የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.15K subscribers
1.96K photos
5 videos
1 file
55 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱ ያስተላልፋል።
👍1
ባለስልጣኑ ከማዕከል እስከ ወረዳ ላሉ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ።
30/04/2016 ዓ.ም
*ቢሾፍቱ*

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማሰከበር ባለስልጣን የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ ላሉ አመራሮች ከታህሳስ 30/2016 እስከ 03/05/2016 ዓ/ም ድረስ በአመራር ክህሎት፣ በእስትራቴጅክ እቅድ አስተቃቀድ፣ በጊዜ አጠቃቀም እና በከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች በሚሰጡ ተጨማሪ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች በቢሾፍቱ የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት በዛሬው ዕለት ስልጠና መስጠት ተጀመረ።

የአቅም ግንባታ ስልጠናውን ያስጀመሩት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንዳሉት ስልጠናው በ2016 በጀት ዓመት ከያዝናቸው እቅዶች መካከል አንዱ መሆኑንና ከተማዋን የሚመጥንና ለውጥ አምጪ አመራር ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል።

ተቋሙ የከተማዋን የደንብ መተላለፍ ለመከላከልና ስርዓት ለማስያዝ በርካታ ስራዎች በመስራት ላይ እንደሚገኝ አስታውሰው፤ የአመራሩን ብቃት ይበልጥ ለማጎልበት በሚያበቁ ዕውቀቶች በኢንስቲትዩቱ ሙሁራንና ለቀጣይ ሶስት ቀናት ስልጠናው እንደሚሰጥ አስታውቋል።

Leadership and time management ርዕስ ያደረገ ስልጠና የሰጡት የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢኒስቲትዩት አማካሪ እና አሰልጣኝ አቶ ጀማል አህመድ ሲሆኑ፤ ስልጠናውም አሳታፊና አነቃቂ የሆነ እንደነበረ ከተሳታፊዎች ተገልጿል።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
1
ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት እና የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት አባቶች ጋር የጥምቀት በዓል አከባበርን በተመለከተ ውይይት አድርገዋል::

በውይይቱ የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን አባቶቹ የገለፁ ሲሆን ቤተ-ክርስቲያኒቷን የማይወክሉ ንግግሮችን እና ድርጊቶችን ፈፅሞ እንደማይቀበሉና እንደሚያወግዙ ይህንንም ለምዕመናቸው ግልፅ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል::

ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በበኩላቸው በዩኒስኮ በቅርስነት የተመዘገበው የጥምቀት በዓል አከባበር ሃገራዊ ቅርስ እንደመሆኑ በዓሉ ሃይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በሰላም እንዲከበር የሃይማኖት አባቶቹ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል::

የሃይማኖት አባቶቹ የከተማ አስተዳደሩ ለበዓሉ አከባበር የተለመደውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል::
ባለስልጣኑ የበጀት ዓመቱ የስድስት ወር ዕቅድ አፈፃፀሙን ከተቋሙ አመራሮች ጋር ገመገመ።

ጥር 03/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2016 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀሙን የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች ጋር ገመገመ።

ተቋሙ በግማሽ ዓመቱ ለማሳካት ያቀዳቸውን ስራዎች በውጤት ያጠናቀቀበትና ካለፈው በጀት ዓመት የተሻለ ብዙ ውጤቶች ያሳካበት መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ሪፖርቱ በጋራ መገምገሙ ሁሉም የራሱን ክፍተት በማየት ለማረም እና በሪፖርቱ ያልተገለፁ ስራዎች ለማስተካከል አንደሚረዳ በመድረኩ ተገልጿል።

የተጠመረውን የዕቅድ አፈፃፀም ሪፓርቱን ያቀረቡት የዕቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል አድማሱ ተክሌ ሲሆኑ የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀሙን ከዝግጅት ምዕራፍ እስከ ትግበራው ድረስ ታቅደው የተከናወኑ ስራዎች እና ና ከዕቅድ ውጭ የተከናወኑ ተግባሮች በሪፖርቱ ቀርበዋል።

የተቋሙ አመራሮች በሪፖርቱ ላይ ሳይካተቱ የቀሩ ነጥቦች በማንሳት በቀጣይ ተካተው እንዲቀርቡ እና በሪፖርቱላይ የተለያዩ ሀሳብና አስተያየቶችን ሰጥተዋል።

በመጨረሻም የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተገኝተው ሪፖርቱ ከክፍለ ከተማና ወረዳ ተግባራት ጋር ተናቦ በተሰጠው ሀሳብና አስተያየት መሠረት በማዘጋጀት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንደሚደረግበት ገልፀዋል።
ህብረተሰቡ አዋኪ ድርጊቶች በሀገር ላይ የሚያስከትሉት ጉዳት በመረዳት በሚወሰደው እርምጃ ከባለስልጣኑ ጎን ሊቆም እንደሚገባ ተገለፀ።

ጥር 03/2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ **

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ከሁሉም ወረዳዎች ትላልቅ ሆቴሎችና ፤ላውንጆች ፤ሬስቶራንቶች ላይ እርምጃ ወሰዶ የወረሳቸው የሺሻ ማስጨሻ ቁሳቁሶዎች በማቃጠል አስወገደ፡፡

በክፍለ ከተማው በተለይ ትላልቅ ሆቴሎች ፤የምሽት ክለቦች ሥራው በልዩ ሚስጥራዊ ኦፕሬሽን ከፀጥታ አካላት በጋራ በመሰራቱ አዋኪ ተግባር ሲፈፅሙ በመገኘታቸው እርምጃ ተወሰዶ ቁሳቁሶቹን መወረሳቸው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሃላፊ ሻምበል ኑርልኝ ገብረኪዳን ገልፀዋል፡፡

ክፍለ ከተማው በዚህ 2016 በጀት አመት የደንብ መተላለፍ ተግባራትን ለመከላከል በወሰደው ተልዕኮ መሠረት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ግብረ ሀይል እና ከፀጥታ ተቋማት አባሎች በተገኙበት የተወረሱት 4970 የሺሻ ማስጠቀሚያ ዕቃዎች በዛሬው ዕለት በማቃጠል ማስወገዱን የክፍለ ከተማው የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አሳውቀዋል ፡፡

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የደንብ መተላለፍን ለመከላከል በተለያየ የአሠራር ሥልት ለህብረተሰቡ ሠፊ ግንዛቤ በተለያየ ውይይት መድረኮች በማዘጋጀት ቤት ለቤት፤በብሮሸርና በበራሪ ወረቀት የታገዘ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች ለበርካታ የህብረተሰብ ክፍል ማድረጉን ጠቅሰው ህብረተሰቡ አዋኪ ድርጊቶች በሀገር ላይ የሚያስከትሉት ጉዳት በመረዳት በሚወሰደው እርምጃ ከባለስልጣኑ ጎን ሊቆም እንደሚገባ እንዳለበት ሻምበል ኑርልኝ መልዕክት አስተላልፈዋል ፡፡

መረጃው ፡- የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ነው ፡፡
ባለስልጣኑ መጭውን የጥምቀት በዓልን አስመልክቶ ውይይት አካሄደ።

06/05/2016ዓ.ም
*አዲስ አበባ*

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2016 የጥምቀት በዓልን አስመልክቶ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ከማዕከል ሰራተኞች ጋር በዛሬው ዕለት በተቋሙ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አካሂዷል።

የ2016 ዓ.ም የጥምቀት በዓል አከባበር ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር የባለድርሻ አካላትና የህዝቡ ሚና አስመልክቶ የተዘጋጀውን ሰነድ ያቀረቡት የባለስልጣኑ የስነምግባር እና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዬብ ከበደ እንዳሉት ሁሉም የአከባቢው የሰላም ዘብ መሆኑን አምኖ መቀበል አለበት ብለዋል።

አክለውም በህትማማችና ወንድማማች መንፈስ ሁሉም የድርሻውን በመወጣት በዓሉ ፍፁም ሰላማዊነቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር የበኩላችንን አስተዋፅኦ እየተወጣን፤ በአከባቢያችን ለየት ያለ እና አጠራጣሪ ነገር ስንመለከት ፈጥነን በየአቅራቢያችን ለሚገኝ የፀጥታ ኃይል ማመልከት ይኖርብናል ብለዋል።

በቀረበው ሰነድ ላይ ከሰራተኞች ጋር ውይይት በማካሄድ በተነሱት ሀሳቦች ላይ ማብራሪያ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።

ዘገባው:-የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
2