የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.15K subscribers
1.94K photos
5 videos
1 file
55 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ፅዱ እና ውብ ኢትዮጵያ ለመፍጠር ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀላፊነት አለበት

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተጀመረውን የ"ፅዱ ጎዳና -ኑሮ በጤና" ንቅናቄ ጥሪ ተቀብለው የተቋማችን አመራሮች እና ሰራተኞች "ፅዱ ኢትዮጵያ"  ለመፍጠር በተጀመረው ዲጂታል ቴሌቶን ላይ በንቁ ተሳትፎ ተቀላቅለዋል።

ጥሪውን ተቀብለው የ“ጽዱ ጎዳና-ኑሮ በጤና” ንቅናቄን ለተሳተፉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እና በራሳቸው ስም ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

ሌሎች ያልተሳተፋችሁ አመራሮች እና ሰራተኞች ይህንን የበጎ ተግባር አላማ መሳካትም ሁሉም ሰው ያገባኛል በሚል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248 የ“ጽዱ ጎዳና-ኑሮ በጤና” ንቅናቄን እንዲቀላቀሉና በስራው የራሳችሁ አሻራ እንድታስቀምጡ እና ሌሎችም እንዲቀላቀሉ እንድታስተባብሩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እና በራሳቸው ስም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል::

በመጨረሻም እንደ ተቋማችን የተሠበሠበው ብር መረጃው ተሰብስቦ ለተቋሙ ሪፖርት መደረግ እንዳለበት ገልፀዋል።

ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣኑ ዋና ስራ-አስኪያጅ
👍7
"በጎነት ለራስ ነው ካለን ላይ አካፍለን እና ተካፍለን መብላት ኢትዮጵያዊ ባህላችን ነው" አቶ ዳኜ ሒርጳሣ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ

24/08/2016 ዓ.ም
*አዲስአበባ *

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤቱ የፋሲካ በዓልን አስመልክቶ የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አከናወነ።

በመርሃ ግብሩ የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳኜ ሒርጳሣ እንደገለፁት በዛሬው ዕለት ለሚያሳድጋቸው 9 ህፃናት ከሰራተኛው ወርሀዊ መዋጮ የተሰበሰበው በገንዘብ ለእያንዳንዳቸው 1300 ብር እና በዓይነት በጎፈቃደኞችን በማስተባበር ዱቄት፤ መኮረኒ፤ሩዝ፣ሳሙናና ሶፍት በስጦታ ማበርከቱን ገልፀዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም "በጎነት ለራስ ነው ካለን ላይ አካፍለን እና ተካፍለን መብላት ኢትዮጵያዊ ባህላችን ነው" በማለት በአሉን በአብሮነት እና በጋራ ለማሳለፍ በማስብ ለፋሲካ በዓል መዋያ የሚሆን የማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር ለ54 ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች ፣9 የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የሚያሳድጋቸው ህፃናት እንዲሁም 14 ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የፅ/ቤቱ ሰራተኞች ማዕድ ማጋራታቸውን ገልፀዋል፡፡

በዕለቱም በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙልጌታ ተስፋዬ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ህገወጥነት ከመከላከልና እርምጃ ከመውሰድ ባሻገር ለአቅመ ደካሞች ቤት መገንባትና ለወገኖቹ አጋዥ መሆኑ በመግለፅ ህብረተስቡ ይህንን በመረዳት ከደንብ ማስከበር ጋራ በመሆን ህገወጥነትን መከላከል እንዳለበት አሳስበዋል ፡፡

ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማ ለመስጠት ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ።
👍2
ባለስልጣኑ ዝቅተኛ ደመወዝ ላላቸው የተቋሙ ማዕከል ሰራተኞች የበዓል ስጦታ አበረከተ

ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ309 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማውጣት ለባለስልጣኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የበዓል ስጦታ አበረከተ፡፡

