥ ማስታወቂያ በመስቀል ሳይክል በማቆም ሳር ላይ ለተኙ እና የኮሪደር ልማት ያበላሹ ድርጅቶች 75,000/ሰባ አምስት ሺህ/ ብር የቅጣት እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።
ድርጊቱ በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ማይ ኢንተርቴይመንት የተባለ ደርጅት በኮሪደር መንገድ ስታንዳርዱን ያልጠበቀ ማስታወቂያ በሳይክል በማቆምና ሳር ላይ በመተኛት ብር 25000 የተቀጣ ሲሆን እንዲሁም ሳምቤክ ሪል ስቴት የኮሪደር መንገድ በማበላሸት ብር 50000 በመቅጣት በድምሩ 75,000/ሰባ አምስት ሺህ ብር/ አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድ ከጥፈታቸው እንዲታረሙ ተደርጓል።
ባለስልጣኑ በኮሪደር መሠረተ ልማት ላይ የደንብ መተላለፍ ለሚፈጽሙ ግለሰቦችና ድርጅቶች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እያሳሰበ በከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ወጪ የተሰራውን የኮሪደር ልማት በሚያበላሹ ግለሰቦች እና ድርጅቶች የሚወስደው አስተዳደራዊ እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል።

👍4❤2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
9995 የደንብ ማስከበር የነጻ ስልክ ጥቆማ መስመር
👍7❤1👏1
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በህ-ወጥ መንገድ ለገበያ ሊቀርብ የተዘጋጀ ስጋ መያዙ ተገለፀ
06/09/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በወረዳ 11 ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት በተካሄደው ድንገተኛ ኦፕሬሽን በድብቅ የታረደና ለገበያ ሊቀርብ የነበረ ከፍተኛ መጠን ያለው የእንስሳት ስጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተገለፀ።
ኦፕሬሽኑ የተካሄደው በወረዳ 11 ልዩ ቦታው ቀጠና 01 "ሰው ለሰው እድር ቤት" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን፣ ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በተደረገ ጥብቅ ፍተሻ ጤንነታቸው ያልተረጋገጡ 13 የታረዱ በጎች፣ 14 ፍየሎች እንዲሁም ፅዳቱ ያልተጠበ 312 ኪሎ ግራም ስጋ ተይዟል።
የወረዳው የደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተክሉ ምንዳ እንደገለጹት የተያዘው ስጋ እንዲወገድ ለአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የተረከበ ሲሆን ድርጊቱን የፈጸሙ ግለሰቦችም በህግ እንዲጠየቁ ተደርጓል።
ኃላፊው አክለውም ህብረተሰቡ መሰል ህገ-ወጥ እርዶችንም ሆነ ማንኛውንም የደንብ መተላለፍ ሲመለከት በነፃ ስልክ መስመር 9995 ጥቆማ በመስጠት ከተቋሙ ጎን እንዲቆም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው

👍6