የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.5K subscribers
3.96K photos
13 videos
1 file
93 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋ ለማድረግ ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር መሠረታዊ ስራ መሆኑ ተገለፀ

13/08/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ለሰራተኞች እና ለተገልጋዮች ምቹ የስራ አከባቢ በመፍጠር የተቋሙ የሚሰጠውን ተልዕኮ በስኬት ለመፈጸም ዝግጁ መሆኑ ገለፀ ።

ጽ/ቤቱ ከህብረተሰብ የሚቀርቡ ጥቆማዎች በመቀበል የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ ለዜጎች ፍትሃዊና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የትራንስፖርት አማራጭ ማዘጋጀቱንም የክፍለ ከተማው የደንብ ማስከበር። ሀላፊ መቶ አለቃ ቦጋለ አለሙ ገልፀዋል።

ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የደንብ መተላለፎችን በመቆጣጠር የተሰጠውን ተልዕኮ በውጤት በመፈጸምና በኃላፊነት ከመወጣት ባሻገር ያከናወነው የተቋም ግንባታ የሚበረታታና ሌሎች ጽ/ቤቶች የሚያነሳሳ ነው ሲሉ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ካባ መብራቱ ገልጸዋል ።

በመርሐ ግብሩ የወረዳዎችን የመፈጸም አቅም ለማሳደግ በክፍለ ከተማው ስር ለሚገኙ ለወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤቶች ለትራንስፖርት አማራጭ ለመጠቀምና የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ለማሳደግ የኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል ስጦታ ተበርክቶላቸዋል ።

መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍74