አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋ ለማድረግ ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር መሠረታዊ ስራ መሆኑ ተገለፀ
13/08/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ለሰራተኞች እና ለተገልጋዮች ምቹ የስራ አከባቢ በመፍጠር የተቋሙ የሚሰጠውን ተልዕኮ በስኬት ለመፈጸም ዝግጁ መሆኑ ገለፀ ።
ጽ/ቤቱ ከህብረተሰብ የሚቀርቡ ጥቆማዎች በመቀበል የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ ለዜጎች ፍትሃዊና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የትራንስፖርት አማራጭ ማዘጋጀቱንም የክፍለ ከተማው የደንብ ማስከበር። ሀላፊ መቶ አለቃ ቦጋለ አለሙ ገልፀዋል።
ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የደንብ መተላለፎችን በመቆጣጠር የተሰጠውን ተልዕኮ በውጤት በመፈጸምና በኃላፊነት ከመወጣት ባሻገር ያከናወነው የተቋም ግንባታ የሚበረታታና ሌሎች ጽ/ቤቶች የሚያነሳሳ ነው ሲሉ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ካባ መብራቱ ገልጸዋል ።
በመርሐ ግብሩ የወረዳዎችን የመፈጸም አቅም ለማሳደግ በክፍለ ከተማው ስር ለሚገኙ ለወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤቶች ለትራንስፖርት አማራጭ ለመጠቀምና የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ለማሳደግ የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል ስጦታ ተበርክቶላቸዋል ።
መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡

👍7❤4
የከተማ አስተዳደራችን ተቋማት ጥንካሬ ሰው ላይ የተንጠለጠሉ ሳይሆኑ ቀጣይነት ያላቸው በሲስተም የሚመሩ ጠንካራ ተቋማት የማድረግ ስራ ፍሬው እየታየ ነው።
ዛሬ ጠዋት በደንብ ማስከበር ባለስልጣን የተሰሩ የተቋም ሪፎርም ስራዎችን ጎብኝተናል። ከዚህ በፊት ነዋሪዎች ቅሬታቸውን “ወይ ሀምሳ ወይ አንሳ” የሚል ቅፅል ስም አውጥተውለት እንደነበር አይዘነጋም ።
ይህንን ስም ለመለወጥ እና የነዋሪዎችን እርካታ ለማሳደግ በተከታታይ በተሰራ ሪፎርም በአስተሳሰብ፣ በስነ ምግባር እንዲሁም የዘመነ አሰራር በመተግበር መሰረታዊ ለውጥ አስመዝግቧል ።
ከወረቀት ንክኪ ነፃ፣ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት፣ መረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለመስጠት እና ቅሬታዎችንም ለመፍታት የሚያግዙ እንዲሁም የደንብ ጥሰትንም በቀላሉ በመለየት ለማረም የሚስችሉ ናቸው ።
በተጨማሪም የዜጎች ቀጥታ ተሳትፎ መተግበሪያ፣ በ5 ቋንቋ አገልግሎት የሚሰጥ የጥቆማና ቅሬታ ማቅረቢያ ዘመናዊ የጥሪ ማዕከል (calling center)፣ የሁኔታዎች መከታተያ ክፍል (situation room)፣ ዘመናዊ የስልጠና ማዕከል (Smart training center)፣ ዘመናዊ የቢሮ አደረጃጀት (Smart office)፣ የህፃናት ማቆያ፣ የሰራተኛ ካፍቴሪያ፣ የሸማች ሱቅ፣ የሰፖርት ማዕከል (ጂምናዚየም) ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።
በመጨረሻም በትጋት መሰረታዊ ለወጥ ያስመዘገቡትን የተቋሙን አመራሮች እና የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ቢሯችንን ከልብ አመሰግናለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

❤14👏2