የባለስልጣኑ የ2ኛ ዙር የአካል ብቃትና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና ሂደት የመስክ ምልከታ ተደረገ
22/03/2018 ዓ.ም
** አዲስ አበባ **
በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ ሰንዳፋ ካምፓስ ለአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኦፊሰሮች እየተሰጠ ያለው የአካል ብቃትና የንድፈሀሳብ ስልጠና የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ፣ በስልጠናው አስተባባሪዎች እና በዩንቨርስቲው አመራሮች የስልጠና ሂደቱን ምልከታና ጎብኝት ተደርጓል።
በመስክ ምልከታው ስልጠናው በተያዘለት ጊዜና ፕሮግራም በጥሩ ዲሲፕሊን እየተሰጠ መሆኑን ተመልክተዋል።
ሰልጣኞቹ የተግባቦት ጥበብ በንድፈ ሀሳብ ስልጠና ሀገር ወዳድነት፣የሰብዓዊ መብት አያያዝ፣የሃይል አጠቃቀም፣ አገልግሎት አሰጣጥ እና የአካል ብቃት ስልጠና በተገቢው መንገድ እተከታተሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል።
ሰልጣኝ ኦፊሰሮች በበኩላቸው እየተሰጣቸው ያለው ስልጠና ለቀጣይ ስራቸው እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ገልፀው ስልጠናው በቀጣይ ቀናትም በተዘጋጀው ፕሮግራም መሰረት እንደሚቀጥል ተገልጿል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ፦ https://linktr.ee/aacodeenforcement

👍3❤1
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በህገወጥ እርድና እንሰሳት ዝውውር የግንዛቤ ማስጨበጫ የህዝብ ውይይት መድረክ አካሄደ
22/03/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በህገ-ወጥ እንሰሳት እርድና ዝውውር ላይ የሀይማኖት አባቶች፣አባ ገዳዎች ፣ሀደ ሲንቄዎች፣ሲቪክ ማህበራት፣ታዋቂ ግለሰቦች፣ የእድር መሪዎች፣የብሎክ አስተባባሪዎች፣ሴቶች፣ወጣቶች፣ ሰላም ሰራዊት፣የልኳንዳ ቤት ባለቤቶች በተገኙበት በህገወጥ እርድና እንሰሳት ዝውውር የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄና የህዝብ ውይይት መድረክ አካሄደ።
መድረኩ በሀይማኖት አባቶች፣በሀገር ሽማግሌዎች እና አባ ገዳዎች ምርቃት የተጀመረ ሲሆን በመድረኩ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መዓዛ ተክሉ እንደተናገሩት ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት እርምጃ ከመውሰዱ በፊት ለህብረተሰቡ በደንብ መተላለፎች ላይ ሰፊ ግንዛቤ እየፈጠረ መሆኑን ገልፀው በዛሬው ዕለትም በህገወጥ እርድና እንሰሳት ዝውውር ላይ ለህብረተሰቡን ግንዛቤ በመስጠት በጋራ በመስራትእንደሚገባ ገልፀዋል።
አክለውም እራሳችንን ከተለያዩ በሽታዎች እና ጤንነቱ ያልተረጋገጠ ስጋዎችን በየወንዝ ዳርቻዎች ፣በየአካባቢያችሁ ጨለማን ተገን አድርጎ ባልተፈቀደ ቦታ ፣በግለስብ ቤቶች ከሚታረዱ ህገወጥ እርዶች ከመመገብ እንቆጠብ ሲሉ አሳስበዋል።
በእለቱ ህገወጥ እርድ ሲከናወን ከህብረተሰቡ የተደበቀ አይደለም ከዚህ ጋር ተያይዞ ደንብ ተላልፈው ሲገኙ ጥቆማ በመስጠት እና ከተቋሙ ጎን በመቆም ደንብ መተላለፍን መቀነስ እና ማጥፋት እንደሚቻል ገልፀው ደንብ ተላልፎ የሚገኝ ማንኛውም ግለሰብ ይሁን ድርጅት ደንብና መመሪያው ባስቀመጠው መሰረት እርምጃ እንደሚወሰድበት ተገልጿል ፡፡
በመድረኩም የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የስልጠና ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ጌታሁን ኃብተ ማሪያም በህገወጥ እርድና እንሰሳት ዝውውር ሰነዶችን አዘጋጅቶ በማቅረብ ሰፊ የህዝብ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በመጨረሻም ህብረተሰቡ ከደንብ ማስከበር ጎን ለመስራት ተነሳሽነት መኖሩን ገልፀው ከመድረኩ የተነሱትን ሀሳብና አስተያየት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መዓዛ ተክሉ፣የደንብ መተላለፍ መከላከል እና ስልጠና ስራዎች አስተባባሪ ወ/ሮ ንፁህ ታጠቅ፣የስልጠና ቡድን መሪ አቶ ጌታሁን ኃ/ማሪያም በጋራ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ተጠናቋል፡፡
በአዲስአለም ከፈለኝ

👍7❤6
የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰራተኞች የስራ ልምድና ተሞክሮ ልውውጥ አደረጉ
23/03/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰራተኞች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጋር በህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራዎችላይ የልምድና ተሞክሮ ልውውጥ አደረጉ።
በልምድ ልውውጡ ላይ የትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አበበ ቸርነት ስለ ተቋማቸው ተግባር እንዲሁም የስራ ክፍሉን መዋቅርና ዝርዝር ስራዎችን ሰፊ ገለፃ አድርገዋል።
በልምድ ልውውጡ ወቅቱን የሚጠይቀው የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ስራዎችን በማዘመን የተሻለ የመረጃ ምንጭ መሆንእንደሚገባ ተገልጿል።
በተቋሙ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት እየተተገበሩ ያሉ የህዝብ ግንኙነት፣የህትመት ውጤቶች ፣የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምና የመረጃ አደረጃጀትና ተደራሽነት ስራዎች ዙሪያ ማብራሪያና በመስጠት የስራዎች ምልከታ ተደርጓል ።
የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን ማሳደግ ስራዎችን ወደ ህብረተሰቡ ለማድረስ ከፍተኛ ጠቀሜታ መኖሩንና ስራዎች በሚሰሩበት ወቅት እና ለህብረተሰቡ ተደረሻ ሲደረግ ጥራታቸውን በጠበቀ መልኩ ሊሆን እንደሚገባ አቶ አበበ ገልጸዋል ።
የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ ለተደረገላቸው የልምድና ተሞክሮ ማጋራት አመስግነው ከትምህርት ቢሮ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም፣የመረጃ አደረጃጀት አና የሚዲያ ሞኒተሪንግ ተግባራትን የወሰዱትንም ልምድ ወደ ተቋማቸው በማምጣት የኮሙኒኬሽን እና የህዝብ ግንኙነት ስራዎች አጠናክረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
መረጃው ፡-የአዲስ አበባ የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

👍4❤1