የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.36K subscribers
2.65K photos
5 videos
1 file
63 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ የወርቃማ ሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር አከናወነ

22/03/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሰኞ ማለዳ ከስራ ገበታ በፊት የሚያካሂደው የእውቀት ሽግግር ፕሮግራም ከተቋሙ ውጪ የሆነ እንግዳ በመጋበዝ የተቋም ውጤታማነት በሚል ርዕስ የባለስልጣኑ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ሳምንቱን ንቁ ሆነን ዉጤታማ ስራ ለማከናወንና በየሳምንቱ ከሰራተኞቻችን ጋር እንደቤተሰብ እየተማማርን መልካም ምኞት በመለዋወጥ ያለንን እውቀት በማካፈል ምንማማርበትና ልምድ የምንለዋወጥበት ነው በማለት አሁን ላይ እየተጠናከረ እየመጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል ።

አክለውም በተቋማችን ምቹ የስራ አከባቢ በመፍጠር እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጡን የተሻለና ዘመናዊ በማድረግ በህብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ሰራተኞቹም ለስራ ተነሳሽነት ያለቸው መሆን እንደሚገባ ተናግረዋል ።

የዕለቱ የወርቃማ ሰኞ እንግዳ የግል ከፍተኛ ተቋማት ማህበር ዋና ሰራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ገበየሁ ተቋማዊ ዉጤታማነት ለፐብሊክ ሰርቪስ በሚል ርዕስ ለባለስልጣኑ አመራሮች ሰራተኞች የተዘጋጀ ሰነድ አቅርበዋል ።

በሰነዱ ተቋማዊ ውጤታማነት ከሲቪል ሰርቪስ አንጻር ምን እንደሚመስል ፣ ለተቋማዊ ውጤታማነት አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ጉዳዮች እና የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ መንገዶች በዝርዝር ቀርበዋል ።

ተቋማዊ ውጤታማነት አንድ ተቋም ያስቀመጣቸውን ግቦች በምን ያህል ደረጃ ማሳካቱ ፣ ለሰራተኞች ምቹ አከባቢ ስለመፍጠሩ እና የተገልጋዩችና የህብረተሰቡን ፍላጎት የማርካቱ አጠቃላይ የግምገማ ውጤት ማሳያና መገለጫ መሆኑን አቶ ተፈራ ገልጸዋል ።

አክለውም ተቋማዊ ውጤታማነት በተግባራዊ ጥረት እና በተቀናጀ ስራ የሚረጋገጥ መሆኑን ተናግረዋል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች
👍2
የባለስልጣኑ የ2ኛ ዙር የአካል ብቃትና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና ሂደት የመስክ ምልከታ ተደረገ

22/03/2018 ዓ.ም
** አዲስ አበባ **

በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ ሰንዳፋ ካምፓስ ለአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኦፊሰሮች እየተሰጠ ያለው የአካል ብቃትና የንድፈሀሳብ ስልጠና የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ፣ በስልጠናው አስተባባሪዎች እና በዩንቨርስቲው አመራሮች የስልጠና ሂደቱን ምልከታና ጎብኝት ተደርጓል።

በመስክ ምልከታው ስልጠናው በተያዘለት ጊዜና ፕሮግራም በጥሩ ዲሲፕሊን እየተሰጠ መሆኑን ተመልክተዋል።

ሰልጣኞቹ የተግባቦት ጥበብ በንድፈ ሀሳብ ስልጠና ሀገር ወዳድነት፣የሰብዓዊ መብት አያያዝ፣የሃይል አጠቃቀም፣ አገልግሎት አሰጣጥ እና የአካል ብቃት ስልጠና በተገቢው መንገድ እተከታተሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል።

ሰልጣኝ ኦፊሰሮች በበኩላቸው እየተሰጣቸው ያለው ስልጠና ለቀጣይ ስራቸው እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ገልፀው ስልጠናው በቀጣይ ቀናትም በተዘጋጀው ፕሮግራም መሰረት እንደሚቀጥል ተገልጿል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ፦ https://linktr.ee/aacodeenforcement
👍31