"ኦፊሰሮች ደንብ ሲስከብሩ ህግንና መመሪያን ጠንቅቆ ማወቅና የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በሞያዊ ስነ-ምግባር ሊወጡ ይገባል" ረ/ፕ ኤርሚያስ ከበደ ዶ/ር
26/07/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የልደታ ክ/ከተማ ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በስነ-ምግባር መመሪያዎችና በአገልግሎት አሰጣጥ ስነ-ምግባር ላይ ስልጠና ተሰጠ።
የክፍለ ከተማውና የወረዳ ፅ/ቤት ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የተሰጠው ስልጠና በዋናነት ኦፊሰሩን በሞያዊ ስነ-ምግባር በማነጽ ማህበረሰቡን በቅንነትና በታማኝነት የሚያገለግልበትን መንፈስ ለመገንባትና የከተማ አስተዳደሩ የሚያወጣቸውን አዋጆች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች ኦፊሰሩ በሚገባ ተረድቶ ተግባራዊ እንዲያደርግ ለማስገንዘብ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
ስልጠናው በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የድህረ-ምረቃ መምሪያ ኃላፊ ዋ/ኢር ዶ/ር ኤርሚያስ ከበደ በስነ-ምግባር መመሪያ ቁጥር 03/2015 እና ደንብ ቁጥር 167/2016 ዓ. መሰረት በማድረግ በየአገልግሎት አሰጣጥና በሙያዊ ስነ-ምግባር ላይ ተሰጥቷል።
ዋ/ኢር ዶ/ር ኤርሚያስ በመድረኩ ላይ እንዳብራሩት፤ የደንብ ማስከበር ስራ ውጤታማ እንዲሆን ኦፊሰሩ ህዝብን አክባሪ፣ ሚስጥር ጠባቂ፣ታማኝ፣ታጋሽ እና ብልሹ አሰራርን በመጸየፍ ህብረተሰቡ ሲያገለግልና የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በሞያዊ ስነ-ምግባር ሲወጣ ተቋሙ የህዝብ ተቀባይነት ያገኛል ብለዋል።
በስልጠናው እያንዳንዱ ኦፊሰር የተቋሙ አምባሳደር መሆኑን ተረድቶ፣ ራሱን በመልካም የሞያ ስነ-ምግባር በማነጽ ለሌሎች አርአያ መሆን እንዳለበትም በጥልቀት ተመላክቷል። ይህም በተቋም ግንባታና በህዝብ አመኔታ ላይ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል።
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ የስልጠናው ተሳታፊዎች እንዲህ ያሉ አቅምን የሚገነቡ ስልጠናዎች ህግንና መመሪያን ጠንቅቆ ለማወቅና በመሬት ላይ ያሉ ፈተናዎችን በሞያዊ ስነ-ምግባር ለመወጣት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥሩ ገልጸዋል።
ኦፊሰሮቹ አክለውም በስልጠናው ያገኙትን እውቀት በመጠቀም ህዝብን በታማኝነት በማገልገልና ብልሹ አሰራሮችን በጽናት በመታገል የተቋሙን ገጽታ ለመገንባት ቃል ገብተዋል።
ዘገባው:- የባለስልጣኑ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው

❤19👍2
በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች በ82% መቀነሱ ተገለፀ ።
08/08/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የ2018 በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት በከተማዋ የደንብ መተላለፎችን በመቀነስ እና የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ ረገድ ውጤታማ ሥራዎችን በማከናወኑ በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች 82% መቀነሱን ገለፀ ።
ተቋሙ ሥራውን በቴክኖሎጂ ለማገዝ የኮል ሴንተር (Call Center) እና ስማርት አይሲቲ (Smart ICT) የሥልጠና ክፍሎችን ገንብቶ ወደ ሥራ አስገብቷል ፣ቅሬታዎችን በፍጥነት ለመፍታትና የአገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ ለማድረግ የሚያስችሉ ዲጂታል አሠራሮች ተዘርግተዋል እንዲሁም ሠራተኞችን የአገልግሎት አሰጣጥ እና ሥነ-ምግባር ለማሻሻል የሚያስችሉ የለውጥ ሥራዎች ማከናወኑ አስታውቋል።
ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች እና አመራሮች የንድፈ ሐሳብና የተግባር ስልጠናዎችን በመስጠት በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በሥነ-ምግባር እና በሰብዓዊ መብት አያያዝ ዙሪያ ለውጥ መምጣቱ ተገልጿል ።
በቀጣይ ባለስልጣኑ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራውን በማጠናከርና የህብረተሰቡን ተሳታፊነት በመጨመር የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ የነበሩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል እና የታዩ ክፍተቶችን በማረም አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ማራኪና ሰላማዊ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሠራ አስታውቋል።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡

👍12❤5