የበዓል ስጦታ ያበረከቱት የባለስልጣኑ ዋና ስራ-አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የበዓል ስጦታ መስጠትና ማዕድ ማጋራት የመተሳሰብ፣የአብሮነት፣ የመደጋገፍ እንዲሁም ወንድማማችነትና አንድነትትን የሚያጠናክር መሆኑን ገልፀው ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን ለበዓሉ አደረሳችሁ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በፕሮግራሙ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በመገኘት በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ እና የመረዳዳት እንዲሆን በመመኘት ለበዓሉ የተዘጋጀውን ስጦታ ለሰራተኞች አበርክተዋል።

ለተጨማሪ መረጃ፦
የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ፎሎው፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
የፌስ ቡክ ገፃችን፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082525711518&mibextid
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/codeenforcement
የዩቱብ ቻናላችን
https://youtube.com/@A.A.C.ACODEENFORCEMENT
የቲክቶክ አካውንታችን
https://www.tiktok.com/@addisababacodeenforcemen
የትዊተር/X/ ሚዲያ ገፃችን
https://x.com/Addis_Denb?t=u8wW3qnxWk48GYzJ4RD96Q&s=09
ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ!
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከየአዲስ አበባ ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲና ከአዲስ ሚዲያ ጋር የተቋማት ቅንጅታዊ ስምሪት በሚል መሪ ቃል የተደረገው የፓናል ውይይት መድረክ ፕሮግራም ዛሬ ከ2 ሰዓት ዜና በኋላ በአዲስ ቲቪ ይቀርባል እንድትከታተሉ ተጋብዛችኋል።
ለነዋሪዎች የበዓል ቅርጫ እርድ ክልከላ አለመደረጉ ተገለፀ

ሚያዚያ 25 ቀን 2016 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**

በአዲስ አበባ ከተማ በዘንድሮዉ ዓመት የሚከበረዉን የትንሳኤ በአል አስመልክቶ ህብረተሰቡ በየቤቱ በእርድ መልክ የሚጠቀመዉን እና በየአካባቢዉ የቁም እንስሳትን ቅርጫ በማረድ የሚከፋፈለዉን ተከልክሏል በሚል በማህበራዊ ሚዲያው መረጃ እየተሰራጨ ሀሰተኛ መሆኑ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የቅርጫ ስጋ እርድ ክልከላ ያልተደረገ መሆኑና በየአካባቢዉ በህገ ወጥ መንገድ እርድ በመፈፀም ለሆቴሎች እና ለስጋ ቤቶች በማከፋፈል ተግባር ላይ የሚገኙ አካላት የቁም እንስሳቱ ጤንነት ባልተረጋገ ጠበት ሁኔታ የከተማዉን ነዋሪ ጤንነት ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርግ ገልጿል።

የከተማችን ነዋሪ በዓላትን ሽፋን በማድረግ ጤንነቱ ያልተረጋገጠ እንስሳት አርዶ ማከፋፈል በጤና ላይ የሚያደርሰዉን ጉዳት ግምት ውስጥ በማስገባት በህገወጥ እርድ የሚሰማሩ አካላት በሚደረገዉ ቁጥጥር ተባባሪ እንዲሆን መልዕክት ተላልፏል።

መረጃው፦የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ነው::
6👍2
እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም የፍቅር የደስታ እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ ይመኛል።

ባለስልጣኑ በከተማዋ የሚፈፀሙ የደንብ መተላለፎችን በመከላከል ፣በመቆጣጠርና ተፈፅሞ ሲገኝ እርምጃ በመውሰድ ከተማዋ ለነዋሪዎቿና ለእንግዶቿ ምቹ እንድትሆን ለማድረግ እየሠራ ይገኛል።

ሰለሆነም መላው የከተማው ህብረተሰብ ከባለስልጣኑ ጎን በመሆን መዲናችን ህገ-ወጥነትና የደንብ መተላለፎች የማይስተዋልባት ከተማ ለማድረግ በጋራ እንስራ እያልኩ በዓሉ የሠላም፣ የፍቅር እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
             
                     መልካም በዓል!
                   ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን  ዋና ስራ አስኪያጅ
👍6